✧ገብርኤል_ተሾመ ✧
የስሙ ትርጓሜ ሰው የሆነ አምላክ ነው
መልአኩ ገብርኤል በአምላክ ፊት ሚቆመው
ተፈጥሮህ ረቂቅ ከነፋስ ከእሳት
ነዱን የሚያደክም የሚያሳጣ ጉልበት
ሰባት እጥፍ ቢሆን የእሳቱ ነበልባል
አንተ ስትመጣ/2×/ አይችልም ሊያቃጥል
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ገብርኤል ተሾመ በሰማይ በራማ
መጽናናትን ልሰብክ ደስታን ልታሰማ
ርግማን ማለፉን በእውነት ነገረከን
ሰባኬ ወንጌል ነህ/2×/ የአዲሱ ኪዳን
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
የተክህኖ ልብስህ እጅግ የሚያበራ
መብረቃዊ ኮከብ ለዓይን የሚያስፈራ
አየንህ ስትቆም በእግዚአብሔር ፊት
ምስጋናን ስትሰዋ/2×/ ስታሳርግ ጸሎት
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ትካዜና ኀዘን እጅግ የከበበው
ሁሉጊዜ ሚያነባ ከሰው ወገን ማነው
አረጋጊ መልአክ እንዳንተ የለምና
ገብርኤል ሆይ ድረስ/2×/ ስንጠራህ ቶሎ ና
👉ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
✥•┈•●◉༒ ናሁ ሰማን-ዜማ ༒◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
✞ @Nahuseman256✞
✞ @Nahuseman256 ✞
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯
የስሙ ትርጓሜ ሰው የሆነ አምላክ ነው
መልአኩ ገብርኤል በአምላክ ፊት ሚቆመው
ተፈጥሮህ ረቂቅ ከነፋስ ከእሳት
ነዱን የሚያደክም የሚያሳጣ ጉልበት
ሰባት እጥፍ ቢሆን የእሳቱ ነበልባል
አንተ ስትመጣ/2×/ አይችልም ሊያቃጥል
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ገብርኤል ተሾመ በሰማይ በራማ
መጽናናትን ልሰብክ ደስታን ልታሰማ
ርግማን ማለፉን በእውነት ነገረከን
ሰባኬ ወንጌል ነህ/2×/ የአዲሱ ኪዳን
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
የተክህኖ ልብስህ እጅግ የሚያበራ
መብረቃዊ ኮከብ ለዓይን የሚያስፈራ
አየንህ ስትቆም በእግዚአብሔር ፊት
ምስጋናን ስትሰዋ/2×/ ስታሳርግ ጸሎት
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ትካዜና ኀዘን እጅግ የከበበው
ሁሉጊዜ ሚያነባ ከሰው ወገን ማነው
አረጋጊ መልአክ እንዳንተ የለምና
ገብርኤል ሆይ ድረስ/2×/ ስንጠራህ ቶሎ ና
👉ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
✥•┈•●◉༒ ናሁ ሰማን-ዜማ ༒◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
✞ @Nahuseman256✞
✞ @Nahuseman256 ✞
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯