⛽️የነዳጅ ጭማሪን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ:- ውድ የራይድ ቤተሰብ- በዛሬው እለት የነዳጅ ጭማሪ እንደተደረገ ተነግሯል:: ይህንን አስመልክቶ አባላት የራይድን ዋጋ ለመጨመር ወይም ባለበት ለማቆየት ከደንበኞች የመክፈል አቅም እይታ ሃሳባቸውን እየገለፁ ይገኛሉ:: በዚህም መሰረት ድርጅታችን የተገበረው የDynamic Pricing feature አማካኝነት የተደረገውን ጭማሪ እንደሚያካክስ እየገለፅን መደበኛ ታሪፋችን ባለበት እንደሚቆይ በአክብሮት እናሳውቃለን:: ይህም ማለት- እሩቅ የሆኑ ቦታዎች እና መመለሻ በማይገኝባቸው ቦታዎች ሲስተማችን ባየር ላይ ዋጋውን በ10% ወይም በ20% የሚያሳድግ ይሆናል:: መልካም በዓል ይሁንልዎ