#መች_መች_ነው ?
ለአንዳንድ ድርጊቶቻችን የነበርንበት ሁኔታ ወሳኝ ሊሆን ይችላል። እንደሰው ለቅሶ ላይ ቆመን የሳቅ መለከት አንነፋም። ሰርግም ላይ ሆነን ሙሾ ስናወርድ አንገኝም። ጸጥታ በጽኑ በሚፈለግበት ቦታ ስንጮህ ብንገኝ እንደ እብድ እንታያለን። ለዚህም ባለንበት ሁኔታ እና ቦታ ልክ በእኛ የሚሆነው ነገር ይወሰናል። ነገር ግን አሁን እንደ ሰው ብቻ ሳይሆን እንደ ክርስቲያን ባለንበት ሁኔታ መወሰን አለብን ወይ የሚለውን ሃሳብ እንመልከት።
ለምሳሌ ምስጋናችን ለእግዚአብሔር የሚሰዋው መች መች ነው? ነገር ሲሞላልን? ሁኔታው ሲሳካልን? ህይወት ሲደላደልልን? በረከት ብለን የምናስበው ሲቀርበን? በትምህርት ወይ በስራ ሲሰምረልን? ተወዳድረን ስንረታ? ተሰልፈን ስንቀድም? ከንድተን ስንጨብጥ? አይተን ስንደርስ? በዚህ ውስጥ አመስግነን ይሆናል። በእርግጥ በዚህ ውስጥ ማመስገን እጅግ ቀላል እና ለማንኛውም ሰው የሚቻል ነው።
ነገር ግን ክርስቲያን መች መች ነው ማመስገን ያለበት? በመጽሐፍ “ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።”( ኤፌ 5፥20) “ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ”(1ኛ ተሰሎ 5፥17-18) “እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት።”(ዕብራውያን 13፥15) “እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር በአፌ ነው።” (መዝሙር 34፥1) ተብሎ ተጽፏል።
ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ማመስገን፣ በሁሉ ማመስገን፣ ዘወትር የምስጋና መሥዋዕት ለእርሱ መሠዋት ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ሃዘን ሲገጥመንም ማመስገን? ሳይሳካ ሲቀርም ማመንገን? ሁኔታው ሲጠምም ማመስገን? ፈተናው ሲያይልም ማመስገን? ከባድ ሁኔታ ላይ ነኝ ስንልም ማመስገን? አዎ በዚህ ሁሉ ነገር ውሰጥ ሆነን ማመስገን ማለት ነው።
በመርህ ደረጃ ይህን ቃል ከእግዚአብሔር ብንወስድም ቅሉ ወደ መሬት በማውረድ ረገድ እና በህይወት ይህንን ከመላድ አኳያ ብዙዎቻችን ችግር አለብን። እግዚአብሔርን ማመስገን የሚታየን ሰኬት ያለነው ነገር ሲሆንልን ብቻ ነው። ይሄ ደግሞ ዘወትር፣ ሁል ጊዜ እና በሁሉ የተባለውን የእግዚአብሔርን መርህ እንድንጥስ ያደርገናል።
ይህን ሃሳብ በጣም ለማቅረብ እንዲያመች በህይወታችሁ ከባድ ያላችሁትን ጊዜ አስቡት። አይገፋም ያላችሁትን ወቅት አሰላስሉት። አያልፍም ያላችሁትን ምሽት እስኪ አሰታውሱት። በእርግጥ በዛ ጊዜ አመስግኑ ብንባል ምስጋና ነው ወይስ ማጉረምረም ነው የሚቀድመን? መዘመር ነው ወይስ ማልቀስ ይቀልን ይሆን? የቱን ነው ያደረገነው? የቱንስ ነው የምናደርገው?
እግዚአብሔር ሆይ አንተ ሁል ጊዜ ትክክል ነህ በማለት ፈንታ ምነው ተውከኝ፣ ምነው እኔን ብቻ የምትፈትነኝ፣ ምን አድርጌህ ነው የምታሰቃየኝ፣ በቃ ለዚህ ነው የፈጠርከኝ ስንል ተሰምተን አናውቅ ይሆን? በሃዘን ባህር ውሰጥ እንኳን ተውጠን ጌታ ሆይ አንተ መልካም ነህ አንተ ሁሌ ትክክል ነህ ስምህ ይመስገን ማለት ነው የክርስትናው ውበቱ።
ይህ ካልሆነ ግን፣ ሲሞላልን ካመሰገንን ግን ከማያምነው መሻላችን ቀርቷል። እግዚአብሔር አባቱ የሆነለት ሰው በምንም አይነት ሁኔታ ውሰጥ ሲያጉረመርም አይሰማም። ምክንያቱም አስተዳዳሪው እግዚአብሔር የህይወቱን መልህቅ በእጁ የያዘ ስለሆነ በምንም ነገር አይናወጥም። ይልቁንስ ተስፋውን እና እምነቱን በእግዚአብሔር ላይ በማድረግ ይጸናል እንጂ። መች መች ነው የሚለው ጥያቄ ለምስጋና አይጠየቅም ምክንያቱም ምስጋናችን የሁልጊዜ ነውና።
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ዘወትር በህይወታችን ያለመወላወል እና በሁኔታ ሳንወሰን አንተን የምናመሰግንበት ጸጋ እና አቅም ለሁላችን ስጠን። አሜን
✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 የካቲት 17 2017 ዓ.ም ተጻፈ
@orthodox_new_mezmur