ሐዋዝን ይህን ያህል ማጥቃት ለምን አስፈለገ?
የጥያቄየ መልስ ግልጽ ነው፤ ሐዋዝ መመለሱ ለብዙዎች መመለስ በር ይከፍታል፤ ኦርቶዶክሳውያን ከቤተ ክርስቲያናቸው እንዳይወጡ ይረዳል፤ የክርስቶስን መንገድ በእውነት ለመኖር የሚፈልጉ ሁሉ ኦርቶዶክሳዊውን ክርስትና ማወቅ አለባቸው፤ ሐሰተኛ ትምህርት ራሱን እውነት አስመስሎ በማቅረብና እውነተኛውን መንገድ ለማጥፋት በመታገል እውነተኛ ሊሆን አይችልም፤ ፕሮቴስታንትነት ምዕራባውያን ክርስትናን የሚያጠፉበት፣ ጥንታዊነትን የሚያወድሙበት መንገድ ነው፤ ማንም ሰው ወደ ኦርቶዶክስ ክርስትና ሲመጣ ወደ ክርስቶስ እውነተኛ ትምህርት መምጣቱ ነው፤ ይህን ለመረዳት በቀላሉ ኦርቶዶክሳዊውን የክርስትና ትምህርት በጥንቃቄ ማጥናት እንጂ ፕሮቴስታንታዊውን መንገድ መከተል ምንም ጥቅም የለውም።
አሰግድ ስለ ሐዋዝ የተናገረውን ሰምቼ በጣም አዘንሁ፤ ምንም ላለማለት ወስኜም እስከ ዛሬ ዝም አልሁ፤ ነገር ግን ብዙ ፕሮቴስታንትና ግልገል ፕሮቴስታንት ተሐድሶዎች እንዲሁም አንዳንድ ኦርቶዶክስ ሰዎች የአሰግድን ንግግር ጤነኛ መልእክት አድርገው እንደወሰዱት ተመለከትሁ፤ አሰግድ ምን ያህል ክፉና ጨካኝ እንደሆነ ያየሁት በዚህ ንግግሩ ነው፤ ደግሞም በጣም ተናዷል፤ መናደዱን እጠብቃለሁ፤ ይህን ዐይነት ክፋት ግን አይበታለሁ ብየ አላሰብሁም።
የሐዋዝን መመለስ በሕልሙ ሲያየው የኖረ እውነት አድርጎ አቀረበው፤ ይህ እውነት ከሆነ ዛሬ ለምን ይበሳጫል? ተስፋ ቆርጦ የቆየ ስለሆነ ይህን እውነት መግለጥ ይበቃው ነበር። ሐዘኑ መንፈሳዊነት ካለበትስ በወንድምነት ብሎም ራሱን እንደ አባት በቆጠረበት መንፈሳዊ መንገድ ሰማሁት ያለውን ጉዳይ በጉባኤ ለማውራት ለምን ፈለገ? ለጉባኤው መግለጥ ካስፈለገስ ለምን አስቀረጸው? በሚዲያ መልቀቅና ይህን ያህል ርህቀት ሂዶ ሐዋዝን ማጥቃት ለምን ፈለገ? ሐዋዝ በጣም ቅን ሰው መሆኑን በጥቂቱ አውቃለሁ፤ አሰግድ ባደረገው ንግግር ውስጥ ክፋትና ንዴት እንጂ ምንም መንፈሳዊነት አላየሁበትም፤ ይህ ስሜት በእያንዳንዱ ንግግሩ ውስጥ ይሰማኝ ነበር። ሰምቼ ስጨርስም የቀረልኝ ስሜት ይህ ነው፤ ብዙ ቀናት ቆይቼ ሳስበውም ሌላ መልካም ነገር አላየሁበትም፤ እኔ በተሰማኝ ነገር ላይ ከሰዎች ጋር ተነጋግሬበታለሁ፤ የኔን ስሜት ማጋራትና አስተያየት መስማት ፈልጌ ይህን ጻፍሁ፤ የኔ ስሜት ስሕተት ሆኖ አሰግድ እውነተኛ መንፈሳዊ አዛኝ ሰው ቢሆን ደስ ይለኛል፤ የኔ ስሜትና ስጋት እውነት ከሆነ ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንድነት ለመመለስ የምትታገሉ ወንድሞችና እኅቶች ተጠንቀቁ፤ በጣም አስቸጋሪ ፈተናን ትጋፈጣላችሁና እግዚአብሔር ያጽናችሁ!
(መጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር)
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖