በአዲስ አበባ የሚሰማው ተኩስ ምንድን ነው?
- በተኩሱ አንድ ሴት መገናኛ አካባቢ ተመትታ ህይወቷ አልፏል
(መሠረት ሚድያ)- ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ እንደ ገርጂ፣ ጃክሮድ፣ ሾላ፣ 6 ኪሎ፣ መነን፣ ጎሮ ወዘተ ያሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ድምፅ ያለው ተኩስ ሲሰማ ነበር።
በርካታ ነዋሪዎች በድምፁ ተደናግጠዋል፣ መረጃ የሰጠ የመንግስት አካልም የለም።
መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ ባደረገው ማጣራት ተኩሱ ከሰሞኑ ከመንግስት ጋር እርቅ ፈፀሙ በተባሉት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት የተተኮሰ ነው።
መገናኛ አካባቢ አንዲት ሴት በተኩሱ ምክንያት በጥይት ተመትታ ህይወቷ ማለፉም ታውቋል።
ታጣቂዎቹ የኦነግን ባንዲራ በመያዝ ከሸገር ከተማ በመነሳት ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ወደ ሰማይ እየተኮሱ እንደገቡ የደረሰን መረጃ ያሳያል።
"ታጣቂዎቹ በቅጥቅጥ አና በሃይሉክስ መኪና ተጭነው ሾላ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ሲደርሱ ወደ ሰማይ ተኩስ አየተኮሱ እየተጓዙ ነበር" ያለን አንድ የአይን ምስክር በሁኔታው በርካቶች እንደተደናገጡ ገልጿል።
ህዝብ በሚንቀሳቀስበት ጎዳና ላይ ድርጊቱ መፈፀሙ እንዳሳዘናቸው የገለፁት ነዋሪዎች ህዝብን በዚህ ሁኔታ፣ በተለይ ቀድሞ ባልተገለፀበት ሁኔታ ማሸበር አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
መሠረት ሚድያ ሾላ ፖሊሲ ጣቢያ ከሚገኙ አንድ የፖሊስ አባል ድርጊቱን ያረጋገጠ ሲሆን አንዳንዶች ከተኮሱ ቦታ በድንጋጤ ሲሸሹ ይታይ እንደነበር ገልፀዋል።
ፎቶ: ፋይል
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia