ጣዕሙን የሚያውቀው
(ሳሙኤል አለሙ)
እንደ ሌላው
እንደ ሌላው፤
ሰርክ...
ጉንጭሽ ጋ አይደረስም
ረ------ጅም ነው ኬላው።
እያዩት...
ያስውላል።
ዕሮብ ለት
እያዩት...
ያፆማል።
አርብ ዕለት
እንደ እኛው
እንደ እኛው፤
አንቺ...
ከቶ አልተፈጠርሽም
በቀን ስድስተኛው።
ለምን...?
አይባልም።
አይጠየቅም።
እንዴት...?
አትለውም።
አትከራከርም።
ከአፈሩም ፣ ከውኃውም
ከእስትንፋሱም ፣ ሌላም
አለው... ሌላም...ሌላም
ሌላም አለው ያከለበት፤
ወተቱን እንዳ---
ፈሰሰ---
---በት
ጉንጭሽን የሳመው።
ጣዕሙን የሚያቀው።
@Samuelalemuu
(ሳሙኤል አለሙ)
እንደ ሌላው
እንደ ሌላው፤
ሰርክ...
ጉንጭሽ ጋ አይደረስም
ረ------ጅም ነው ኬላው።
እያዩት...
ያስውላል።
ዕሮብ ለት
እያዩት...
ያፆማል።
አርብ ዕለት
እንደ እኛው
እንደ እኛው፤
አንቺ...
ከቶ አልተፈጠርሽም
በቀን ስድስተኛው።
ለምን...?
አይባልም።
አይጠየቅም።
እንዴት...?
አትለውም።
አትከራከርም።
ከአፈሩም ፣ ከውኃውም
ከእስትንፋሱም ፣ ሌላም
አለው... ሌላም...ሌላም
ሌላም አለው ያከለበት፤
ወተቱን እንዳ---
ፈሰሰ---
---በት
ጉንጭሽን የሳመው።
ጣዕሙን የሚያቀው።
@Samuelalemuu