#Opinion በአቶ ሙሼ ሰሙ የተፃፈ
"የገንዘብ ፓሊሲ ኮሚቴ" ትናንት ያወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ተስፋ ሰጭነትን ተላብሶ ቀርቧል። ነገር ግን "ከግሽበት ምጣኔውና ቀድመው ከተሰሉ መስፈርቶች ውጭ" አብዛኛዎቹ መሰረታዊ የኢኮኖሚ መለኪያዎች በቁጥር ወይም በመቶኛ ስሌት ተደገፈው ስላልቀረቡ በቅጡ ላጤናቸው ብዙ ጥያቄዎችን ያጭራሉ።
ምዘናቸው የቀረበበትም መንገድ ፦ ይገመታል፣ ይጠቁማል፣ ይጠበቃል፣ ታይቷል፣ ጨምሯል፣ አሳይቷል፣ እያሳየ ነው፣ ይደግፋል፣ ከፍ ይላል... ወዘተ በሚሉ ምናባዊ ስሌቶች ላይ ተመርኩዞ ሰለሆነ ለንጽጽር አይበቁም።
አሁንም ፈተናዎች አፍጥጠው ለያዥ ለገናዥ ከማስቸገራቸው በፊት ግልጽነት ቢኖር መፍትሔውን እንደ ሕዝብ በጋራ መሻት ይቻላል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ሕዝብ ኃያል ነው። መፍትሔውን ከሕዝብ ጋር ለመሻት ደግሞ ግልጽነት፣ ግልጽነት፣ አሁንም ግልጽነት ያስፈልጋል።
ለማንኛውም ከግሽበቱ ውጭ ዝርዝር የጋዜጣዊ መግለጫው ሐተታ ይዘት ሲጠቃለል ይህንን ይመስላል።
-በዘንድሮው የሰብል ዘመን ከፍ ያለ ምርት እንደሚመዘገብ ሁኔታዎች ያመላክታሉ። (በኩንታል፣ በቶን ስንት ነው)
-የተመዘገበው የመብራት ሐይል ምርት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍ ያለ ዓመታዊ የምርት እድገት እንደሚኖር ይጠቁማል። (የመብራት ሐይሉ አቅርቦቱም ሆነ የእንዱስትሪ እድገቱ ስንት ነው)
-የአየር ትራንስፓርትና የቱሪስቶች ፍሰት የአገልግሎት ዘርፉን እድገት እንደሚደግፍ ይጠበቃል። (እንዴት ይደግፋል፣ በቁጥር ስንት ነው)
-በ2017 የተጠናከረ ዕድገት እንደሚኖር ይጠበቃል (የተጠናከረ ዕድገት ስንት ነው።)
-የውጭ ንግድ ዘርፍ ትልቅ መሻሻል እያሳየ ነው። (የተሻሻለው በስንት % ነው)
-የውጭ ንግድና ሐዋላ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል ። (ከፍተኛ እድገት በቁጥር ወይም በመቶኛ ስንት ነው)
-የገቢ ንግድ ግን መጠነኛ ቅናሽ ታይቶበታል። (ቅናሹ በመቶኛ ወይም በቁጥር ስንት ነው)
-ከግልና ከመንግስታዊ ምንጮች ወደ ሀገር ውስጥ የፈሰሰው የካፒታል መጠን ጨምሯል። ( የጨመረው በስንት መቶኛ ነው)
-የከረንት አካውንት ትርፍ ተመዝግቧል። (ትርፉ በቁጥር፣ በመቶኛ ስንት ነበር )
-የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በከፍተኛ ደረጃ አድጓል። ( ከፍተኛ ደረጃ ስንት ነው።)
-የበጀት አንቅስቃሴዎች ጥሩ አዝማሚያ አሳይተዋል። (ጥሩ አዝማሚያ ማለት በቁጥር በመቶኛ ስንት ነው)
- ከአጠቃላይ የሀገራዊ ምርት አኳያ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር ቅናሽ ታይቷል። (ቅናሹ በቁጥር ወይም በመቶኛ ስንት ነው)
@MeseretMedia