🌹
ጣ ዕ ም ፡ የ ሌ ለ ው ፡ ስ ብ ከ ት
ወደ ከተማችን አንድ ሰባኪ ሊሰብክ መጣ ፣ የመጣው ለመስበክ ፈልጎ አልነበረም እኛን ለማዳን ጉጉት አድሮበት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ሊያሰማን ጓጉቶ አልነበረም በግድ ተገፍትሮ ፣ ተተፍቶ ፣ ተወርውሮ የመጣ ዓይነት ሰው ነበር ፡፡
ወደ መሃል ከተማም አልገባም የከተማችን አንድ ሦስተኛውን ብቻ ከተጓዘ በኋላ ስብከቱን ጀመረ የሰበከው ስብከት ሰላምታ የለውም ፣ መግቢያ የለውም ፣ መውጫም የለውም ፣ ማጽናኛም የለውም ‹ ንስሓ ግቡ › የሚል አዋጅ የለውም በጩኸት የተናገረው አንድ አስደንጋጭ ዐረፍተ ነገር ብቻ ነበር ‹‹ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች !! ›› ከነነዌ ነዋሪዎች አንዱ የነነዌን ታሪክ ቢጽፈው የሚጽፈው እንዲህ ነበር ፡፡
የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ናቸው ዮናስ ደግሞ እነርሱ የማያውቁትን አምላክ የሚያመልክ ነቢይ ነው ዮናስ ወደ እነርሱ የመጣው የማዳን ተልዕኮ ይዞ አልነበረም ፡፡
ወደ አሕዛብ መላኩ አላስደሰተውም ዮናስ ወደ ነነዌ የመጣው እንደ ሌላ ሰባኪ በየትኛውም ትራንስፖርት ተጉዞ ሳይሆን በዓሣ አንበሪ ወደ ነነዌ ተተፍቶ ነው ፡፡
የተተፋ ሰባኪ እንዴት ደስ ብሎት ይሰብካል ? እንኳን ስብከት ይቅርና ማንኛውም ሥራ ያለ ፍላጎት እንዴት ሊሳካ ይችላል ? ዮናስ የነነዌ ሕዝብ እንዲድን ፍላጎትም አልነበረውም እንዲያውም ከመጀመሪያውም ፍርሃቱ ‹ ትጠፋላችሁ › ብሎ ተናግሮ ሳይጠፉ ቢቀሩስ የሚል ነበር ፡፡
ዮናስ ወደ ከተማይቱ ዘልቆ ሲገባም በፍላጎት አልሰበከም ፤ የሰበከው ስብከት ተስፋ የሚያስቆርጥ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ነበር የነነዌ ሰዎች የማያውቁትን አምላክ እንዲያውቁ ዕድል የሚሰጥ ትምህርት አልተሠጣቸውም ፡፡
ዮናስም እንደ ኖኅ ‹ ይኼንን ያህል ዘመን ተሠጥቷችኋል ተመለሱ › ብሎ አልሰበከም መርከብ ሠርቶ ግቡም አላላቸውም በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች › ብሎ ጮኸ ፡፡
የነነዌ ሰዎች ግን ( ማን ነው የሚገለብጣት ? › ለምን ትገለበጣለች ? › ‹ ለመሆኑ አንተ ማን ነህ ? › ( ዝም ብሎ ትገለበጣላችሁ ይባላል ? መጀመሪያ ትምህርት አይቀድምም ? › አላሉም ፡፡
ራሳቸውን እንጂ ሰባኪውንና ስብከቱን ለመገምገም ጊዜ አልነበራቸውም፡ ‹‹ እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ ››
አንድ ላይ ኃጢአት መሥራት ቀላል ነው ፤ አንድ ላይ ንስሓ መግባት ግን ይከብዳል በሀገር ደረጃ ንስሓ መግባት ግን እጅግ ያስደንቃል የነነዌ ሀገር ህዝቦች ሀገር የምትገለበጥ ከሆነ ሀገር እንቀይር › አላሉም ፤ ራሳቸውን መቀየር እንደሚሻል ተረድተው ነበር ሁሉም እኩል ልቡ ተሰበረ ፤ ሁሉም ማቅ ለበሰ ፡፡
የሰባኪው ስብከት ጣዕም የለውም ብለው አላማረሩም ፣ ‹ ተስፋ የሚሠጥ ስብከት መቼ ሰማን › አላሉም ሰባኪው እያዋዛ አላስተማራቸውም ፣ ምሳሌ አልነገራቸውም ፣ ቅኔ አልተቀኘላቸውም
ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ‹‹ የተላከላቸው ጨካኝ ሐኪም ነበር የያዘው መድኃኒትም የሚያቃጥል ነበር ፤ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ቃል ተናገራቸው ፤ እነርሱ ግን አቁስሏቸው ተፈወሱ ›› የነነዌ ሰዎች ንስሓ ከላይ እስከታች ነበር ነገሥታቱ ሳይቀር ማቅ ለበሱ ‹‹ ነነዌ ትገለበጣለች ›› ብሎ ሲናገር ንጉሡ ወታደሮች ልኮ ዮናስን ማሰር ይችል ነበር ፡፡ ‹‹ ምን በሀገራችን ላይ ታሟርታለህ ? ›› ብለው_አፉን አላፈኑትም ።
መፍትሔውን ንገረን ያለውም የለም ችግሩ እነርሱ ናቸውና መፍትሔውንም ያውቁታል ስለዚህ ራሳቸውን መውቀስ ወደዱ ሀገሪቱ በአንድ ልብ አለቀሰች።
ንጉሡ ፡- ሰዎችና እንስሶች አንዳች አይቅመሱ ! ብሎ አዋጅ አስነገረ ከቤተ መንግሥት ጾም የሚታወጅባት ነነዌ እንዴት የታደለች ናት ? ‹‹ መኳንንቶችሽ ማልደው የሚበሉ አገር ሆይ ወዮልሽ ›› ተብሎ ከተጻፈ መኳንንቶችዋ የሚጾሙላት ሀገር እንዴት የታደለች ትሆን ? ( መክ . 10 ፡ 16 )
መቼም ሕዝብ ብቻ መጾሙ ነገሥታት ቢበሉ የተለመደ ነው ነገር ግን እየበሉ የሚጾምን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል ? ሲጠጡ እያደሩስ ሲጸልይ የሚያድርን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል ?
ንጉሥሽ ላንቺ ማቅ ለብሶ ያለቀሰልሽ ፣ እንስሳት ሳይቀር የጾሙልሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ ? ሕዝብሽ ጾም ሲታወጅ የማያላግጡ ፣ ‹ እኔ በፈለግሁበት ጊዜ ነው የምጾመው › ብለው የማይመጻደቁ ፣ እንኳን ከቤተ ክህነት ይቅርና ከቤተ መንግሥት የታወጀን ጾም በትሕትና የሚጾሙብሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ ? የዋሐን ሕጻናትን ጡት ከልክለው የፈጣሪን ርኅሩኅ ልብ የሚያስጨንቁ ፣ እንስሳትን ከውኃ ከልክለው ለምህላ የታጠቁ የነነዌ ሰዎች ምንኛ ድንቅ ናቸው ፡፡
ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የቤተ መንግሥቱን ሁኔታ እንዲህ ይሥለዋል ፡፡
‹‹ የነነዌ ንጉሥ ወታደሮቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸውም ፡- ይህ ድል እንደተጎናጸፍንባቸው ውጊያዎቻችን አይደለም ፤ ከባዕድ ሀገር በተሰማው ዜና ኃያላኖቻችን ሳይቀሩ ተብረክርከዋል ፤ አንድ ዕብራዊ መጥቶ በቃሉ አብረከረከን የጀግኖች እናት ነነዌ አንድን ለብቻው የመጣ ደካማ ሰው ቃል ፈርታለች ፡፡ስለዚህ ወገኖቼ ፤ የማይፈርስ አጥር እንገንባ ፤ ይህች አጥር ንስሓ ናት ፤ ሥውር ጦርነት ታውጆብናልና ራሳችንን ሥውር መሣሪያ እናድርግ !! ››
ዮናስ በነነዌ መመለስ ደስ አልተሰኘም ትንቢቱ ስለማይፈጸምለት ብቻ አይደለም ‹‹ የእስራኤል ሽማግሌዎች በሚቀማጠሉባት ሰዓት የነነዌ ሽማግሌዎች ሲያለቅሱ አየ ።
ጽዮን በዝሙት እንደ ሰም ስትቀልጥ ነነዌ ታነባ ነበር ›› እስራኤል ከፈጣሪ በራቁበት ሰዓት አሕዛብ የንስሓ ዕንባ ሲታጠቡ ሲያይ ክብር ከእስራኤል መልቀቁን አይቶ ተከፋ ፡፡
ዮናስ እስከመጨረሻው ሰዓት የነነዌን መጥፋት ይጠባበቅ ነበር ዮናስ ነነዌ የምትገለበጥበትን ቀን ሲቆጥር ነነዌ ደግሞ ኃጢአትዋን ትቆጥር ነበር ፡፡
ዮናስ ስለ ነነዌ እንደ ሙሴ ‹ እነርሱን ከምታጠፋ እኔን አጥፋኝ › አላለም ፤ በተቃራኒው ‹ እነርሱን ካላጠፋህ እኔን አጥፋኝ › እስከማለት ደረሰ በእርግጥም ዮናስ በሽተኛ አክሞ ስለዳነለት የሚበሳጭ ሐኪም ሆነ ፡፡
የነነዌ ሰዎች ግን የሰባኪው ማንነት ፣ የስብከቱ ውበት አልባነት ፣ የአነጋገሩ ለዛ ምክንያት ሳይሆናቸው ተስፋ በማይሰጥ ስብከት ተሰብረው ራሳቸውን አዳኑ ፡፡
ብዙ ስብከት አልፈለጉም ፤ ክፋትን ለመተው እ.ና ይቅር በለን ለማለት የተሰበረ ልብ እንጂ በእውቀት መሞላት አያስፈልግም የኛ ኃጢአታችን ደግሞ ከነነዌ ሰዎች ከበለጠ ቆየ የጋራ ክፋታችንን በጋራ ንስሓ እንጠበው።
📖 የኤፍራጥስ ወንዝ መጽሐፍ
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.