ንጹህ ፍቅር
“የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው” (1ጢሞ. 1፡5)፡፡
ንጹህ ፍቅር አንድን ነገር ስናደርግ ካለን የመነሻ አሳብና እንዲሁም ከምናደርገው ተግባር አንጻር የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ፣ ንጹህ ፍቅር በአንድ ጎኑ አንድን ነገር ስናደርግ ያደረግንበት ምክንያት ንጹህ የመሆኑ ጉዳይ ይነካል፡- “ፍቅር በባልንጀራው ላይ ክፉ አያደርግም፤ስለዚህ ፍቅር የሕግ መፈጸሚያ ነው” (ሮሜ 13:10)፡፡
በሌላ ጎኑ ደግሞ ምንም እንኳን በውስጣችን ፍቅር እንዳለ ብንናገርና መነሻ ሃሳባችን ንጹህ ቢሆንም ንጹህ ፍቅር በመልካም ተግባር ይገለጣል፡- “ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ” (1ዮሐ. 3:18)፡፡
የግሪኩን ጽሑፍ በሚገባ የሚገነዘቡ የስነ-መለኮት አስተማሪዎች የተለያዩ የፍቅር ገጽታዎች እንዳሉ ያስተምሩናል፡፡
1) ስቶርጌ (Storge) - የቤተሰብ ፍቅር ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ወላጆች ለቤተሰባቸው ያላቸውን ፍቅር ያሳያል፡፡
2) ኢሮስ (Eros) - በተለያዩ ጾታ መካከል ያለ ፍቅር ነው፡፡ በሰው ላይ ከምናየው ውብ ነገር ከመነሳት የሚኖረንን ፍቅር ያሳያል፡፡
3) ፊሊዮ (Philio) - የጓደኝነት ፍቅር ነው፡፡ ሰውን በፍጹም ጓደኝነት ስንወደው የሚኖረንን ፍቅር ያሳያል፡፡
4) አጋፔ (Agape) - ሰውን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ የምንወድበት ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛንና ዓለምን የወደደበትን ፍቅር ያሳያል፡፡ እኛም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ የተባልንበት ፍቅር ነው፡፡
ቃሉ፣ “የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ማንም የለም” (ኤፌ. 5፡2) ስለሚል አንድ ሰው ለራሱ የሚኖረውን ፍቅር አልፈን ስንሄድ፣ ሶስት አይነት የአጋፔ የፍቅር መገለጫዎችን እንደመለከታለን፡፡
1. እግዚአብሔርን መውደድ
“ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ” (ማቴ. 22፡37)፡፡
ቃሉ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር በምንም የእንካ-በእንካ ላይ ያልተመሰረተና ንጹህ እንዲሆን ይመክረናል፡፡ ጌታን ለመውደድ ምንም ሌላ ምክንያት አያስፈልገንም፤ “እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን” (1ዮሐ. 4፡19)፡፡
2. ባልንጀራን መውደድ
“ባልንጀራህን … ውደድ” (ማቴ. 22፡39)፡፡
ለእግዚአብሔር ያን ንጹህ ፍቅር የሚታወቀው አጠገባችን ላለው ወገናችን በምናሳየው ፍቅር ነው፡፡ “ማንም፣ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን መውደድ አይችልምና” (1ዮሐ. 4፡20)፡፡
3. ጠላትን መውደድ
“ጠላቶቻችሁንውደዱ” (ማቴ. 5፡44)፡፡
“የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከእርሱ ጋር ከታረቅን” (ሮሜ 5፡10) እና በንጹህ ፍቅር ከተወደድን እኛም ይህንን ፈለግ በመከተል ጠላቶቻችንን በይቅርታ በመቀበል ልንወድ እንደሚገባን ክርስቶስ ምሳሌን ትቶልን አልፏል፡፡
የሚቀጥለው ትምህርት፡ “ንጹህ አምልኮ”