መንግሥት ካርድ የተሰኘዉን የሰብአዊ መብት ድርጅትን ጨምሮ ሌላ አንድ ተቋምን ከስራቸዉ አገደ
የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን በሰብአዊ መብት ሥራዎች ታዋቂ የሆኑ ድርጅቶችን በደብዳቤ ማሸጉን ዋዜማ አረጋግጣለች። ከታገዱት ድርጅቶች መካከልም “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል” (በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃሉ “CARD” እና “ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ” (AHRE) ይገኙበታል።
ባለሥልጣኑ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አስታውቋቸዋል።
ዋዜማ የተመለከተችው ደብዳቤ ለእገዳው የሰጠው ምክንያት “ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራቱ ከባድ የህግ ጥሰት መፈጸሙን ማረጋገጥ ተችሏል” የሚል ነው። ዋዜማ የደረሳት መረጃ የታገዱት ድርጅቶች ቁጥር ከሁለት እንደሚበልጥ ቢጠቁምም፣ ለጊዜው ማረጋገጥ አልቻልንም።
ይህ እርምጃ መንግሥት በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በሚሠሩ ድርጅቶች ላይ ሲያደረግ የቆየው ጫና የመጨረሻ ከፍታ ነው ሲሉ ስለጉዳዩ በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። የእግድ እርምጃው በድርጅቶቹ መሪዎች አካባቢ የተጠበቀ እንዳልነበር ለመረዳት ችለናል።
የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን መያዶችን የማገድ ስልጣን ቢኖረውም “የአሁኑ እርምጃ በሕጉ የተዘረዘረውን ቅደም ተከተልና ቅድመ ሁኔታ የሚጥስ ነው” ብለዋል ሌላ የሕግ ባለሞያ። ድርጅቶቹ እግዱን በሕግ የመቃወም መብት ይኖራቸዋል። ለባለሥልጣኑ ቅርብ የሆኑ የዋዜማ ምንጮች እገዳው የተላለፈበት ሂደት ለእርሱም ግልጽ እንዳልሆነ ተናግረዋል።(Via-ዋዜማ)
@marakinews