Forward from: የስብዕና ልህቀት
"መውደቅን መፍራት የሚመጣው የማይረቡ እሴቶችን ከመምረጥ ነው።"
✍️ ማርክ ማንሶን
መራመድ እየተማረ ስላለ ህፃን ልጅ ስታስብ፣ ያ ልጅ ለመቶዎች ጊዜ እየወደቀ ራሱን ይጎዳ ነበር፡፡ ነገር ግን የትኛውም ነጥብ ያንን ልጅ ቆም ብሎ “አይ ይቅር ሳስበው መራመድ ለእኔ አይሆንም እዚህ ላይ ጥሩ አይደለሁም” ብሎ እንዲያስብ አያደርገውም፡፡
መውደቅን መሸሽ በህይወታችን በኋላ ላይ የምንማረው ነገር ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ አብዛኛው የትምህርት ስርዓታችን ነው፡፡ ሌላው ትልቁ ድርሻ የሚመጣው ደግሞ ሁልጊዜ ለማዘዝ በሚሞክሩ ሀሳብን በሚያናንቁ ልጆቻቸው እየወደቁም በማይፈቅዱ ቢሆን በራሳቸው እንዲማሩ እንዲያውም የትኛውንም ያልታታዙትን ነገሮች በመሞከራቸው ልጆቻቸውን ከሚቀጡ ጥብቅ ወላጆች ነው፡፡ ከዚያ ደግሞ ያለማቋረጥ የከዋክብትን በስኬት ላይ ስኬት ማግኘት የሚነግሩን መገናኛ ብዙሃን አሉ፡፡ እነዚህ መገናኛ ብዙሃን ስኬቱን ሲነግሩን ያንን ስኬት ለማግኘት የሚያስፈልጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ከባድና አሰልቺ ልምምዶችን አያሳዩንም፡፡
በሆነ ነጥብ ላይ አብዛኞቻችን መውደቅ የምንፈራበት ቦታ ላይ እንደርሳለን፡፡ የዚያን ጊዜ በደመነፍስ ውድቀትን እንሸሽና ፊት ለፊታችን ባለው ነገር ላይ ወይም በለመድነው ነገር ላይ ብቻ ተጣብቀን እንቀራለን፡፡
ይህ ደግሞ ያስረናል፡፡ አፍኖ ይይዘናል፡፡ በእውነት ስኬታማ የምንሆነው ለመውደቅ በመረጥንበት የሆነ ነገር ላይ ብቻ ነው፡፡ ለመውደቅ ፈቃደኛ ካልሆንን ስኬት ለማግኘት ፈቃደኛ አይደለንም ማለት ነው፡፡
አብዛኛው መውደቅን መፍራት የሚመጣው የማይረቡ እሴቶችን ከመምረጥ ነው፡፡ ለምሳሌ ራሴን የምለካበት ደረጃ “የማገኘው ሰው ሁሉ እንዲወደኝ ማድረግ” በሚል ቢሆን መውደቄ የሚወሰነው በራሴ ድርጊቶች ሳይሆን መቶ በመቶ በሌሎች ድርጊቶች ላይ በመሆኑ ጭንቀታም እሆናለሁ፡፡ እኔ ልቆጣጠረው የምችለው ነገር ባለመሆኑ ለራሴ ያለኝ ዋጋ በሌሎች ፍርድና ምህረት ስር ይወድቃል ማለት ነው፡፡
ነገር ግን በዚያ ፈንታ መለኪያዬን “ማህበራዊ ህይወቴን ማሻሻል” ላይ ባደርገው ሌሎች ሰዎች ምንም አይነት ምላሽ ቢኖራቸው እኔ ግን “ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት መኖር” በሚለው እሴት መሰረት መኖር እችላለሁ፡፡ ለራሴ ያለኝ ዋጋ የተመሰረተው በራሴ ባህርያትና ደስታ ላይ ይሆናል ማለት ነው፡፡
የማይረቡ እሴቶች ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ የሚጨበጡ ውጫዊ ግብ የያዙ ናቸው፡፡ እነዚህን ግቦች መከተል ጭንቀት ያመጣል፤ ልናገኛቸው ብንችል እንኳን ባዶነትና ሕይወት አልባነት እንዲሰማን ያደርጉናል፡፡ ምክንያቱም አንድ ጊዜ ካገኘናቸው የምንፈታቸው ሌሎች ችግሮች አይኖሩንም፡፡የተሻሉ እሴቶች እንደተመለከትነው ሂደት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡
“በአለማዊ ደረጃ ስኬታማ መሆን ለሚለው እሴት መለኪያህ “ቤትና አሪፍ መኪና መግዛት” ቢሆን፣ ያንን ለማግኘት ሀያ አመታት ወጥረህ በመስራት ታሳልፋለህ፡፡ ከዚያ አንድ ጊዜ መለኪያህን ካገኘኸው የሚቀርህ ነገር አይኖርም፡፡ ከዚያ መላውን እድሜህን ሲያሽከረክርህ የኖረው ችግርህ ስለተወገደ የጉልምስና ዘመን ቀውስን መቀበል ትጀምራለህ፡፡ማደግን ለመቀጠልና ለመሻሻል ሌሎች አጋጣሚዎች የሉም፡፡ እናም ደስታን የሚፈጥረው ደግሞ እድገት እንጂ በዘፈቀደ የመጡ ረጅም ዝርዝር ያላቸው ክንውኖች አይደሉም፡፡
ፒካሶ መላውን ህይወቱን ብዙ የሰራ ነው፡፡ እስከ ዘጠናዎቹ እድሜው ድረስ የኖረና እስከ መጨረሻዎቹ ቀናት ድረስ ስዕል ይሰራ ነበር፡፡ መለኪያው “ዝነኛ መሆን” ወይም “በጥበቡ አለም ብዙ ገንዘብ መስራት” ወይም “አንድ ሺ ስእሎች መሳል” ቢሆን ኖሮ ከረጅም ጊዜ በፊት አንድ ቦታ ላይ ቆሞ ይቀር ነበር፡፡ ከዚያ በጭንቀት ወይም ራስን በመጠራጠር ይሸነፍ ነበር፡፡ ስራዎቹን እንዲህ ከአመት ወደ አመት እንዲሻሻሉና እንዲፈጠሩ ማድረግ አይችልም ነበር፡፡ሽማግሌ ሆኖም ካፌ ውስጥ ቁጭ ባለበት ብቻውን በወረቀት ላይ በመሳሉ ደስተኛ ነው፡፡ የተመሰረተበት እሴት ትጉህ እና ፈጣሪ መሆን ነበር፡፡ የእነዚህ እሴት መለኪያ የማያልቅ ቀጣይነት ያለው የሕይወት ዘመን ሂደት ነው።
#share
የስብዕና ልህቀት
@Human_intelligence