ዋልታ ከፋና ጋር ከተዋሀደ በኋላ በርካታ የስራ ቅጥሮች በትውውቅ እየተፈፀሙ እንደሚገኙ ሰራተኞች ተናገሩ
(መሠረት ሚድያ)- ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በቅርቡ ከዋልታ ሚድያ እና ኮሙኒኬሽን ማዕከል ጋር ውህደት መፈፀሙን ተከትሎ በርካታ ህገወጥ የሆኑ የትውውቅ የስራ ቅጥሮች እንደተፈፀሙ ሰራተኞች ተናግረዋል።
እነዚህ ሰራተኞች ለመሠረት ሚድያ በሰጡት ጥቆማ ፋና ውህደቱን ተከትሎ አብዛኛውን ነባር፣ ጠንካራ እና ታታሪ የሚባሉ ሰራተኞቹን ያገለለ የደረጃ ሹመት ሰጥቷል ብለዋል።
"በሹመቱ 95 ፐርሰንት የሚሆነውን ቦታ ያገኙት የቀድሞዋ የፋና ብሮድካስቲንግ ባልደረባ፣ የአሁኗ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ የቅርብ ወዳጆች ናቸው" የሚሉት ሰራተኞቹ ከዳይሬክተር እስከ ስራ አስፈጻሚነት ደረጃ እንዲሾሙ የተደረጉት በዚህ መልኩ መሆኑን አስረድተዋል።
ቀደም ሲል ለሀገርና ለተቋሙ በታታሪነት የሚሰሩ ሰዎች እንዲገፉ ምክንያት ሆኗል በተባለው አካሄድ ዙርያ አስተያየት የሰጡን አንድ የተቋሙ ሰራተኛ "እንደበቀል እንዳያድጉ እና እንዲገፉ የተደረጉ በርካቶች ናቸው" ብለዋል። በሌላ በኩል ካለምንም መስፈርት፣ ብቃትና ለዘርፉ ልምድ ሳይኖራቸው በስራ አስፈጻሚነት እና በዳይሬክተርነት እንዲሾሙ የተደረጉ በርካቶች እንዳሉ ከነማስረጃው ለሚድያችን ሰጥተዋል።
መሠረት ሚድያ የተመለከተው አንድ የተቋሙ የቅርብ የቅጥር አካሄድ ከዳይሬክተር በታች ያሉት ብቻ ለውድድር ክፍት ሆነው ሌላውን በሹመት መፈፀሙን ያመላክታሉ። በዋልታ ይሰሩ የነበሩ በርካታ አንጋፋ ባለሙያዎችም ከስራ እንደተገለሉ ወይም ዝቅ ብለው እንዲሰሩ እንደተደረጉ በተጨማሪ ታውቋል።
ሚድያውን በዚህ ዙርያ ለማነጋገር የሞከርን ቢሆንም ምላሽ አላገኘንም፣ ወደፊት ተጨማሪ ማብራርያ ካገኘን በዜናው ዙርያ እንመለስበታለን።
ከፋና በተጨማሪ በሌላኛው የመንግስት ሚድያ ኢቢሲ ውስጥ 400 ሰራተኞች በሀሰተኛ ወይም ፎርጅድ ዶክመንት ተቀጥረው መገኘታቸውን መሠረት ሚድያ በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል። ይህን የኢቢሲ ድርጊት ያጋለጠው የተቋሙ ሰራተኛ የሽብር ክስ ቀርቦበት ለእስር ተዳርጎ እንደነበር መረጃ አቅርበን ነበር።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia