Forward from: Bekele Ejeta
ቫ ቲ ካ ን
━🇻🇦━
➥ አንዲት ሀገር እንዳለች ሙሉ በሙሉ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዝግባለች። ይህች ሙሉ ይዘቷ በዩኑስኮ ቅርስነት የተመዘገበው ሉዓላዊት ሀገር ቫቲካን ናት።
➥ ቫቲካን የዓለማችን ትንሿ ሀገር ስትሆን የቆዳ ስፋቷ 44 ሔክታር ነው። በቆዳ ስፋት ትንሽ ሀገር ብትመስልም በዓለማችን ላይ ቁጥር አንድ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር ናት።
➥ የህዝቧ ብዛት 932 ብቻ ሲሆን ያላት የባቡር ሀዲድ ርዝመት 890 ሜትር ብቻ ነው።
➥ ምንም ዓይነት ደን እና የእርሻ ምርት፣ መሥሪያ ቤት እንዲሁም ምንም የፖለቲካ ፓርቲ የሌላት ብቸኛ ሉዓላዊት ሀገር ቫቲካን ናት።
➥ ቫቲካን ከካርበን የአየር ብክለት ፍፁም የጸዳች ሀገርም ነች።
➥ የቫቲካን ሙዚየም 14.5 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ሲሆን በሙዚየሙ ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ቅርስ ለአንድ ደቂቃ እያየን ብናልፍ በአጠቃላይ ሙዚየሙን አይቶ ለመጨረስ የሚፈጀው ጊዜ 4 ዓመት ነው! ሙዚየሙ ከቫቲካን ድንበር አልፎ እስከ ሮማ ይዘረጋል።
➥ ቫቲካን በሮማ መሀል የምትገኝ የጣልያን ምድር ብትሆንም ለየት ባለ ሁኔታ ራሷን የቻለች ሉዓላዊት ሀገር ናት። የሮማ ካቶሊክ ሊቀ-ጳጳስ መቀመጫ የሆነችው ቫቲካን ራሷን ችላ እንድትተዳደር የተወሰነው በ1929 ዓ.ም. ነው።
➥ ጣልያናዊ ዜግነት ያላቸው ሁሉ ከገቢያቸው ላይ 8% ለቫቲካን መንግሥት ይለግሳሉ።
➥ ቫቲካን የኢኮኖሚ መሰረቷ ከመላው ዓለም የካቶሊክ እምነት ተከታዮች በሚሰጠው አስራት፣ መባ እና ስጦታ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች የገቢ ምንጮቿ ህትመት፣ ፖስታ፣ ቴምብር፣ የጥንታዊ ሳንቲሞች ሽያጭ እና ቱሪዝም ናቸው።
➥ ቫቲካን የምትተዳደረው በንጉሠ ነገሥታዊ ሥርዓት-መንግሥት ነው። ንግሥናው ግን በዘር የሚወረስ አይደለም። የንግሥናው ምንጭ የሮማ ሊቀ-ጳጳስ መሆን ነው። የካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ሊቀ-ጳጳስ የቫቲካን ንጉሥ ናቸው።
➥ በቫቲካን የሊቀ-ጳጳሱ ጠባቂ ለመሆን የስዊዘርላንድ ዜጋ መሆን ያስፈልጋል።
➥ 100% ወይም ሙሉ ለሙሉ ከተማ የሆነች ሉዓላዊት ሀገር ቫቲካን ብቻ ናት።
➥ ከቫቲካን ሲቲ በመቀጠል የዓለማችን ትንንሽ ሉዓላዊ ሀገራት ሞናኮ፣ ናሁሩ፣ ቱቫሉ፣ ሳንማሪኖ፣ ሊቸንስቴን፣ ሴንትኪትስ፣ ማልዳይቭ፣ ማልታ እና ግሪናዳ ናቸው።
━━━━━━━━
ምንጭ ➢ የዕውቀት ማኅደር