ስለረዳሽኝ እመቤቴ አወድስሻለሁ
ከኔጋር ስለሆንሽ እመቤቴ አወድስሻለሁ
ምስጋናሽን ይዤ ጠዋት ማታ ፊትሽ እቆማለሁ
ምስጋናሽን ይዤ እመቤቴ ፊትሽ እቆማለሁ /፪
ሀዘን ትካዜዬ ባንቺ ተወግዷል
ልመና ፀሎቴ ሀሳቤ ተሟልቷል
ያጣሁትን ሁሉ አግኝቼብሻለሁ
በእናትነትሽ ዘወትር እመልካለሁ
አዝ....
ባንቺ ደስ ይለኛል ያርፋል ልቦናዬ
ሰዓሊ ለነ ብዬ ተቃና ጉዞዬ
አልፈራም እንግዲህ ገደል እንቅፋቱን
ይዘሽኛልና ድንግል አዛኝቱ
አዝ....
የተስፋ መብራቴ አትጠፊም ከፊቴ
መድኃኒቴ አንቺ ነሽ ለብቸኝነቴ
ይች አለም ብትከፋ ፊቷን ብትመልስ
ጨክነሽ አታውቂም እናቴ በኔስ
አዝ....
ምስክር አልሻም ከእንግዲህ በኃላ
ነብሴ ትጮሀለች አማላጄ ብላ
አወድስሻለሁ እናቴ እመቤቴ
በኑሮዬ ሁሉ እስከለተ ሞቴ
አዝ....
መዝሙሩን ሊንኩን በመጫን ያድምጡ
https://youtu.be/RjqKbJ4Ej84
https://youtu.be/RjqKbJ4Ej84
የእመቤታችን ምልጃ ቃልኪዳን ከሁላችን ጋር ይሁን
መልካም እለተ ሰንበት!
ሰብስክራይብ ሼር...........
ከኔጋር ስለሆንሽ እመቤቴ አወድስሻለሁ
ምስጋናሽን ይዤ ጠዋት ማታ ፊትሽ እቆማለሁ
ምስጋናሽን ይዤ እመቤቴ ፊትሽ እቆማለሁ /፪
ሀዘን ትካዜዬ ባንቺ ተወግዷል
ልመና ፀሎቴ ሀሳቤ ተሟልቷል
ያጣሁትን ሁሉ አግኝቼብሻለሁ
በእናትነትሽ ዘወትር እመልካለሁ
አዝ....
ባንቺ ደስ ይለኛል ያርፋል ልቦናዬ
ሰዓሊ ለነ ብዬ ተቃና ጉዞዬ
አልፈራም እንግዲህ ገደል እንቅፋቱን
ይዘሽኛልና ድንግል አዛኝቱ
አዝ....
የተስፋ መብራቴ አትጠፊም ከፊቴ
መድኃኒቴ አንቺ ነሽ ለብቸኝነቴ
ይች አለም ብትከፋ ፊቷን ብትመልስ
ጨክነሽ አታውቂም እናቴ በኔስ
አዝ....
ምስክር አልሻም ከእንግዲህ በኃላ
ነብሴ ትጮሀለች አማላጄ ብላ
አወድስሻለሁ እናቴ እመቤቴ
በኑሮዬ ሁሉ እስከለተ ሞቴ
አዝ....
መዝሙሩን ሊንኩን በመጫን ያድምጡ
https://youtu.be/RjqKbJ4Ej84
https://youtu.be/RjqKbJ4Ej84
የእመቤታችን ምልጃ ቃልኪዳን ከሁላችን ጋር ይሁን
መልካም እለተ ሰንበት!
ሰብስክራይብ ሼር...........