ራስን በትክክለኛ ሰዎች መክበብ
“ወንጌልን እንድሰብክ አደራ እንደተሰጠኝ ተገነዘቡ … እንደ አዕማድ የሚቈጠሩት ያዕቆብ፣ ጴጥሮስና ዮሐንስም፤ የተሰጠኝን ጸጋ ባስተዋሉ ጊዜ፣ለእኔና ለበርናባስ የትብብር ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤ ከዚያም እኛ ወደ አሕዛብ፣ እነርሱ ደግሞ ወደ አይሁድ እንድሄድ ተስማሙ። አጥብቀው ዐደራ ያሉን ድኾችን ማሰባችንን እንዳናቋርጥ ብቻ ነው፤ እኔም ይህንኑ ለማድረግ ጒጒቴ ነበር” (ገላ. 2፡7-10)፡፡
በአጠገባችን የሚገኙት የቅርብ ወዳጆቻችን ሁለት ነገሮችን ይጠቁሙናል፡፡ በመጀመሪያ፣ እነዚያን ሰዎች የቅርብ ወዳጅ ያደረግንበት ምክንያት ቀድሞውኑ ያለንበትን አመለካከት ደረጃ ሲጠቁመን፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ እነዚህ ያቀረብናቸው ሰዎች የራሳቸው አመለካከት ይዘው ወደእኛ ስለሚመጡ ለዚያ ተጽእኖ ራሳችንን የማቅረባችንን ሁኔታም ይጠቁማል፡፡ ይህ በቃሉም ሆነ በልምምዳችን የምናውቀው እውነት ነው፡፡
በሌላ አገላለጽ፣ የወዳጅ ምርጫችን ያለንን ቅድመ-አመለካከትና ለወደፊትም ያለንን ተጋላጭነት ጠቋሚ ነው፡፡ከላይ በጳውሎስ ሕይወት እንዳነበብነው፣ በአካባቢህ የሚገኙ ሰዎች የተሰጠህን ጸጋና በውስጥህ ያዘልከውን ራእይ ሲያዩና ሲሰሙ የሚያበረታቱህ አይነት ሰዎች የመሆናቸው ጉዳይ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡
ይህንን የማድረጉ ምርጫ ደግሞ በእጅህ ላይ ነው ይለው፡፡ ለምትከታተለው ራእይና ዓላማ የሚመጥንን ወዳጅነት የመምረጥ እድሉም፣ መብቱም ሆነ አቅሙ አለህ፡፡
ስለዚህ ወዳጅ ስትመርጥ የሚከተሉትን መስፈርቶች ተመልከት፡፡
1. ዓላማህን በሚገባ የተገነዘቡትን ምረጥ
“ወንጌልን እንድሰብክ አደራ እንደ ተሰጠኝ ተገነዘቡ”
በውስጥህ ያለውን ዓላማ አንተ በምታየውና በተገነዘብከው መጠን ሙሉ ለሙሉ የሚያውቁልህ ሰዎች ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ሆኖም ግን ያንን ለማድረግ ራሳቸውን ያቀረቡልህን ሰዎች በመለየትና የሕይወትህን ዓላማ ማካፈል መልካም ልምምድ ነው፡፡ ምናልባት ከዚህ በፊት ዓላማህን ከሰሙ በኋላ ለመደገፍ ያላቸው ፈቃደኝነት አናሳ የሆነ ሰዎች አጋጥመውህ ይሆናል፡፡ ሆኖም፣ የዓላማ ሰው ያለበትን ውጣ ውረድ በሚገባ የሚገነዘቡ ሰዎች እንዳሉም ማስታወስ ልቦናህን ይደግፈዋል፡፡
2. ከአንተ ደረጃ አለፍ ያሉትን ምረጥ
“እንደ አዕማድ የሚቈጠሩት ያዕቆብ፣ ጴጥሮስና ዮሐንስም”
ለእነ ጳውሎስ ቀኝ እጃቸውን የሰጡ ሶስቱ በሕይወታቸው የተመሰከረላቸው፣ እነሱ ካሉበት አንድ ደረጃ ከፍ ያለ ልምምድ ያላቸው ነበሩ፡፡ የበሰሉ ሰዎች ሌሎች መደገፍና ማበረታታትን ያውቃሉ፡፡ ከእኛ ደረጃ ከፍ ያሉ ሰዎች እነሱ ወደደረሱበት ደረጃ ይስቡናል፡፡ ሰዎች አሁን ካለንበት ደረጃ ደግፈውን ወደሚቀጥለው ደረጃ የማይወስዱን ስላልፈለጉ ብቻ ሳይሆን ስልቻሉም ጭምር ሊሆን ይችላል፡፡
3. ከአንተ ጋር የሚስማሙ፣ ነገር ግን በሃላፊነት የሚጠይቁህን ምረጥ
“እነርሱ ደግሞ ወደ አይሁድ እንድሄድ ተስማሙ … አጥብቀው ዐደራ ያሉን ድኾችን ማሰባችንን እንዳናቋርጥ ብቻ ነው፤እኔም ይህንኑ ለማድረግ ጒጒቴ ነበር”
በሁሉ ነገር የሚስማሙ ሰዎች ያጠፉሃል፣ በሁሉም ነገር የሚቃሙህ ሰዎች ደግሞ ከጉዞህ ይገቱሃል፡፡ ወዳጆችህን ስትመርጥ ዓላማህን በመደገፍ የሚስማሙ፣ ነገር ግን ሚዛናዊነትን ከአንተ የሚጠብቁ መሆናቸውን አረጋግጥ፡፡ የእነጳውሎስ መካሪዎች ምንም እንኳን ቢደግፏቸውም ከተሳሳተ መንገድ እንዲጠበቁ ማስጠንቀቂያና ምክርንም ለግሰዋቸው ነበር፡፡
የሚቀጥለው ትምህርት፡ “የየዕለት ልማዶችን ማዳበር”