#ከዜናዎቻችን| የፋይናንስ ተቋማት ፌዴሬሽን በአዲሱ የባንክ ሰራተኞች የገቢ ግብር ደንብ ላይ ተቃውሞ አነሳ
(መሠረት ሚድያ)- የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ሰራተኞች ማህበራት ኢንደስትሪ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን በፃፈው ደብዳቤ ብሄራዊ ባንክ ባወጣው አነስተኛ የወለድ ምጣኔ ለባንክ ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ብድር እንዲነሳ መደረጉን ተቃውሟል።
መሠረት ሚድያ የተመለከተው ይህ ደብዳቤ እንደሚለው አዲሱን የግብር ገቢ ደንብ ተከትሎ ባንኮች፣ ኢንሹራንስ እና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ለሰራተኞቻቸው በሚሰጧቸው ጥቅማ ጥቅሞች ላይ የአይነት ጥቅም ታክስ በመሰብሰብ ለታክስ ሰብሳቢው ተቋም ገቢ እንዲያደርጉ መታዘዛቸውን ተከትሎ ባንኮች ከጥቅምት ወር 2017 ጀምሮ ይህንኑ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በደብዳቤ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ ብሏል።
ይህ አካሄድ የፋይናንስ ተቋማቱን እና ሰራተኞቻቸውን ይጎዳል ያለው የባንኮች ፌዴሬሽን ሰራተኞች ከፋይናንስ ተቋማት ይለቃሉ የሚል ስጋት እንደፈጠረ ጠቁሟል።
የባንክ ሰራተኞች ከሚሰሩባቸው ባንኮች ለቤት እና መኪና ግዢ በአነስተኛ ወለድ ለወሰዱት ብድር የሚከፍሉት አነስተኛ ወለድ ከገበያው ወለድ ጋር ያለው ልዩነት ተሰልቶ የሚመጣው ልዩነት እንደ ገቢ ተቆጥሮ ግብር እንዲከፍሉ የተወሰነው በቅርብ ሳምንታት ነበር።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ሕብረት ባንክ አ.ማ ከጥቅምት 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከሰራተኛው የወር ደመወዝ ላይ እንዲቆረጥ የፃፈውን ደብዳቤ ተመልክተናል።
በዚህም መሰረት የባንኩ ሰራተኞች "ሌሎች ባንኮች ክፈሉ ሳይባሉ እኛ ብቻ ተለይተን መክፈል የለብንም" በማለት ሲከራከሩ ቆይተው አሁን ግን በግዳጅ ክፈሉ እየተባልን እንገኛለን ብለው ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።
@MeseretMedia