"ኢትዮጵያ እና ሱማልያ ሁለቱንም በሚያግባባ መልኩ ስምምነት ላይ ደርሰዋል"--- የተርኪዪ መሪ ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን
(መሠረት ሚድያ)- የሶማልያ እና የኢትዮጵያ መሪዎችን በተርኪዪ እያስተናገዱ የሚገኙት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ኢትዮጵያ እና ሱማልያ ሀለቱንም ሀገራት በሚያግባባ መልኩ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ብለው ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርገዋል።
ኤርዶጋን ሁለቱ ሀገራት በጋራ ይፋ የሚያደርጉት የስምምነት ዶክመንት እንደተዘጋጀ ጠቅሰው ዶክመንቱ ሀገራቱ የበፊቱን ሳይሆን መጪውን ግዜ እንዴት በጋራ አብረው ተከባብረው እና በመልካም ጉርብትና እንደሚወጡት የሚያሳይ ነው ብለዋል፣ ለዚህም ሁለቱን ሀገራት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ በምሽቱ ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ከህልውናዋ ጋር የተያያዘ መሆኑን አንስተው የዛሬው ውይይት ወደ ጓደኝነት መልሶናል ብለዋል።
የሶማልያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በበኩላቸው ዛሬ ምሽት የተደረገው ውይይት በቅርብ ግዜ በሀገራቸው እና ኢትዮጵያ መሀል የነበረውን አለመግባባት ያስቆመ ነው ብለዋል። ሱማልያ የኢትዮጵያ "እውነተኛ ጓደኛ" ሆና ትቀጥላለችም ብለዋል። የኢትዮጵያ ጦር በሶማልያ ለአመታት የከፈለውን መስዋዕትነትም ፕሬዝደንቱ አንስተዋል።
የዛሬ አመት ገደማ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መሀል የባህር በር አጠቃቀምን በተመለከተ የመግባብያ ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው የሚገኙት ኢትዮጵያ እና ሶማልያ ከስምንት ወር በፊት ጀምሮ በተርኪዪ አመቻችነት ንግግር ቢጀምሩም ውጤት ሳያመጣ ቆይቷል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia