#ቴዎድሮስ_ካሳሁን
#አርማሽ (ቀና በል)
አርማሽ ይውለብለብ …ከደጄ
ልቤ ናፍቆሻል …ወዳጄ
እኔስ እስካይሽ …ጨነቀኝ
ሃገሬ መምጫሽ …ናፈቀኝ
ቀን እየሄደ …ቀን መጣ
ልቤ ከሀሳብ…ሳይወጣ
መጥታ ታብሰው …እንባዬን
ሀገሬን ጥሯት …አርማዬን
መቼም በዚህ ምድር ላይ… ሄዶ ነው ሁሉም ቀሪ
ሀገር ናት… ቋሚ ሰንደቅ… ለዘላለም… ኗሪ
ትናንትም እንደ ጀምበር… እያዩት ከዐይን ይርቃል
ኢትዮጵያ እንድትመጪ… ስንት ቀን ይበቃል?
እኔማ… ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ
ግን ባባሁ… ናፈቅኩሽና እንባ ቀደመኝ
እኔማ… ናፈቅኩ እስካሁን… ተስፋ ሰንቄ
በወንዜ… በአገሬ እያለሁ… ሐገር ናፍቄ
ወጥተሽ በምሥራቅ…አንቺ የዓለም ጀንበር
አንድ አርጊንና …ጠላትሽ ይፈር
የቦረቅኩበት …በልጅነቴ
የያኔው መልክሽ… ብቅ ሲል ፊቴ
እየመለሰኝ …ወደ ትናንቱ
ናፍቆኝ በብርቱ
ትዝ አለኝ የጥንቱ
እህህ …………………አሂ… …………
አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ
ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ
እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ
ሃገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ
አገር ለክብሩ ሲጣራ
ከፍ ያደረገው ባንዲራ
ዘመም ሳይል ቀን ጎድሎ
ባክሽ ኢትዮጵያ ነይ ቶሎ
ብዙ ነሽ አንቺ ሀገሬ የሞላሽ ታምራት
ምኩራብሽ የተፈራ የነፃነት ቤት
የአርበኞች የድል ችቦ ለትውልድ እንዳበራ
መኖር ለአገር ሲሆን …ሞትም አያስፈራ
እኔማ… ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ
ግን ባባሁ… ናፈቅኩሽና እንባ ቀደመኝ
እኔማ… ናፈቅኩ እስካሁን… ተስፋ ሰንቄ
በወንዜ…በአገሬ እያለሁ… አገር ናፍቄ
ዓመት ዓውደዓመት… ድገመን ሲሉ
ልጆች በቀዬው …ችቦ እያበሩ
መስቀል ፋሲካ …ኢድ እንቁጣጣሽ
ዓውደዓመት አይሆን …አንቺ ካልመጣሽ
ዘመን አድሰሽ …በፍቅር ቀለም
ብቅ በይ ኢትዮጵያ …ሁኚና መስከረም
ሆነሽ መስከረም……አሲዮ
ብቅ በይና ……… ቤሌማ
እንበል አሲዮ…………አሲዮ
ናና ቤሌማ …………ቤሌማ
ብቅ በይና …አሲዮ…ሆነሽ ሙሽራ …ቤሌማ
ይብቃን ስደቱ …አሲዮ…ስቃይ መከራ …ቤሌማ
ቤሌ ቤሌማ …ናና ቤሌማ…
ዘር ያበቀለው…(አሲዮ) ታጭዷል መከራው…(ቤሌማ)
ኢትዮጵያዊነት …(አሲዮ) አሁን ነው ተራው…(ቤሌማ)
አሲዮ አሲዮ…… ናና ቤሌማ
ቤሌማ… ……ናና ቤሌማ
ዘመን አድሰሽ …(አሲዮ) በፍቅር ቀለም …(ቤሌማ)
ብቅ በይ ኢትዮጵያ…(አሲዮ) ሁኚና መስከረም…(ቤሌማ)
እኛስ ከመንገድ ላይ… ጠፍተን መቼ አወቅነው
ብንሄድ ብንሄድ… አንደርስም ገና ነው
በመባረኪያችን …በመንገድ ላይ ዝለን
አይበቃም ወይ ማሳል… በዘር ጉንፋን ታመን
በዘር ጉንፋን ታመን
ቀን አለ በሉ ………አለ በሉ
ቀና እንደገና…… አለ ገና
ለኢትዮጵያዊነት… ቀን አለ ገና
ስምሽን በክፉ…አለ ገና…ያነሳሽ ጠፍቶ
አርማሽ ከፍ ሲል…አለ ገና…ሰማይ ላይ ወጥቶ
እኛ ልጆችሽ…አለ ገና…ልናይ ቆመናል
አንድ ቀን መጥቶ…አለ ገና…አንድ ያደርገናል
ቀን አለ በሉ ቀን አለው ገና
ስንቱ ተሰደደ …ይብቃን ሐዘን ለቅሶ
አንድ ሆነሽ ኢትዮጵያ …ባየን ፍቅር ነግሶ
ዘር ያበቀለው …… ታጭዷል መከራው
የኢትዮጵያዊነት …… አሁን ነው ተራው
ቀና በል አሁን ቀና በል ቀና
ቀና በል አሁን ቀና በል ቀና
የጀግኖቹ ልጅ ……አንተ ነህና…
ከአገር ወዲያ ሞት… ሞት የለምና…
ዝም ያለ መስሎን… ኢትዮጵያዊነት…
ማንም አይገታው …የተነሳ ዕለት…
ቀና በል አሁን… ቀና በል ቀና
ጥንት አባቶችህ …ያቆዩት‘ን’
ከፍ አርገህ ይዘህ ባንዲራህ’ን‘
ቀና በል አሁን
ቀና በል ቀና
ቀና በል
እ እ እ………………
❇️
@muzicalword ❇️
http://www.youtube.com/watch?v=PkOstq4GuLk