ስፍራችሁ ካልሆነ . . . ውጡ!
ስፍራ ማለት፣ ያላችሁበት ስራ፣ የምትኖሩበትን ቤት፣ ጓደኝነታችሁን ወይም ሌሎችን የወደፊታችሁ የሚወስኑ ሁታዎችን የሚወክል ጉዳይ ነው፡፡ ከተጠቀሱትና ከመሰል ሁኔታዎች አንጻር ውስጣችሁ ያመነበትን፣ ለእናንተ ተስማሚና ትክክለኛ የሆነውን “ስፍራችሁን” ማግኘት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
ስፍራችሁን ለይታችሁ ያለማወቃችሁ ቀንደኛው አጉል ውጤት ያላችሁበትን ስፍራ ተቀብላችሁ እዚያው የመክረማችሁ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ሲሆን፣ እድሜያችሁን እንዲሁ ታባክናላችሁ፣ በአንድ ስፍራ ተተክላችሁ በመቅረታችሁ ምክንያት ትክክለኛና ለእናንተ መሆን የሚገባቸው እድሎች ያመልጧችኋል፣ ውስጣችሁ ተስፋ ይቆርጣል . . . ፡፡ ስለዚህ ስፍራችሁን ልይታችሁ ለማወቅ ማድረግ ያለባችሁን ማድረግ አለባችሁ፡፡
ስፍራችሁን ከለያችሁ በኋላ እዚያ እስክትደርሱ ድረስ አሁን ባላችሁበት የመቆየታችሁ ሁኔታ ችግር የለበትም፡፡ ስፍራችሁን ከለያችሁ በኋላ ግን አሁን ያላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ካለማቋረጥ ወደትክክለኛ ስፍራች የምትደርሱበትን እቅድ ማውጣት አለባችሁ፡፡
ያንን እቅድ ካወጣችሁ በኋላ ደግሞ ጉዞ በመጀመር ካለማቋረጥ ወደዚያ መንቀሳቀስ የግድ ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ የሚያስከፍላችሁን ሁሉ መስዋእትነት ከመክፈል ወደኋላ አትበሉ፡፡
ስፍራችሁን ከለያችሁ በኋላ እዚያ መድረስ ከባድና መስዋእትነት እንደሚያስከፍላችሁ እስባችሁ ያላችሁበት ከቀራችሁ የበለጠ ዋጋ ያስከፍላችኋል፡፡
አንድ ነገር አትዘንጉ፡- ወደ ትክክለኛው ስፍራችሁ ለመራመድ ከምትከፍሉት ዋጋ የበለጠ የምትከፍሉት ስፍራችሁ ባልሆነ ቦታ በመቆየት ነው፡፡ በመንቀሳቀስ የአጭር ጊዜ ዋጋ ትከፍላላችሁ፣ ያላችሁበት በመቅረት ግን የረጅም ጊዜ ዋጋ ትከፍላላችህ፡፡
ያላችሁበትን ስፍራ መርምሩ፣ ትክክለኛውን ስፍራችሁን ለዩ፣ ከዚያም በጥንቃቄ ወስኑና ካላችሁበት ወጥታችሁ ተንቀሳቀሱ!
Dr. eyob ✍️
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery