️🌙ኢስላም የሰላም መንገድ🌙️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌
ወደ አላህ ከጠራና መልካምን ከሰራ

ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማነው?
አል–ፉሲለት ምዕ41:33
t.me/MuslimNegnEneSul
t.me/MuslimNegnEneSul
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ከኢብኑ አባስ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ፡ እንዲህ ይላሉ፦

﴿كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَجْوَدَ النَّاسِ بِالْخَيْرِ، وَكَانَ أَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي رَمَضَانَ حِينَ يَلْقَاهُ جِبْرِيلُ،﴾

“ነቢዩ (ﷺ) ከሰዎች መልካምን በመቸር አቻ አልነበራቸዉም። በተለይ በረመዳን ከጅብሪል ጋር ሲገናኙ ቸርነታቸው እጅግ ይጨምራል። ጅብሪል በየረመዳኑ እየመጣ ቁርአንን ይማማሩ ነበር።”

📚 ቡኻሪ (1902) ሙስሊም (2308) ዘግበውታል


إِن تُقْرِضُوا اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا يُضَاعِفْهُ لَكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ وَاللَّهُ شَكُورٌ حَلِيمٌ
17  التغابن
ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩ (ምንዳውን) ለናንተ ይደራርበዋል፤ ለናንተም ይምራል፤ አላህም አመስጋኝ ታጋሽ ነው፡፡

(ተጋቡን 17)


...................................ረመዳን 6/1446 ዓ᎐ሂ    
🔷የተባረከው ቀለብ  ሱሁር

       ዒርባድ ኢብኑ ሳሪያህ ረዲየላሁ ዐንሁ
የአላህ መልክተኛ ﷺ በረመዷን ወር ውስጥ  ስሑር ወቅት ላይ ፦
#ወደ_ተባረከው_ቀለብ_ኑ_ተሰባሰቡ_ብለው_ሰዎች_ሲጣሩ_ሰምቻለሁ_ብለዋል
               📚ነሳኢይ (2163)

ረሱል ﷺ  እንዲህ ብለዋል፦
#ስሑርን_ተጠቀሙ_እርሱ_በረከት_ያለበት_ምግብ_ነውና
          📚ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

ረሱል ﷺ  እንዲህ ብለዋል፦
﴿نِعْمَ سَحورُ المُؤمِنِ التَّمْرُ.﴾
#የአማኝ_ምርጡ_ስሁር_ቴምር_ነው
           📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 562

ረሱል ﷺ  እንዲህ ብለዋል፦
﴿تَسَحَّرُوا ولوْ بِجَرْعَةٍ مِنْ ماءٍ﴾
#ስሁርን_ተመገቡ_ውሃ_በመጎንጨትም_ቢሆን
           📚 ሰሂህ አልጃሚ: 2945

ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
﴿فَصْلُ ما بيْنَ صِيامِنا وَصِيامِ أَهْلِ الكِتابِ، أَكْلَةُ السَّحَرِ.﴾

#በእኛ_ጾምና_በአህለል_ኪታቦች_ጾም_መካከል_ያለው_ልዩነት_ሱሑር_መመገብ_ነው
     📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1096
🌙  🌙  🌙  🌙  🌙  🌙  🌙  🌙


............................... ረመዳን 5/1446 ዓ᎐ሂ
#ሡሑር

#በአላህ_ስም_እጅግ_በጣም_ሩኅሩህ_እጅግ_በጣም_አዛኝ_በሆነው

59፥7 → መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና።
وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ
🌙🌙🌙  🌙🌙🌙  🌙🌙🌙  🌙🌙🌙

“ሡሑር” سُّحُور ወይም “ሠሑር” سَّحُور ማለት ቋንቋዊ ፍቺው “ሠሐር” سَحَر ማለት ነው።

“ሠሐር” سَحَر ማለት “የሌሊት መጨረሻ” ማለት ነው።

“ሠሐር” سَحَر የሌሊት መጨረሻ በሚል ቃል ሦስት ጊዜ ቁርኣን ውስጥ መጥቷል፦
3፥17 → ታጋሾች እውነተኞችም ታዛዦችም ለጋሶችና *”በሌሊት መጨረሻዎች”* ምሕረትን ለማኞች ናቸው፡፡
الصَّابِرِينَ وَالصَّادِقِينَ وَالْقَانِتِينَ وَالْمُنفِقِينَ وَالْمُسْتَغْفِرِينَ بِالْأَسْحَارِ

51፥18 →*”በሌሊቱ መጨረሻዎችም”* እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡
وَبِالْأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ

54፥34 →እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱንስ *”በሌሊት መጨረሻ”* ላይ አዳንናቸው፡፡
إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبًا إِلَّا آلَ لُوطٍ ۖ نَّجَّيْنَاهُم بِسَحَرٍ

“ሡሑር” سُّحُور ማለት ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ በሌሊት መጨረሻዎች ከፈጅር አዛን በፊት ለጾም መያዢያ የሚበላ ምግብ ነው።

#ይህንን_የሌሊት_ምግብ_መብላት_የዚህችን_ኡማ_የጾም_ሥርዓት_ካለፉት_አህሉል_ኪታብ_የሚለይበት_ሥርዓት_ነው፦
        ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 22 , ሐዲስ 77
ዐምር ኢብኑል ዐስ እንደተረከው፦
”የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ”በእኛ ጾም እና በአህሉል ኪታብ ጾም መካከል ያለው ልዩነት ሡሑር ነው”።
عَنْ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ فَصْلَ مَا بَيْنَ صِيَامِنَا وَصِيَامِ أَهْلِ الْكِتَابِ أَكْلَةُ السُّحُورِ ‏

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ሡሑርን መመገብ የሚኖረው ትሩፋት ረድኤታዊ በረከት ነው፦
    ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 32
አነሥ ኢብኑ ማሊክ ሰምቶ እንዳስተላለፈው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ሡሑርን ብሉ! በሠሑር ውስጥ በረከት አለና”*።
قَالَ سَمِعْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ تَسَحَّرُوا فَإِنَّ فِي السَّحُورِ بَرَكَةً

“ተሠሐሩ” تَسَحَّرُوا የሚለው የግስ መደብ “ሠሑር” سَّحُور ከሚለው የስም መደብ የረባ ቃል ነው።
#አምላካችን_አላህ፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” ስላለን ሡሑርን መብላት ከነቢያችን”ﷺ” ያገኘነው ሱናህ ነው፦

59፥7 →መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና።
وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ነቢያችን”ﷺ” የአላህ ነብይ ስለሆኑ በዐቂዳህ እና በፊቅህ ጉዳይ ላይ የሚናገሩት ሁሉ ወሕይ ነው። ኢሥላም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይሆን ዐቂደቱል ረባንያ ነው።

ይህንን በቅጡ የማያውቁ ሰዎች፦ “የሙሥሊም ጾም ማለት ሌሊቱ ወደ መዓልት ተቀይሮ ሌሊቱ በሙሉ ሲበላ ይታደርና በመዓልት የሚተኛበት” ይመስለዋል። ይህ የተሳሳተ መረዳት ነው። ሙሥሊም መግሪብ አዛን ሲል ያፈጥራል እስከ ዒሻህ ሊበላ ይችላል። በዚህ ጊዜም ጾመኛ ማስፈጠር፣ ሰደቃ፣ ዳዕዋህ በማድረግ መሽጉል ነው። ዒሻህ ከተቆመ በኃላ ተራዊሕ ሶላት ይቀጥላል፥ ከዚያ ሶላቱል ለይል አለ። ይህ ሁሉ ዘርፈ-ብዙ እና መጠነ-ሰፊ አምልኮ ለምሳሌ ዚክር፣ ዱዓ፣ ቂርኣት፣ የሱናህ ሶላት ወዘተ.. ከተካሄደ በኃላ የፈጅር ሶላት አዛን ከማለቱ በፊት በሡሑር ይያዛል። ይህንን ካላወክ ቀረብ ብለክ አንድ ቀን ማየት ነው። በተለይ አውሮፓ አካባቢማ ጾሙ በጋ ላይ ከዋሉ ጾሙ 19-21 ሰአት ያክል ይጾማል። ከ 3-5 ሰአት ምግብ በማፍጠር የተበላው ቁጭ ብሎ ሡሑር የሚቀመሰው ለሱናው ያክል በወፍ በረር ነው። ይህንን የመለኮት ሕግና ሥርዓት የያዘው ጾም የምትተቹ አላህ ሂዳያህ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

✍ከወንድም ወሒድ ዑመር




⭐️⭐️⭐️⭐️ حديث اليوم ⭐️⭐️⭐️⭐️


....................................ረመዳን 4/1446 ዓ᎐ሂ  
 ከተበረው የአላህ ቃል ቁርዓን
          ደረጃዎች ውስጥ፦


1⃣ ለማዳመጥ
قال تعالى
     🌹وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
🌹
#ቁርዓንም_በተነበበ_ጊዜ_እርሱን_አዳምጡ_ጸጥም_በሉ_ይታዘንላችኋልና

2⃣ ለማንበብ
قال تعالى
  🌹الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ يَتْلُونَهُ حَقَّ تِلَاوَتِهِ
🌹
#እነዚያ_መጽሐፉን_የሰጠናቸው_ተገቢ_ንባቡን_ያነቡታል


3⃣ ለሂፍዝ
قال تعالى
     🌹بَلْ هُوَ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ فِي صُدُورِ الَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ ۚ
🌹

#ይልቁንም_እርሱ_ቁርዓን_በእነዚያ_ዕውቀትን_በተሰጡት_ሰዎች_ልቦች_ውስጥ_የጠለቀ_ግልጾች_አንቀጾች_ነው

4⃣ ማሰተንተን
قال تعالى
     🌹كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ
🌹
#ይህ_ወዳንተ_ያወረድነው_ብሩክ_መጽሐፍ_ነው #አንቀጾቹን_እንዲያስተነትኑና_የአእምሮዎ_ባለቤቶችም_እንዲገሰጹ_አወረድነው

5⃣ ብሰራት
قال تعالى
    🌹الَّذِينَ يَسْتَمِعُونَ الْقَوْلَ فَيَتَّبِعُونَ أَحْسَنَهُ ۚ
🌹
#እነዚያን_ንግግርን_የሚያዳምጡትንና_መልካሙን_የሚከተሉትን_አብስር

          🌹 اللهم إجعلنا من أهل القرآن🤲


🍂ዕረፍት

☞ስንቅ የፈለገ አላህን መፍራት ይበቃዋል።

◾️ልዕልና የፈለገ እስልምና ይበቃዋል።

☞ፍትህን የፈለገ የአላህ ፍርድ ይበቃዋል።

◾️አጫዋች የፈለገ አላህን ማስታወስ ይበቃዋል።

☞መካሪን የፈለገ ሞት ይበቃዋል።

◾️ሐብትን የፈለገ መተናነስ ይበቃዋል።

☞ጌጥን የፈለገ እውቀት ይበቃዋል።

◾️ቁንጅናን የፈለገ ጥሩ ፀባይ ይበቃዋል።

☞ዕረፍትን የፈለገ አኺራ ይበቃዋል።
"ይህ ሁሉ ያልበቃው እሳት ይበቃዋል"




#አላህ የፆምን ታላቅነት ለማሳየት ከሁሉም ዒባዳዎች ለይቶታል። #የአላህ_መልእክተኛ በዘገቡት በሀዲስ አልቁድስ እንዲህ ይላል፦
عن رسول الله صلى الله عليه وآله وسلم أنه أخبر عن الله عزَّ وجلَّ قوله: «كُلُّ عَمَلِ ابْنِ آدَمَ لَهُ إِلَّا الصَّوْمَ، فَإِنَّهُ لِي وَأَنَا أَجْزِي بِهِ»

[ ሁሉም የአደም ልጅ ስራው ለራሱ ነው ፆም ሲቀር ፤ ፆም ለኔ ነው እኔም እመነዳዋለሁ። ]
ቡኻሪና ሙስሊም


ሁሉም ዒባዳዎች ለአላህ ሁነው ሳለ የሚመነዳቸው እሱ ሁኖ ለምን ፆምን ለየው ?
ኡለሞች ይህንን ስያብራሩ ሌሎች ዒባዳዎች የሚያታዩ ናቸው (ሶላት፣ ዘካ ሲሰጥ፣ ሀጁ ኡምራው)። ለአላህ ብሎም ለሰው ብሎም ሊሰራቸው ይችላል ፆም ግን የተለየ ነው አንድ ሙእሚን ሲፆም በእሱና በአላህ መካከል ነው። ከሰዎች ተደብቆ መብላትና መጠጣት ይችላል ነገርግን አላህ ያየኛል በሚል ሙሉ ቀን ከምግብና መጠጥ ታቅቦ ይውላል ለዚህም አላህ እኔ ነኝ የምመነዳው አለ። ለብቻውም ረያን የሚባል የጀነት በር አደረገላቸው በዚህም በር ከፆመኛ ውጭ አይገባም።


....................................ረመዳን 3/1446 ዓ᎐ሂ
                        ዱዓ አብዙ!!
🔹🔹🔷 የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
﴿ثلاثةٌ لا تُردُّ دعوتُهم: الصائمُ حتى يُفطرَ، والإمامُ العادلُ، ودعوةُ المظلومِ﴾

“ሶስት አይነት ሰዎች ዱዓቸው አይመለስም (ተቀባይነት አለው) ፆመኛ እስኪያፈጥር ድረስ፣ ፍትሃዊ መሪ እና የተበደለ ሰው ዱዓ (ፀሎት) ናቸው።”

           📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ 4/407
      🌟  🌟  🌟  🌟  🌟  🌟  🌟  🌟
አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
    አንድ ባርያ አላህ ዘንድ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ሱጅድ ላይ በሆነ ጊዜ ነው። ስለዚህ ዱአ አብዙ።
           📚 ሙስሊም ዘግበውታል
      🌟  🌟  🌟  🌟  🌟  🌟  🌟  🌟
https://t.me/MuslimNegnEneSul
    https://t.me/MuslimNegnEneSul


.......... ረመዷን ገባ ማለት የጀነት በር ተከፈተ ማለት ነው።
ከኛ የሚጠበቀው ጀነት የሚጠበቀው ጀነት የሚያስገቡ የአምልኮ ተግባራትና መልካም ሥራዎች ላይ የሙጥኝ ማለት ነው።
ጀነትን እያሰቡ መፆም ።

አላህ ከጀነት ሰዎች ያድርገን።


.....................................ረመዳን 2/1446 ዓ᎐ሂ
    ጾመኛን የተመለከቱ ጠቃሚ ነጥቦች
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
1. ገላን የመታጠብ ግዴታ ሳይፈፅሙ (ጀናባን ሳይታጠቡ) ለጾም ኒያ ማድረግ እና ጎህ ከቀደደ በኋላ ገላን መታጠብ ለጾመኛ ሰው ይፈቀዳል፡፡

2. ሴት ረመዳን ውስጥ ከጎህ መቅደድ (ከፈጅር) በፊት ከወር አበባም ሆነ ከወሊድ ደም ከጠራች ገላዋን ከነጋ በኋላ የምትታጠብ ቢሆን እንኳ ጾሙን መጾም ግዴታ ይሆንባታል፡፡

3. ጾመኛ ሰው ጥርሱን መነቀል ቁስሉን ማከም በአይኖቹ እና በጆሮዎቹ መድሀኒት መጨመር ይፈቀድለታል፡፡ የመድሀኒቱ ስሜት አፉ ውስጥ ቢሰማው እንኳ ይህን ማድረግ ይፈቀድለታል ባይሆን ወደ ሆድ እንዳይገባ መጠንቀቅ አለበት።

4. ጾመኛ ሰው ጠዋትም ሆነ ማታ ጥርሱን መፋቅ ይፈቀድለታል፡፡ ሲዋክ ለጾመኛ ሰውም ልክ እንደሌላው ሰው ሁሉ ሱንና ነውና፡፡

5. ጾመኛ ሰው ሙቀት እና የውሀ ጥሙን ሊያቃልሉለት የሚችሉ እንደ ቀዝቃዛ ሻወር እና ኮንዲሽነር ያሉ ነገሮችን መጠቀም ይፈቀድለታል፡፡

6. በደም ግፊት ምክንያትም ሆነ በሌላ ምክንያት የሚደርስበትን የትንፋሽ ማጠር ለመቋቋም በአፉ በኩል አየር መንፋት ይፈቀዳል፡፡

7. ጾመኛ ሰው ከንፈሮቹ ሲደርቁ በውሀ ሊያርሳቸው እንዲሁም አፉ ሲደርቅም አልፎ እንዳይገባ በመጠንቀቅ አፉን በውሀ መጉመጥመጥ ይፈቀድለታል፡፡

8. ስሁርን ማዘግየት ፍጡርን ማፋጠን ሱንና ሲሆን ሲያፈጥር በቴምር እሸት ወይም በተገኘው የቴምር አይነት ጾምን መፈሰክ ሱንና ነው፡፡ ካላገኘ ግን በውሀ ያፈጥራል፡፡ ውሀም ካላገኘ በተገኘው ማንኛውም ምግብ ማፍጠር ነው፡፡ ምንም ነገር ከጠፋ ግን እስኪያገኝ ድረስ ጾሙን ለማፍጠር በልቡ ኒያ ያደርጋል፡፡

9. ጾመኛ ሰው የአላህን እና የነብዩን ትዕዛዛት በቅንነት በመፈፀም ትርፍ ሱና ስራዎችን ማብዛት እና ከተከለከሉ ነገሮች መራቅም ሱንና ነው፡፡

10. ጾመኛ ሰው ሀይማኖታዊ ግዴታዎችን በትጋት በመፈጸም እና ሀራም ከሆኑ ነገሮች ሁሉ በመራቅ አምስቱን እለታዊ የግዴታ ሰላቶች ጊዜያቸውን ጠብቆ በህብረት (በጀመዓ) መስገድ ይጠበቅበታል፡፡
  ሀሰት መናገር ፣ ሀሜት ፣ ማጭበርበር እና አራጣዊ ግብይቶችን እንደዚሁም ማንኛውም ሀራም የሆነ ንግግር እና ተግባር መተው ግዴታ ነው፡፡ #ነብያችን (ﷺ) ይህንኑ በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፡- «አንድ ሰው ሀሰት መናገርን እና በርሱ መሰረት ክፉ መስራትን እንደዚሁም ግብዝነትን ካልተወ በስተቀር ምግብ እና መጠጡን (በጾም) በመተው አላህ ጉዳይ የለውም»፡

ምንጭ፦የሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሳሊህ አል-ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ስራዎችን መሰረት ያደረገ
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
https://t.me/MuslimNegnEneSul
https://t.me/MuslimNegnEneSul
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★




............................ረመዷን 1/1446 ዓ᎐ሂ
•°•°•°•°• ★ ፆምና ጥበባቱ ★•°•°•°•°•°

    ኢስላም አንድን ነገር ለጥበብ ቢሆን እንጂ አይደነግግም፡፡ አንዳንዱ ቢረዳውና ሌላው ባይረዳውም፡፡ አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ የድንጋጌው ጥበባት ድንቅ ነው፡፡
   በአፈጣጠሩም በትእዛዛቱም ጥበበኛ ነው፡፡ ምንም ነገር ለከንቱ አልፈጠረም፤ ምንም ነገር ለቀልድ አላዘዘም፡፡

#አላህ_ሱብሃነሁ_ወተዓላ_ከዓለማት_የተብቃቃ_ነው_ፍጡራኑና_ባሪያዎቹ_ግን_ወደርሱ_ከጃዮች_ናቸው

ባሪያዎች የሚፈፅሙት ወንጀል እንደማይጎዳው ሁሉ ትእዛዛቱ ስለተፈፀሙለትም ጥቅምን አያገኝም፡፡ 
                    ምክንያቱም
#የአላህን_ትእዛዛት_የመፈፀም_ጥቅም_ወደታዛዦች_ተመላሽ_ነውና፡፡

💎የሀይማኖቱ ድንጋጌ ሰነዶች ባመለከቱት መሰረት ፆም ብዙ ጥበባትና ጥቅሞች አሉት፡፡ ከነሱም ውስጥ፡-

🔵 የአላህን ትእዛዛት በመፈፀም ራስን ማጥራት፤  ከእቀባዎቹ ራስን በመግታት ሙሉ ታዛዥነት ላይ ነፍስን ማለማመድ፤ ነፍስን ከስሜቷ በማገት ዙሪያዋን ከተበተቧት ማነቆዎች ነፃ ማውጣት ነው፡፡
   ሰውዬው የአላህን ውዴታ ከጃይ ባይሆንማ (በረመዳን ቀን ክፍለ ጊዜ) ከፈለገ ይበላል ፣ ይጠጣል ከባለቤቱም ጋር ግንኙነት የፈፅማል፡፡ ይህን ሁሉ ቢያደርግ ከአላህ በስተቀር ማንም አያውቅበትም፡፡
   ይህን አስመልክቶ አቡሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦
“ነፍሴ በጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ የፆመኛ ሰው የአፍ ጠረን አላህ ዘነድ ከሚስክ ሽቶ በላይ ጣፋጭ ነው። ምግብ መጠጥና ስሜቱን ለእኔ ብሎ ነው የተወው። የአደም ልጅ ስራ በሙሉ ለራሱ ነው። ፆም ሲቀር እርሱ ለእኔ ነው። እርሱን እኔ ነኝ የምመነዳው።”
               (ቡኻሪና ሙስሊም) 

🔵  ዶክተሮችና የጤና ባለሙያዎች እንዳረጋገጡት ፆም የሰውነትን ጤና ለመጠበቅ ይጠቅማል፡፡
  ከዚህም ባሻገር የሰው ልጅን መንፈሳዊ ማንነቱ በቁሳዊ ክጃሎቱ ላይ ድልን ይጎናጸፍ ዘንድ ያግዘዋል።
የሰው ልጅ  ወደ ጥሩም ወደ መጥፎም የማዘንበል ተፈጥሯዊ አቅም ተሰጥቶታል።
    ብሎም የአፈጣጠሩ መዋቅር የተቦካ ጭቃ እንዲሁም ከአላህ የሆነ መለኮታዊ እስትንፋስ (ሩህ) ውህድ ነው፡፡
አንዱ ለውርደቱ ምክንያት ሲሆን
ሌላኛው ደግሞ ማዕረጉን ይጨምርለታል።    
   ጭቃዊ አፈጣጠሩ በማንነቱ ላይ የበላይ ከሆነ ውርደትን ከመላበስ በተጨማሪ ወደ እንስሳ ደረጃ ያዘቅጠዋል፤ አልያም መንገዱን የሳተ ያደርገዋል።
#ግና_መንፈሳዊ_ማንነቱ_የበላይ_ከሆነ_ወደ_መላእክት_አድማስ_ከፍ_ይላል_ልዕልናንም_ይጎናፀፋል፡፡

ስለዚህ በፆም ወቅት መንፈሳዊ ማንነት ቁስን፤ ህሊና ስሜትን ያሸንፋሉ፡፡
   ጿሚ የሆነ ሰው በየቀኑ እስኪያፈጥር ድረስ የሚያጣጥመው ደስታ ሚስጥሩ ይህ ነው። በሃዲስ እንዲህ ተብሏል፦
“ለፆመኛ ሁለት ደስታዎች አሉት፡፡
① ሲያፈጥር በማፍጠሩ ይደሰታል።
② ከጌታው ጋር ሲገናኝም በጾሙ ይደሰታል፡፡”
 
              (ቡኻሪና ሙስሊም) 

🔵 ፆም ፍላጎትን የመግሪያ፣ ነፍስን (ከመጥፎ ጎዳና) ታግሎ የመጣያ፣ ብሎም ትዕግስትን መለማመጃ የሆነ ታላቅ የንቅናቄ አውድማ ነው።
    የሰው ልጅ በፍላጎት የተከበበ አይደለምን?
መልካም ነገርስ በፍላጎት እንጂ ይገኛልን?

(ዲን) እምነትስ ታዛዥ በመሆን ላይ መጽናትና ከወንጀል መራቅ ላይ ብርቱ መሆን አይደለምን? በዚም ጾም በራሱ ሁለት የትዕግስት ምህዳሮችን ያመላክተናል።

☆አንደኛ: የአላህ መልእክተኛ ሰለለሁ ዓለይሂ ወሰለም የረመዳንን ወር የትዕግስት ወር ብለው ሲጠሩት እንዲሁ አልነበረም።
   በሀዲስ ከኢብን ዐባስ እና አሊይ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተጠቀሰው 
“የትዕግስት ወር (የሆነውን ረመዳን) መጾም፤ እንዲሁም ከእያንዳንዱ ወር ሶስት ቀን መጾም የደረትን ዝገት ያስወግዳሉ።”
     በዚህ ሀዲስ የደረት ዝገት  ሲባል የነፍስን ውስወሳና አባይነት ነው
    እንዲሁም ተንኮልንና ንዴት(ብስጭት) ነውም ተብሏል

☆ሁለትኛ: የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንደገለጹት “ጾም ጋሻ ነው”።
   ይህንንም በተለያዩ ዘገባዎች ብዛት ባላቸው ሰሃቦች ተነግረው በሀዲስ እናገኛቸዋለን።
   ለአብነት ያህል ከአቡ ሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና  የተዘገበው ሀዲስ “ጾም በዚህች ዓለም ከወንጀል መጠበቂያ፤ በመጨረሻይቱ ቀንም ከእሳት መዳኛ ነው።”
 በሌላም ሀዲስ 
  “አንዳቹ በጦርነት እንደሚከላከልበት ጋሻ ጾምም ከእሳት መከላከያ (ጋሻ) ነው።”
      (አህመድና ነሳኢ) እንዲሁም አቢ ኡማማ በጠቀሱት ሌላ ሀዲስ ደግሞ
   “ጾም ጋሻ ነው። እሱም ከሙእሚን ምሽጎች ውስጥ አንዱ ነው።” (ጦበራኒ)
•°•°•°•°•°•°•° ★__★ •°•°•°•°•°•°•°
https://t.me/MuslimNegnEneSul
https://t.me/MuslimNegnEneSul
•°•°•°•°•°•°•° ★__★ •°•°•°•°•°•°•°




Forward from: Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል
🛑 ተራዊህ በመስገድ ከሚገኙ ጥቅሞች

📌 ቀኑን በጾም ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች እንመደባለን

📌 ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኛለን

📌ተራዊሕ ብዙ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን

📌ከወንጀል ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን

📌ዒባዳ ላይ ትዕግስትን እንማራለን

📌ሰላተል-ለይል እንለማመዳለን

📌በተደጋጋሚ ከኢማሙና ማእሙሞች ጋር "አሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል

📌 መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል

📌 ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል

📌 የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን

📌 ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል

📌 ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅ ለወጣቱ መልካም አርዓያ እንሆናለን

📌 ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እናይበታለን

📌 ቁርኣንን በብዛት በመስማት የአላህን እዝነት እናገኛለን እንዲሁም ብዙ በመስማት ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራርም እንማራለን

📌 በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "አሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን

📌 ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እንሸምታለን

📌 የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፥ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውም

📌 ሰግደን ስንመለስ የውስጥ ደስታና እፎይታና ሌሎችንም የዲንም የዱኒያ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊህን ሳንሰለች እንስገድ።

አላህ ያግራልን


ታላቁ የረመዷን ጾም ነገ ቅዳሜ ይጀምራል!

በሳኡዲ አረቢያ የረመዷን ጨረቃ መታየቷን ተከትሎ ታላቁ የረመዷን ጾም ነገ እንደሚጀመር ተገልጿል።

ዛሬ የተራዊህ ሶላት የሚጀመር ሲሆን ነገ ቅዳሜ የረመዷን ጾም ይጀምራል ተብሏል።

⭐️ረመዳን ሙባረክ⭐️


ዛሬ ኸሚስ የሻዕባን ወር 28 ነው(28/08/1446)።

ጁመዓ ምሽት ጨረቃ ከታየች ቅዳሜ ረመዷን 1 ይሆናል ጨረቃ ካልታየች ሻዕባን ወር ቅዳሜ 30/08/1446 ዓ᎐ሂ ይሆንና እሁድን ረመዷን1 ብለን ጾም እንጀምራለን።


አላህ ከቤተሰቦቻችን፣ ከዘመዶቻችን፣ ከጓደኞቻችን ጋር በሰላም አድርሶን በዚክር በኢባዳ ረመዳንን የምናሳልፍ ያድርገን።


🌙 #ጾምን_የሚያበላሹ_ነገሮ 🌙

1 ሆን ብሎ መብላትና ሆን ብሎ መጠጣት።
   🌙 ረስቶ ተሳስቶ የበላ የጠጣ ሰው ጾሙ አይበላሽም

2  ምግብና መጠጥ የሚተኩ ነገሮች መጠቀም።
የምግብ መዳኒቶች  የምግብ 💉መርፌ መወጋት ጾም ያበላሻል።
🩸ደም መቀበል ጾምን ያበላሻል።

🌙 ደም መስጠት ግን ጾም አያበላሽም።
 
3   የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም።
ጾመኛ ሆኖ የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም ፆም ያበላሻል ከባድ ቅጣትም አለው ይህን የፈፀመ ሰው፦
     ①☞ሙእሚን የሆነ/ችን ባሪያ ነፃ ማውጣት አለበት።  ይህን ካልቻለ
     ②☞ከቀዷኡ ቀን  ውጭ  ሁለት ተከታታይ ወራት ያለማቋረጥ መፆም አለበት ።  ይህን ካልቻለ
     ③☞ ስልሳ(60) ሚስኪኖችን ማብላት አለበት።
 
4  የዘር ፈሳሽን(መንይ) ሆን ብሎ ማፍሰስ።
በጅ በመነካካት፣ ከሚስት ጋር በመተሻሸት᎐᎐᎐የዘር ፈሳሽ ከፈሰሰ ጾም ይበላሻል።

🌙 ጾመኛ ሆኖ በቀኑ ክፍለ ጊዜ  በድካም ተኝቶ በእንቅልፍ ልብ የሚከሰት የዘር መፍሰስ(ኢህቲላም መሆን) ጾም አያበላሽም።

5 ሆን ብሎ ማስታወክ።
  ሆን ብሎ እጅን ወደ ጉሮሮ ከቶ᎐᎐᎐ ማስታወክ ጾም ያበላሻል።
  🌙  ሳይታሰብ ከቁጥጥር ውጪ መቶ በራሱ ከወጣ(ካስታወከ) ጾም አይበላሽም።

6 የወር አበባና የወሊድ ደም መፍሰስ ጾም ያበላሻል።
  🌙 ከተለመደው የወር አበባ ቀን ውጪ በበሽታ ምክንያት የሚፈስ ደም(ኢስቲሃዳ) ጾም አያበላሽም።
🔺ጥንቃቄ
🔴ከኢስላም መውጣት ጾም ያበላሻል።
🔴አላህን አስቦ ሳይሆን ለይሉኝታ ብሎ መጾም ጾምን ያበላሻል።
🔴ጾምን ለማቋረጥ በቁርጥ መወሰን ባይበላም ባይጠጣም ጾም ያበላሻል።

🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙
⭐️ከሰውነት ደም ማውጣትን መተው የተመረጠ ነው።
⭐️ለዋግምት ውዝግብ ያለበት ጉዳይ ነው መራቁ ተመራጭ ነው።
🌟 ደም መለገስ በሌሊት ቢሆን ይመረጣል።
   ጾመኛ ሆኖ መለገስ ድካምና ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል
⭐️ ለህክምና ምርመራ ናሙና የሚወሰድ ደም
      ነስር(የአፍንጫ መድማት)
      ከቀላል ቁስል የሚፈስ ደም
      ጥርስ በመነቀል የሚፈሱ ደሞች ጾም አያበላሹም።
https://t.me/MuslimNegnEneSul
   https://t.me/MuslimNegnEneSul
https://t.me/MuslimNegnEneSul

20 last posts shown.

315

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

🕌     #ከጁምዓ_ቀን_ሱናዎች_ጥቂቶቹ 🕌 ☑️ በጠዋት መነሳት ☑️ ገላን መታጠብ ☑️ ጥሩ ልብስ መልበስ ☑️ ሽቶ መቀባት (ለወንድ) ☑️ ሲዋክ ...
ሁሌም ከሰዎች ጋር ስታወራ #እውነትን አውራ እውነትን የምታወራ ከሆነ #ማስታወስ_አይጠበቅብህም😊
ዛሬ ኸሚስ የሻዕባን ወር 28 ነው(28/08/1446)። ጁመዓ ምሽት ጨረቃ ከታየች ቅዳሜ ረመዷን 1 ይሆናል ጨረቃ ካልታየች ሻዕባን ወር ቅዳሜ 30/08/...
★★★★★    #መልካም_ጁመዓ    ★★★★★ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا نُودِىَ لِلصَّلَوٰةِ مِن يَ...
🌙 #ጾምን_የሚያበላሹ_ነገሮ 🌙 1 ሆን ብሎ መብላትና ሆን ብሎ መጠጣት።    🌙 ረስቶ ተሳስቶ የበላ የጠጣ ሰው ጾሙ አይበላሽም 2  ምግብና መጠጥ የሚ...