ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቀበሌያት በፈፀሙት አሰቃቂ የተባለ ጥቃት ከ40 በላይ ዜጎች እንደተገደሉ ታወቀ
(መሠረት ሚድያ)- የትናንቱ ጥቃቱ የደረሰው በክልሉ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ጋር በሚዋሰንባቸው የዱግዳ ቦራ ወረዳ ቀበሌያት ሲሆን የሶዶ ጉራጌ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ነበር ተብሏል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ሸኔ በማለት የሚጠራው ታጣዊ ቡድን) ጥቃቱን እንደፈፀማ ከስፍራው እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በዚህም ቢርቢርሳና ጋሌ ተብለው በሚጠሩ ቀበሌያት ልዩ ስማቸው ደረባ፣ ኩሬ እንዲሁም ቢጢሲ ተብለው በሚታወቁ ስፍራዎች አሰቃቂ ጥቃት መድረሱ ተነግሯል።
ጥቃቱ ከምሽቱ 2:00 ገደማ ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት መካሄዱ የታወቀ ሲሆን ሕጻናትን ጨምሮ እናቶችና አረጋውያን መገደላቸውንም ተሰምቷል።
የተከፈተባቸውን ጥቃት መመከት ያልቻሉ አርሶ-አደሮች ቤታቸው ውስጥ እያሉ በእሳት እንዲቃጠሉ በማድረግ ከነከብቶቻቸው እንዲሞቱ መደረጉንም ነዋሪዎች ገልፀዋል።
''በጥይት ከተገደሉት ከ40 እስከ 44 ከሚደርሱት ሰዎች ባሻገር ከተቃጠሉ ቤቶች እስካሁን ጭስ አለ'' ይላሉ ነዋሪዎች። ሰውን ጨምሮ ከብቶች እና እህል አብሮ የነደደ፤ የወደመ በመሆኑ የሟቾችን ቁጥርና የአደጋውን ጥቅል ቀውስ በትክክል ማወቅ እንዳልተቻለም ገልፀዋል።
ይህንን ጥልቅ ኃዘን በሌሊት የሰሙ የሶዶ-ክስታኔ የተረፉትን ወገኖቻቸውን ለማፅናናትና ያለወላጅ የቀሩ ሕፃናትን ለማሰባሰብ በቦታው ተገኝተው የደረሰውን ሃዘን እየተመለከቱ ነበር ተብሏል፣ መሪር ሀዘንም በሥፍራው ተከስቷል።
ይሁንና በፌደራል፣ በክልል ሆነ በአካባቢው ባለስልጣናት እና የፀጥታ አካላት ስለ አሰቃቂ ግድያው እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia