ትግል መሪን ይፈጥራል ታጋይ እስካለ ለህዝቡ ይታመናል
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
። በመሪዎች እና አስተባባሪዎች ሁናቴ የሚቆም ትግል፥ ትግል አይደለም።የሚመራን ሰው አንድ ነገር ከሆነ ፣ የሚያታግለን ድርጅት አንድ ነገር ከሆነ፥ አለቀልን የሚመስል ስጋትና አመለካከቶች በልካቸው መጤን አለባቸው።የአማራ ትግል ፡ የሆነ ሰውዬ ደሕና እስከሆነበት ድረስ ፥ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ ጤነኛ እስከሆነ ብቻ ሕልውና የሚኖረው አይደለም፤ ሊሆንም አይገባም።
ምናልባት የአላማ ጥራት ፥ የስትራቴጂ እና ስልቶች ትክክለኛነት ላይ የጠራ ግንዛቤ አለመያዝ የፈጠረው ሊሆን ይችላል። የአላማ ስትራቴጂ እና ስልቶች ጥራት ቢኖር ፣ አላማው ከግለሰቦች በላይ መሆኑን እንረዳ ነበር። የአላማው አልፋና ኦሜጋ ሕዝብ እንደሆነ እንገነዘብ ነበር።
ፊት መጥተው የአማራን ጉዳይ በሚችሉት ልክ የሚታገሉና የሚያታግሉትን ግለሰቦች ማድነቅ ተገቢ ነው ማለት ፥ ግለሰቦቹ ትግሉንና አላማውን ይተካሉ ማለት አይደለም ። ወይንም በዚያ መጠን ውዳሴና እርግማን መቅረብ አለበት ማለት አይደለም።
በዚህ ትግል ላይ ፊታውራሪ የሆኑ መሪዎች በግልም ሆነ በቡድን ለአማራ ሕዝብ ትግል የየራሳቸውን አወንታዊና አሉታዊ ሚና ሊወጡ ይችላሉ። መቼም ቢሆን ግን የአማራን ብሔራዊ ትግልና አላማ አይተኩም። የአማራ ትግል ከግለሰቦቹ በላይ ነው። ሁሉም ከአማራ በታች ናቸው። ከአማራ አላማዎች በታች ናቸው። የአንድ ትውልድ አላማ ከያዝን አዎ ፥ ትግላችን የሕልውና ይሆናል።
ከፕ/ር አስራት ፣ ከጀነራል አሳምነው ፣ ከዶ/ር አምባቸው ፣ ከጎቤ መልኬ ፣ ..... ከሌሎችም ፣ ከሌሎችም ጋር የተቀበረ ትግል እና አላማ አለመኖሩን ማረጋገጥ እስከቻልን ድረስ የአማራ ትግል ዛሬም ነገም ሕያው ነው።
አሁን፥ ፊት ካሉት እና ከሚመጡት ጋር የሚቀበር አላማ እና ትግል አለመኖሩን ማረጋገጥ የሚቻለው አላማችን የትውልድ፣ ትግላችን የሕዝብ ሲሆን ነው።
የምንታገለው ለላቀ አማራዊ ሕልውና እንዲሁም የፍትሕና ርትዕ መረጋገጥ እስከሆነ ፥ በጥቂት ግለሰቦች ወይም ቡድኖች የትግል ዘመን ብቻ የሚቆምና የሚቀጥል፣ የሚሳካ እና የሚወድቅ እንዳይሆን አድርገን ባሕር ለሆነው ሰፊ ሕዝባችን እናስርፀው ።
ግለሰቦች የላቀ ሚና አላቸው!!
አያከራክርም !!
መሪዎች ያስፈልጋሉ!!
ማክበርና መጠበቅ ይገባል!!
አያከራከርም!!
በትግል ትክክለኛነት ላይ ያመነ ማሕበረሰብ ሲኖር መሪዎች ሁሌም ይወጣሉ።የእነዚያ መሪዎች ሚናቸው ፣ ቆራጥነታቸው፣ ተቆርቋሪነታቸው፣ አላማቸው ፣ የሚከፍሉት ዋጋ ለሕዝብ የተጋራ እሳቤ መሆኑን ማረጋገጥ እንጂ፥ እነሱን ራሳቸውን ትግል ማድረግ አይጠቅምም !።
አንዳንድ መሪዎች የሚታገሉለትን ትግል አላማና ማስፈፀሚያ ለሌላው ሳይሸጡትና ሳያጋሩት ይቀራሉ። ስለሆነም ግለሰቦቹ እንጂ ሀሳባቸው የትግል ማዕከል አይደረግም። ብዙ ጊዜ ግለሰቦችን ትግል የሚያደርጉ ሰዎች፥ ስምና ፎቶ ይዞ መዞር እንጂ የሚያነሱ የሚጥሏቸውን ሰዎች አላማ እና የትግል መንገድ አያውቁትም።
በግለሰቦች ላይ የሚንጠለጠል አጀንዳና ትግል አደገኛ ነው።
፦ አንደኛ ግለሰቦቹን ያሳስታቸዋቸል፥ አይተኬነት ስሜት ይፈጥራል።
፦ ሁለተኛ ግለሰቦቹ ከሆኑትና ከሚችሉት በላይ የሆነ ገፅታ (Image) በመፍጠር የሚሠሩትና የሚጠበቅባቸው የተራራቀ ሲመስለን እንቀየማቸዋለን።
፦ ሶስተኛ የመሳሳት ተፈጥሯዊ መብታቸውን ይነፍጋል።
፦ አራተኛ ቢሳሳቱ ወይ ቢጠፉ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይፈጥራል። ሕዝብን በተግባር የሚያንቀሳቅስ አጀንዳ እናስርፅ፣ እንታገል !።