የሰው ልጅ ሲከማች እንደማንኛውም መንጋ ማመዛዘኑን ስሜት ይወርሰዋል። ዘዴውን ሀይል ይገስሰዋል። ሰው በተናጠል ሲቀርብ ነው ሰው የሚሆነው። በጅምላ ከተጠራ እንደማንኛውም እንስሳ መንጋ ነው። ስልጣኔው ቦታው ላይ አይገኝም። ዛሬም ቢሆን ኢየሱስ ብዙሃኑ ፊት ከቀረበ እጣ ፈንታው አትለወጥም። ይገረፋል፣ይወገራል፣ የእሾህ አክሊል ይደፋል፣ ይሰቀላል፣ በህዝቦች እጅ ውስጥ ጊዜ ስልጣን የለውም። ያኔ የሆነው ሳይዘንፍ ዛሬ ይደረጋል።
📓 ቅበላ
🪄አለማየሁ ገላጋይ