በመዲናዋ እስከ ምሽት 4:00 ድረስ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በማይሰጡ አሽከርካሪዎች ላይ የ5 ሺሕ ብር ቅጣት እንደሚጣል ተገለጸ
በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ምሽት 4:00 ድረስ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በማይሰጡ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የ5 ሺሕ ብር ቅጣት እንደሚጣል የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በደንብ ቁጥር 185/2017 በተደነገገው ደንብ መሠረት ማንኛውም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ እስከ ምሽት 4፡00 ሰዓት የትራንስፖርት አገልግሎትን መስጠት እንደሚጠበቅበት አሳውቆ ማንኛውም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በፊት የትራንስፖርት አገልግሎትን ማቋረጥ፣ ከስምሪት መስመር ውጪ አገልግሎት መስጠት፣ አቆራርጦ መጫንና የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ካወጣው ሕጋዊ ታሪፍ ውጪ ሕብረተሰቡን ማስከፈል እንደማይቻል ቢሮው በጥብቅ አሳስቧል፡፡
Via @mussesolomon