ከሀገር ከሰፈሩ እኔ አንቺን መርጬ ጨረቃ አይንሽን አያለሁ ከሁሉም አብልጬ ጨረቃ ከተማማልንበት ብለሽ ወለም ዘለም አደራን አደራን እንዳንቀያየም ሺ ሰው ብትፈጂ ብትለፊ ብትደክሚ እንድ ሰው ላንድ ነው የሰው ምክር ስሚ እዛም እዛም አይበል አይቀላምድ አይንሽ ሁሉ አማረኝ ይቅር ላያዛልቅሽ ከኔው ጋር ይሁን ልብሽ ይቀመጥ ፍቅር በወረት ተይ አይለወጥ እንመካከር ፍቅርን አክብሪ መዋደድ ይጥበቅ ከጎኔ ኑሪ ነሽ የኔ ጨረቃ አይኔም አይቶሽ አይበቃ ልቤም ወዶሽ አላበቃ ነሽ የኔ ጨረቃ ያንቺን አኔ አላውቅም የኔ ብሶ ይገኛል ጨረቃ ፍቅር እንደውሀ ጥም ያንገበግበኛል ጨረቃ የሆዴን ገልጬ መንገሬ አስጨክኖኝ ከረሳሽኝማ ጉድ ነው ወረት ይዞሽ የማትሆኚኝ እንደው የማታዛልቂኝ ልቤን ተው ልበለው በይ ቁርጡን ንገሪኝ ልቤ ከመናፈቅ ከምኞት አይድንም ካንቺ ጋር ካልሆነ ኑሮ አይማርከኝም ቆላ ውረጄ ደጋ ወጥቼ ተመልሻለሁ አንቺን አግኝቼ ወዳጅ ዘመዴ አንቺው ነሽና ከኔው ጋር ሁኚ በይ ቁረጪና
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏