¹
ሳብኩት ንጋቴን
በመርሳት ልጓም
መርኋን ጣስኩኝ
ተሻረ ህጓም ።
ጣርኩኝ ለመርሳት
ስርጉዷን ሳቋን
ማማር መላቋን
ሓዘኗን ጭንቋን
ግልጧን ድብቋን
ቻልኩኝ መዘንጋት
ከሞት ግንባር ቆምኩ
ቀረብኩኝ በጋት ።
²
በማውሳት ብዛት
ከረሳሁ መልኳን
በካብኳት መጠን
ከናድኩት ልኳን ፣
ብዬ ብነሳም . . .
የመዳን ቆቤን
ከትውስታዋ . .
እልፍኝ ባስስም ፣
ኣልፈወስም ።
እኩል ያመኛል . . .
ስቆ ማለፍም
ቆሞ ማልቀስም ።
[ ሙሃመድ እድሪስ ]
@Samuelalemuu
ሳብኩት ንጋቴን
በመርሳት ልጓም
መርኋን ጣስኩኝ
ተሻረ ህጓም ።
ጣርኩኝ ለመርሳት
ስርጉዷን ሳቋን
ማማር መላቋን
ሓዘኗን ጭንቋን
ግልጧን ድብቋን
ቻልኩኝ መዘንጋት
ከሞት ግንባር ቆምኩ
ቀረብኩኝ በጋት ።
²
በማውሳት ብዛት
ከረሳሁ መልኳን
በካብኳት መጠን
ከናድኩት ልኳን ፣
ብዬ ብነሳም . . .
የመዳን ቆቤን
ከትውስታዋ . .
እልፍኝ ባስስም ፣
ኣልፈወስም ።
እኩል ያመኛል . . .
ስቆ ማለፍም
ቆሞ ማልቀስም ።
[ ሙሃመድ እድሪስ ]
@Samuelalemuu