ጠባቂሽ. . .
ደህና ነች
ዛሬም እንደፊቱ ደምቃለች ፈክታለች!
የውበት አምባ ጥግ የሄዋን ተምሳሌት
የመዋደድ ጣዖት የፍቅር አማልክት
አንቺ...
አንቺ በመውደድ ጥምዝምዝ አስረሽ የማትፈቺ
የአይኖቼ ጥም ሀሩር የማትሰለቺ
እስቲ እንደው ገምቺ...
እስቲ እንደው ገምቺ ...
እንዴት ባለ ምትሀት እንዴት ባለ ታምር
የሰው ቀልብ አርፎብኝ እንደዛ የማምር
የእውቀቶች ባለቤት ባለብዙ ተስፋ
አይሽ እንደሁ ብዬ ሰርክ የምለፋ
ዛሬ እንዴት እንደሆንኩ የሸርፍ ተራ ሰው.
ሌላ ምንም አይደል
ውለሽ ስትገቢ ባይኔ እንድታልፊ ነው
ከሸርፍ ተራው ጥግ እጠብሻለሁ
የሰው ብትሆኚም ዛሬም አይሻለሁ
ዛሬም ደህና ነሽ.. ዛሬም አምሮብሻል
ህይወት ቀንታሻለች ወልደሻል ከብደሻል
ጊዜ አልለወጠሽ እድሜ አልወጠነሽ
ማሻላህ ደህናነሽ
የዘመን ባዘቶ መች ይቀይርሻል
ወላሂ አምሮብሻል
ሳታውቂው ማፍቀሬን እስከመፈጠሬም
አልሃምዱሊላህ ትስቂያለሽ ዛሬም
ገርጅፎ ያልጃጀ በፍቅር ያሳደገሽ
በልጅነት ልቡ ወዶ የፈለገሽ
መስዋዕት ሳያሻው ራሱን የከፈለሽ
ተርቦ ማይጠግብ ድብቅ ፍቅር እንዳለሽ
እንኳን ስሜን መልኬን አንቺ መች ታውቂያለሽ..
ብቻ... ምንም ቢሆን
ህመሜ ተሰምቶሽ ልምጣ ያልሽ እንደሆን
እንደጠዋት ጀምበር ዘወትር ናፋቂሽ
የማታውቂው እውነት የፍቅር ደባቂሽ
ካስቀመጥሺኝ ቦታ አለሁኝ ጠባቂሽ
✍ኤልሳ[FB]
JOIN 👉👉👉 @Fkerofficial
@yegetemkalat
@poem_merry
ደህና ነች
ዛሬም እንደፊቱ ደምቃለች ፈክታለች!
የውበት አምባ ጥግ የሄዋን ተምሳሌት
የመዋደድ ጣዖት የፍቅር አማልክት
አንቺ...
አንቺ በመውደድ ጥምዝምዝ አስረሽ የማትፈቺ
የአይኖቼ ጥም ሀሩር የማትሰለቺ
እስቲ እንደው ገምቺ...
እስቲ እንደው ገምቺ ...
እንዴት ባለ ምትሀት እንዴት ባለ ታምር
የሰው ቀልብ አርፎብኝ እንደዛ የማምር
የእውቀቶች ባለቤት ባለብዙ ተስፋ
አይሽ እንደሁ ብዬ ሰርክ የምለፋ
ዛሬ እንዴት እንደሆንኩ የሸርፍ ተራ ሰው.
ሌላ ምንም አይደል
ውለሽ ስትገቢ ባይኔ እንድታልፊ ነው
ከሸርፍ ተራው ጥግ እጠብሻለሁ
የሰው ብትሆኚም ዛሬም አይሻለሁ
ዛሬም ደህና ነሽ.. ዛሬም አምሮብሻል
ህይወት ቀንታሻለች ወልደሻል ከብደሻል
ጊዜ አልለወጠሽ እድሜ አልወጠነሽ
ማሻላህ ደህናነሽ
የዘመን ባዘቶ መች ይቀይርሻል
ወላሂ አምሮብሻል
ሳታውቂው ማፍቀሬን እስከመፈጠሬም
አልሃምዱሊላህ ትስቂያለሽ ዛሬም
ገርጅፎ ያልጃጀ በፍቅር ያሳደገሽ
በልጅነት ልቡ ወዶ የፈለገሽ
መስዋዕት ሳያሻው ራሱን የከፈለሽ
ተርቦ ማይጠግብ ድብቅ ፍቅር እንዳለሽ
እንኳን ስሜን መልኬን አንቺ መች ታውቂያለሽ..
ብቻ... ምንም ቢሆን
ህመሜ ተሰምቶሽ ልምጣ ያልሽ እንደሆን
እንደጠዋት ጀምበር ዘወትር ናፋቂሽ
የማታውቂው እውነት የፍቅር ደባቂሽ
ካስቀመጥሺኝ ቦታ አለሁኝ ጠባቂሽ
✍ኤልሳ[FB]
JOIN 👉👉👉 @Fkerofficial
@yegetemkalat
@poem_merry