ኢትዮጵያ ካላት 120 ሚልዮን ህዝብ 86 ሚልየኑ በድህነት ውስጥ እንደሚኖር አንድ ጥናት አረጋገጠ
(መሠረት ሚድያ)- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ኦክስፎርድ በጋራ ያዘጋጁት ይህ ጥናት እንደጠቆመው ህንድ 234 ሚልዮን በድህነት የሚኖሩ ዜጎችን በመያዝ በአለም በአንደኝነት ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ፓኪስታን በ93 ሚልዮን ሁለተኛ፣ ኢትዮጵያ በ86 ሚልዮን ሶስተኛ፣ ናይጄርያ በ74 ሚልዮን አራተኛ እንዲሁም ዴሞክራቲክ ኮንጎ በ66 ሚልዮን አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
እነዚህ አምስት ሀገራት ከአለማችን 1.1 ቢልዮን ድሀ ህዝቦች መሀል 48 ፐርሰንቱን እንደሚይዙ የተጠቀሰ ሲሆን ከእነዚህ የአለማችን ህዝቦች መሀል 455 ሚልዮኑ ጦርነት በሚካሄድባቸው ሀገራት ይገኛሉ ብሏል።
ኢትዮጵያ ካላት 120 ሚልዮን ህዝብ 86 ሚልየኑ ወይም 72 ፐርሰንት ገደማው በድህነት ውስጥ እንደሚኖር ቢረጋገጥም ከመንግስት የሚወጡ ተከታታይ ሪፖርቶች ኢኮኖሚው እንዳደገ የሚጠቁሙ ናቸው።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia