#ከዜናዎቻችን| መንግስት ዘንድሮ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በታክስ መልክ ከህዝብ እና ከንግዱ ማህበረሰብ ለመሰብሰብ አቅዷል
(መሠረት ሚድያ)- በዘንድሮ አመት የፌደራል እና የክልል ገቢዎች መስሪያ ቤቶች በሁሉም ዘርፍ ላይ ምንም አይነት መዝገብ ቢቀርብ እርሱን ውድቅ በማድረግ በራሳቸው ስሌት ጭምር እጥፍ እና ከዛ በላይ የሆነ ታክስ እያስከፈሉ እንደሆነ ታውቋል፣ ይህ ደግሞ የታክስ ከፋዩን ማህበረሰብ ማማረር ጀምሯል።
"እያቀረብነው ያለው መዝገብ ጥቅሙ ምንም እየሆነ ነው" የሚሉት ታክስ ከፋይ ነጋዴዎች ግብር መክፈላችን ተገቢ ከመሆኑ ጋር እየተጣለብን ያለው የተጋነነ ግብር ከስራ ውጪ የሚያደርግ ነው ብለው ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።
አክለውም "ከላይ ትእዛዝ መጥቷል" እያሉ ኪሳራ እና ባዶ መቀበል አቁመዋል ብለው ሁኔታው ከበፊቱ እንደተባባሰ ገልፀዋል።
"ገቢዎች የቀረበላቸውን መዝገብ ሳይመለከቱ ደስ ያላቸውን ጨምረው ክፈሉ ይላሉ። ይሄ ደግሞ ነጋዴውን እያጨናነቀ ነው ያለው። ካለው የስራ መቀዛቀዝ፣ ፈረሳ፣ ኮሪደር ልማት ግንባታ፣ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ያሉ ግጭቴች ጋር ተዳምሮ ከሌለን አቅም ላይ የሚጣለው ግብር ከስራ ውጪ የሚያደርግ ነው ብለው ነጋዴዎቹ አቤቱታቸውን አሰምተዋል።
"ለምሳሌ እኔ አምና ከነበረኝ ገቢ ላይ በ2016 በግማሽ ቅናሽ አሳይቷል፣ ይሄም የሆነው በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ባለው ጦርነት ምክንያት ገበያ በመቀዝቀዙ ነው። ሆኖም ግን አምና ከከፈልኩት ግብር ላይ ዘንድሮ በእጥፍ ግብር ተወስኖብኛል" ያለው አንድ አስተያየት ሰጪ ይሄ መሬት ላይ ካለው አካሄድ ጋር ያልተጣጣመ ህግ እና መመሪያ የሚያስከትለው መቃወስ ከባድ ነው ብሏል።
አክሎም "ከሰሞኑ የገቢዎች ሚኒስቴር ባካሄደው የ 4 ወር አፈፃፀም ግምገማ ወደፊት ኪሳራ እና ባዶ የሚያሳውቁትን ለማስቀረት በእቅድ ላይ መሆኑን ተመልክቻለሁ። ይሄ ነገር ልዩ ትኩረት የሚሻ ይመስለኛል" ብሏል።
ሌላ ግብር ከፋይ ደግሞ "መውጫ መግቢያ አጣን፣ ዘግተህ ስጠፋ አሸባሪ ይሉሀል፣ እንዲሁም ሱቅህን ያሽጉታል። ከፍተህ ስትቀመጥ የገዛህበት ደረሰኝ ይሉሀል፣ ከሌለህ እቃህን ይወስዳሉ" በማለት ምሬቱን ገልጿል።
(#ከዜናዎቻችን በሳምንቱ በቪድዮ ዩትዩብ ላይ ያቀረብናቸውን የተመረጡ መረጃዎች ቆየት ብለን በድጋሜ በፅሁፍ የምናቀርብበት አምድ ነው)
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMrdia