በዚህ ዘመን ሰው ሆድ እንዲብሰው እንደማድረግ ቀላል ነገር የለም ። ሰዉ እንዳለ ስስ ሆኗል ። ቀኑ እንዲጨረብ ትንሽ ምክንያት ይበቃዋል ።
አጠገብህ ያለውን ስራ ፈት በብሄርህ ምክንያት ነው ስራ ያላገኘኸው ብትለው ሲብሰከሰክ ይውላል ።
አንዱ ጓደኛህ ሲደውልልህ "እየነዳሁ ነው መልሼ እደውልልሃለሁ" ብትለው ቀኑን ሙሉ ይቆዝማል ።
የሆነችን ልጅ "በጣም ወፍረሻል" ብትላት ለጊዜው የሆነ የሆነ ነገር ትልህና መስታወት ፊት ቆማ ትብሰለሰላች ።
እስኪ አንዱ ሲስቅ ጠብቀህ "ሳይኖርህ አትሳቅ" በለው ፤ ወዲያው ይከስማል።
እፊቱ እንግሊዘኛ ስታወራ የሚከፋው ሰውም አለ።
አፍቅሮ የተጎዳ ሰው "እህህህ" እንዲል የፌስቡክ ጨለምተኞች ከblack and white ፎቶ ጋር የሚለጥፉት አጭር ጽሑፍ ይበቃዋል ።
ናፋቂውን ምንም አትበለው ፤ ገና ደመና ሲያይ ውስጡ ይረበሻል ።
ለማልቀስ "ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ" የሚል ዘፈን ብቻ የሚበቃው አለ ።
ደህና ነሽ ? ስትላት እንባዋ ግጥም የሚል አለች ።
ህልምህ ምን ነበር ? ብለህ ብትጠይቀው የማይከፋው አለ ? ።
ፀሐይ ሲመታው ብቻ ኑሮ የሚመረው አለ ።
ሰዉ እንደ ድሮው ረጅም የታክሲ ሰልፍ የመጠበቅ አቅም የለውም ። መኪና የለኝም ወይም የራይድ የለኝም ብሎ ያዝናል ።
እና ይሄ በሆዱ እንባ ያጠራቀመ ህዝብን ማስለቀስ ምን ሞያ ይጠይቃል ?
ከባዱ ነገር ተስፋ መስጠት ነው ። ተስፋ ስጠው ስልህ ምክረው ማለቴ አይደለም ። ከምር ተስፋ ስጠው ። አስቀው ። አለሁ በለው ። ራሱን እንዲችል አድርገው ። ባዶ ሆዱን አትሰክሰው ። አብልተህም አትሰክሰው ። ዕድል ስጠው ። እመነው ። እቀፋት ። ተቃቀፉ ። ምናምን...
Via: Hab HD