( በአጠቃላይ ምድራዊ ነው ስንል ሰማያዊ፤ ሰማያዊ ነው ስንል ምድራዊ (ብእሲ ሰማያዊ ወመልአክ ምድራዊ) ሁኖ እናገኘዋለን፡፡
ዜማውን በግዕዝ ዕዝል አራራይ የዜማ ስልት የደረሰ፤
በዓለም ደረጃ የዜማ ምልክቶች ባልታወቁበት ጊዜ ዜማዎቹን በምልክት የቀመረ፤
የዜማ ሥርዓትን በመንደፍ የዓመቱን ቀለም ያዘጋጀ
ዜማውን በ4ት ዘመናት ከፋፍሎ፤ ዘመናቱን በንዑሳን ዘመናት ከፋፍሎ ለወራቱና ለሰሙኑ ለእለቱ የሚገባውን ቀምሮ የደረሰ፤
እንኳን በእርሱ ዘመን ዛሬ እንኳን ብዙ ነገሮች ተሰባስበዋል በተባለበት ዘመን ሊሠራ አይደለም ሊታሠብ በማይችሉ መልኩ መጽሕፍትን እንደ ንብ እየቀሰመ፤ እንደ ወይን እየጨመቀ፤ እንደ አረቂ እያጣራ፤ እየተረጐመ ላሰበው ድርሠት ያዋለ፤ … ስለ ቅዱሱ ምኑን ተናግረን እንጨርሰዋለን፡፡ …
.. ይኼማ ኢትዮጵያዊ ሊኾን አይችልም ብለው ብዙ የውጭ ሃገራት ወደ ራሳቸው ለመውሰድ የሚዳዳቸው፡፡
የቅዱስ ያሬድ ልደትና የስሙ ትርጓሜ
ꔰ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ ሚያዚያ 5 ቀን በ505 ዓ.ም. ከአባቱ ይስሐቅ(አብድዩ) ከእናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) በአኵሱም ከተማ ተወለደ፡፡ (አንዳንዶች /መሪጌታ ልሳነ ወርቅ/ ልደቱን 493 ዓ.ም. ነው ይላሉ/፤ እንዲሁም አቶ በላይ ግደይና መሪጌታ ልሳነ ወርቅ አባቱ ኖኅ ነው ይሉና መሪጌታ ይስሐቅ የቀለም አባቱ/መመህሩ/ ነው ይላሉ፡፡
ꔰ የስሙም ትርጓሜም ያሬድ ማለት እንዚራ፣ በገና፣ መሰንቆ ማለት ነው ፡፡ እነዚህ መሣሪያዎች በስልት በስልት ሲመቱ ለሚሰማቸው ደስ እንዲያሰኙ የያሬድም ዜማ በንጉሠ ነገሥቱ ክርስቶስ አደባባይ በቤተ ክርስቲያን ሲሰማ መላእክትን፥ ሰውንና እንስሳትን ደስ ያሰኛልና፡፡
( አንድም ያሬድ ርደት፣ ወሪድ፤ መውረድ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ሰማያዊውን ልዩ ጣዕመ ዜማ ወደ ኢትዮጵያ አውርዷልና፡፡
( አንድም ያሬድ ማለት ንብ ማለት ነው፤ ንብ የማይቀስመው አበባ እንደሌለ ሁሉ ቅዱስ ያሬድም ከመጻሕፍት የማይጠቅሰው የማይቀሰመው የለም፤
( አንድም ያሬድ ማለት ረአዬ ምሥጢር፥ ነጻሬ ኅቡአት ማለት ነው፤ የመላእክት ምሥጢራት የነበሩትን ጸዋትወ ዜማ አምልቶ አስፍቶ ተናግሯልና፣ ነጻሬ ኅቡአት አለ፥ ኅቡእ (ስውር) የሆነ የጻድቃን፣ የሰማዕታት የነቢያት የሐዋርያትን ገድል አምልቶ አስፍቶም ይናገራልና፡፡
-ዐፄ ካሌብ ቤተ እስራኤል፣ ገብረክርስቶስና ገብረ መስቀል የሚባሉ ልጆች ነበሩት፤ ቅዱስ ያሬድ የተነሳው ከእነዚህ ውስጥ በዓፄ ገብረመስቀል ዘመን ነው፡፡
ሌሎች ቅጽል መጠሪያ ስሞቹ፤
ሊቅ (ርእሰ ሊቃውንት )
ዓርከ ሊቃውንት፤
ደራሲ፤
የመጽሐፍ መምህር፤ (ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ)
ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ)፤
ጥዑመ ልሳን፤
የሱራፌል አምሳያ፤
የቤተ ክርስቲያን እንዚራ፤
የቤተ ክርስቲያን ብርሃን፤
የቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ
ካህን (ካህነ ስብሐት)
መዓርዒረ ዜማ፤
ማኅሌታይ፤
መዘምር ዘበድርሳን፤
ልዑለ ስብከት፤
ሰማዕት፤
ባሕታዊ፤
መናኝ
የዜማ አባት፤
በየኢትዮጵያ ብርሃን፡፡ ..
የሚታወቁት ድርሠቶቹ፤
1ኛ) ምዕራፍ (ውዳሴ ማርያም በዜማን፣ መስተጋብዕ፣ አርባዕት፣ አርያም፣ ሠለስት፣ ክስተተ አርያምን) ያጠቃለለ
የውዳሴ ማርያም ዜማው ልብን የሚመስጥ፤
መስተጋብዕ፤ ስብስብ ማለት ሲኾን፡፡ ከዳዊት መዝሙር (ከ180ው የመስተጋብእ ድርሰት 1ድ ድርሰት በስተቀር) ለጸሎትና ለዝማሬ ተስማሚ የኾነው እየተውጣጣ ለመዝሙር ተስማሚ የኾነው የተቀመረ ነው፡፡ መስተጋብዕ ሲጀምር ‹‹ወለቡ ጽራኅየ (ጩኸቴን ልብ አድርግ›› ብሎ ነው፡፡ በዐቢይ ጾም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ጠዋት ይዘመራል፤ የቀድሞ መምህራን በፍልሠታም ይዘምሩት ነበር፤ ዜማው በዋነኛነት በግዕዝና በዕዝል ሲኾን በአራራይ ከሐሙስ ‹‹አንተሰ እግዚኦ ለዓለም›› የሚለውና ከቅማዴ ‹‹መንግሠትከሰ መንግሥት›› የሚለው ይገኙበታል፡፡ በየእለቱ እንዲደርስ (ከእሑድ በስተቀር) አድርጎ የደረሰው ነው፤
አርባዕት፤ አራት አራተኛ ማለት ሲን በዳዊት መዝሙር በአራተኛው መሥመር ውስጥ እየገባ የሚዘመር ነው፤ ‹‹ቃልየ አጽምእ እግዚኦ ወለቡ ጽራኅየ፤ ወአጽምአኒ ቃለ ስእለትየ፤ ንጉሥየኒ ወአምላኪየኒ፡፡ ከፈጸመ በኋላ አርባዕት ይገባል፡፡ አርባዕት ሲጀመር ‹‹ቃልየ፤ ከመ ያፈቅርለ ጐሥዓ፤ ዐቢይ፤ ተሣሃለኒ›› ብሎ ነው (በዳዊት መዝሙር ጀምሮ ቀጥሎ በቅዱስ ያሬድ ድርሠት በኾነው በአርባዕት ያጠናቅቃል፡፡አብዛኛው በግጥም መልክ የተቀመረ ሲኾን አልፎ አልፎም በስድ ንባብ መልክ ይገኛል፡፡ ግእዝ ዕዝልና አራራይ ዜማ አለው፡፡
አርያም፤ አርያም ልዑል፥ ከፍተኛ ማለት ሲኾን፤ ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ሰምቶ ‹‹ቀዳሚ ዜማ፤ አንድም ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ›› ስላመጣው ነው፡፡ ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብሎ የግጥም መል ባለው አእያም በተባለው ይጀምራል፡፡ በግጥም መልክና በስድ ንባብ ሲገኝ የግጠም አገጣጠሙ ከፍ ያለ የግጥም አገጣጠምን የተከተለነው፡፡ የሚባልበት ጊዜ በጾም ጊዜ በጾመ ድጓው እየገባ፣ በተለይ ደግሞ በክብረ በዓል ክሥተተ አርያም ሲደርስ ይዘመራል፡፡
ሠለስት፤ ስምዐኒ ብሎ የሚጀምር ባለ ብዙ ሃሌታ ያለው፤ በዳዊት መዝሙር በሦስተኛው መሥመር እየገባ የሚዘመር፤ አንድም 3 መዝሙሮች ብቻ የሚዘመሩለት ብዙውን ጊዜ በግጥም የሚቀርብ ሲኾን፤ ይኽ ዜማ የሚደርሰው በክብረ በዓላት ዋይዜማ፤ በስብሐተ ነግህ፣ በአርያም፣ በጾመ ድጓ ውሎ፣ በአርያም፣ በሰንበት፣ በፍትሐት ጊዜ ነው፡፡
ክስተተ አርያም፤ የሰማይ መከፈት ማለት ሲኾን በታላላቅ በዓል ቀን እንዲሁም ታላላቅ? ሰዎች ሲሞቱ የሚዘመር ነው፤ ክስተትን ቅዱስ ያሬድ ያዘጋጀው ከዳዊት መዝሙራት፥ ከጸሎተ ነቢያትና ከራሱም ጭምር ኀይለ ቃል ያላቸውን ባለሁለት መስመሮች ሐረግ በመውሰድ ሲኾን ዜማው እጅጉን ነፍስና ሥጋን፥ ልብንና ኅሊናን የሚመስጥ ነው፡፡
2ኛ) ጾመ ድጓ፤ በዐቢይ ጾም የሚባል ነው፡፡
3ኛ) ድጓ፤ በ4ት ክፍላተ ዘመናት የተቀመረ ነው፡፡
4ኛ) ዝማሬ፤ ቅዱስ ቊርባን ድርገት ሲወርድ ለቅዱስ ቊርባን ክብር የሚዘመር ነው፡፡
5ኛ) መዋሥዕት፤ ሰው ሥጋው ከነፍ ስትለይ ፍትሐት የሚደረግበት ጸሎት ነው፡፡
6ኛ) የ14ቱን ቅዳሴያት ዜማ
7ኛ) አንቀጸ ብርሃንን፤ ድርሠቱ ነው፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@wiseholyfathersአስተያየት ካላቹ በ
@Wisecomment_bot ይላኩልን