የዘመኑ ይሁዳ
ከዘመናት በፊት ሞተ የተባለው
እያቀፈ ስሞ አምላኩን የሸጠው
ያ ለሰላሳ ዲናር ነብሱን የዘነጋ
ይሁዳ አልሞተም አለ ይኸው እኛ ጋ
የሞተ ቢመስለን እንዲያው ያበቃለት
ተቀቶ የሚኖር ሲኦል ባለው እሳት
የሞተው እሱ ነው ሀሳቡ ተላልፏል
የዘመኑ ይሁዳም ስራውን ጀምሯል
ተዋህዶ ማለት የሀገር ምሰሶ ናት
በሀገር ያለው ሁሉ ህዝቡ የሚያከብራት
ብሎ በአንደበቱ ሲደሰኩር ኖሮ
ወንበሩ ሲመቸው ፈጠረ አምባጓሮ
ይከፋፈል አለ ሀይማኖት እንደ ቅርጫ
በብሄር በጎሳ ይሁን መጫወቻ
አንደበቱ አራምባ ተግባሩ ቆቦ ነው
በቅቤ ምላሱ ህዝቡን አታለለው
ተደመር እያለ አካፍሎ ገደለው
ማህተብ አልፈታ ያለውን በሙሉ
በጥይት በክላሽ ሲያበቃ ዘመኑ
ድምፁን ሰቶ ሁሉ እሱ ይምራን ባለው
ልምራህ እኔ ብሎ ከአፈር ደባለቀው
ይለያል መንገዱ አያስጠረጥርም
ጉንጭኮ አደለም ይኸኛው ይሁዳ እግር ነው የሚስም
አጎንብሶ ሲስም መስሎን ያከበረ
ሲተበትብ ቆየ መጥለፊያ እያሰረ
ሁሉንም ለመናድ ከስር መሰረቱ
ቢገፋ ቢገድል ቢሆንብን ብርቱ
ማህተብ አንበጥስ ለአህዛብ አንገዛ
ሲገፋን ሲገሉን ነንኮ የምንበዛ
ንገሩት ለዛ ሰው ለዘመኑ ይሁዳ
ፈገግ ብሎ ስሞ ሀገሩን ለከዳ
እንደው ላይቻለው ተዋህዶን ሊያጠፋ
ሰራዊት በመላክ በመግደል አይልፋ
ፀንታ የምትኖር ነች ዘላለም በእምነት
በምድራዊ ሀይል የማትፈርስ አለት
✍ቤዛዊትድሪባ
(የተክልዬዋ)
@yegetemkalat
@poem_merry
ከዘመናት በፊት ሞተ የተባለው
እያቀፈ ስሞ አምላኩን የሸጠው
ያ ለሰላሳ ዲናር ነብሱን የዘነጋ
ይሁዳ አልሞተም አለ ይኸው እኛ ጋ
የሞተ ቢመስለን እንዲያው ያበቃለት
ተቀቶ የሚኖር ሲኦል ባለው እሳት
የሞተው እሱ ነው ሀሳቡ ተላልፏል
የዘመኑ ይሁዳም ስራውን ጀምሯል
ተዋህዶ ማለት የሀገር ምሰሶ ናት
በሀገር ያለው ሁሉ ህዝቡ የሚያከብራት
ብሎ በአንደበቱ ሲደሰኩር ኖሮ
ወንበሩ ሲመቸው ፈጠረ አምባጓሮ
ይከፋፈል አለ ሀይማኖት እንደ ቅርጫ
በብሄር በጎሳ ይሁን መጫወቻ
አንደበቱ አራምባ ተግባሩ ቆቦ ነው
በቅቤ ምላሱ ህዝቡን አታለለው
ተደመር እያለ አካፍሎ ገደለው
ማህተብ አልፈታ ያለውን በሙሉ
በጥይት በክላሽ ሲያበቃ ዘመኑ
ድምፁን ሰቶ ሁሉ እሱ ይምራን ባለው
ልምራህ እኔ ብሎ ከአፈር ደባለቀው
ይለያል መንገዱ አያስጠረጥርም
ጉንጭኮ አደለም ይኸኛው ይሁዳ እግር ነው የሚስም
አጎንብሶ ሲስም መስሎን ያከበረ
ሲተበትብ ቆየ መጥለፊያ እያሰረ
ሁሉንም ለመናድ ከስር መሰረቱ
ቢገፋ ቢገድል ቢሆንብን ብርቱ
ማህተብ አንበጥስ ለአህዛብ አንገዛ
ሲገፋን ሲገሉን ነንኮ የምንበዛ
ንገሩት ለዛ ሰው ለዘመኑ ይሁዳ
ፈገግ ብሎ ስሞ ሀገሩን ለከዳ
እንደው ላይቻለው ተዋህዶን ሊያጠፋ
ሰራዊት በመላክ በመግደል አይልፋ
ፀንታ የምትኖር ነች ዘላለም በእምነት
በምድራዊ ሀይል የማትፈርስ አለት
✍ቤዛዊትድሪባ
(የተክልዬዋ)
@yegetemkalat
@poem_merry