ከ2017 አእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
✞ ማርያም ደስ ይበልሽ ✞
ማርያም❨፪❩ደስ ይበልሽ በገብርኤል ሰላምታ በአንቺ ስላደረ የዓለም ሁሉ ጌታ❨፪×❩
የአምላክ ቸርነቱ ፈቃዱ ሲሆን
ጨለማው ተገፎ ሲወጣ ብርሃን
መድኃኒት ሲመጣ ሰይጣን እንዳፈረ
የዜናው አብሳሪ ገብርኤል ነበረ
/አዝ = = = = =
ድንግል ተቀምጣ በቤተመቅደስ
ሃር ወርቁን አስማምታ ስትፈትል ንግስት
ገብርኤል ገብርኤል ዜናዊ ሐዲስ
የአምላክን መወለድ ስጋ በመልበስ
/አዝ = = = = =
ገብርኤል ሲያበስራት ድንግል ስትሰማ
በእሷ ላይ አደረ የመለኮት ግርማ
እዉነተኛ መልአክ መሆኑን ስላየች
ይሁንልኝ ብላ ቃሉን ተቀበለች
/አዝ = = = = =
ድንግል ተቀምጣ በቤተመቅደስ
ሃር ወርቁን አስማምታ ስትፈትል ንግስት
ገብርኤል ገብርኤል ዜናዊ አዲስ
የአምላክን መወለድ ስጋ በመልበስ
👉ዘማሪ ፍቃዱ አማረ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═══✞╗
✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞═══●◉❖◉●═══✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ