#ከዜናዎቻችን| በአፋር እና ሲዳማ ክልሎች ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ለገዢው ፓርቲ በግድ ከደሞዝ አዋጡ ተባልን ብለው ተናገሩ
(መሠረት ሚድያ)- በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ለመሠረት ሚድያ እንደተናገሩት በጥቅምት ወር ለብልፅግና መዋጮ በሚል ከመምህራን ላይ የ20 ፐርሰንት የደሞዝ መዋጮ በግዴታ እንደተቆረጠ ተናግረዋል።
ከሌሎች የመንግስት ቢሮ ሰራተኞች ላይ ደሞ 50 ፐርሰንት ተቆረጠ ሲሆን መዋጮው በህዳር ወርም ይቀጥላል ተብሏል።
"ተስፋ ቆርጠናል፣ አዲሱን የደሞዝ ጭማሪ ስንጠብቅ ጭራሽ ደሞዛችንን መቁረጥ ተጀምሯል" ያሉት ሰራተኞች የመምህራን የደረጃ እድገት እርከን እንኳን በክልሉ ከቆመ 2 አመት እንደሞላው ጨምረው ገልፀዋል።
በሌላ በኩል በሲዳማ ክልል ደራራ ወረዳ ለብልፅግና ፓርቲ የህንፃ ግንባታ ተብሎ የፓርቲ አባል ያልሆኑትን ጭምር የአንድ ወር ደሞዝ እንዲቆረጥ መወሰኑ ለመሠረት ሚድያ የደረሰው ጥቆማ ያሳያል።
"ደሞዛችን እንዲቆረጥ አንፈርምም" ያሉ መምህራን ደሞዛቸው ጭራሽ እንዳልተከፈላቸው ገልፀው ችግር ላይ እንዳሉ ጠቁመዋል።
በ2017 ዓ.ም የወረዳው የብልፅና ፅ/ቤት በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን በማስተባበር የወረዳውን የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ህንፃ ለመስራት ገንዘብ እየሰበሰበ እንደሚገኝ ባደረግነው ዳሰሳ አረጋግጠናል።
"እስካሁን የአብዛኛው የወረዳው መምህራን ደሞዝ በግዳጅ እንዲፈርሙ ተደርጎ ደሞዛቸው ተቆርጦ ተከፍሏል። እኛ አንፈርምም ያልን ሁለት መቶ የምንጠጋ መምህራን ግን በግድ ካልፈረማችሁ ተብለን እስከ ዛሬ ድረስ ደሞዛችን ተይዟል" ያሉ ሲሆን የታሰሩም ሰዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።
ጉዳዩን ከወረዳ እስከ ክልል ማህበር ብናመለክትም እስከዛሬ ድረስ ሊከፈለን አልቻለም በማለት ለሚድያችን ተናግረዋል።
መረጃን ከመሠረት!