ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የቅድመ ክፍያ ካርድ ሥራ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር አካሄደ፡፡
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ “ ቴክኖሎጂ መር በሆነው የባንክ ኢንደስትሪ አሸንፎ መውጣት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በዚህም ማስተርካርድ ባንካችንን በአጋርነት ስለመረጠ ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ" ብለዋል፡፡
የቅድመ ክፍያ ካርድ አገልግሎቱ ለደንበኞች ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የክፍያ መሳሪያ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ይህም ደንበኞች ለዕለትተዕለት ወጪዎች፣ ለኢንተርኔት ኦንላይን ግብይት እና ከጉዞ ጋር ለተያያዙ ግብይቶች በቀላሉ ክፍያ እንዲፈጽሙና ሌሎች የተለያዩ ቁልፍ ፋይዳዎችም እንዳሉት አብራርተዋል። ካርዱ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለውና ንብ ኢንተርናሽናል ባንክም በሁሉም ቅርንጫፎቹ ዝግጁ የሚያደርገው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
“25ኛ አመት የብር ኢዩቤልዩ የምሥረታ በአሉን እያከበረ የሚገኘው ባንካችን ለደንበኞቹ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ነው”ም ብለዋል፡፡
በማስተርካርድ ኢንኮርፖሬሽን ዴቨሎፕመንት የኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ሱዳን ዋና ዳይሬክተር አቶ እልፍዓገድ አረጋኻኝ በበኩላቸው “በዚህ ደንበኞች የመረጡትን ነጻነት ያለው የፋይናንስ ስርአት እንዲከተሉ በሚደግፍ ቴክኖሎጂ ረገድ ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር ለመስራት በመቻላችን ትልቅ ደስታ ይሰማናል” ብለዋል፡፡
ባንኩ ይህንን የቅድመ ክፍያ ማስተር ካርድ በመጠቀሙ ደንበኞቹ ያለምንም እንከን በአለም አቀፍ ንግድ ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያስችል ሲሆን የሁለቱ ተቋማት ግንኙነት እያደገ የሚሄድ መሆኑንና ላቅ ያሉ የቴክኖሎጂው አሰራሮችን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ጠቅሰዋል፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!