የተዋበ መልክ የገዛኝ
የፍቅር ሰው ዘበ ፍጥረት
የኑር ብራ የጊዜ አለት
በወፍ ዜማ ተቃኝቼ
በተራራ ሜዳ ሰርጓጅ
ቀለም አልባ ውሃ ፍሳሽ
ከድጋይ ጋር ዜማ ምዋጅ
እንቡጥ ለጋ ኪዳነ ቃል
በምድር ልብ አጎንብሼ
እንደሰሌን የምነጠፍ
መጪ ሂያጁ የሚረግጠኝ
ወጭ ወራጁ የሚያጎብጠኝ
በእድሜ ቀላይ የምቀጠፍ
ሁሉ ገርፎ የሚያስጮኸኝ
ሁሉ ስቆ የሚያስቀኝ
ሁሉ ወድቆ ሚያስነክሰኝ
ከአፀዱ ስር አደግድጌ
ከሙሀባው ተጠምቄ
እንደአምላኬ ሆድ የባሰኝ
ከሰው ስጋ ተፈጥሬ
ከአፈር ብናኝ ተከልቄ
ሰው ፍለጋ ምንከራተት
ከተፈጥሮ ተዋድቄ
የመኖር ሀቅ የከውኑን ሲር
በአጭር ቋንቋ ላመሳጥር
ድቅድቅ መሀል የምታትር
ለቀን ፀሀይ ወፍ ዘምሮ ሳያበስረኝ
ዶሮ ቀድሞኝ ሳይኮሎኩል
ሻማ ኩራዝ አንጠፍጥፌ
ለሰው ንጋት የምቸኩል
ከትል ከዛፍ እውቀት ስሻ
ለአንድ እውነት ሰባት ግዜ የምባክን
ተቅበዝብዤ የማልጠፋ
ተናግሬ የማልሰክን
ከዲዳ ጋር የማወራ
ብጫቂ ጨርቅ ያልደለለኝ
ቀለም መርጦ ማይገድበኝ
ከእብድ ጋር የምዋልል
በአየሁት ላይ የምማልል
ፍቅር ልኩን የመገበኝ
ፆታዬን በነብሴ
ግብሬን በወድ ልክ አኗኗሬን በሴት
ያበቃው ያነቃው
ገጣሚ ነኝ የሰው ደሴት
[ አዲብ መሃመድ ]
@Samuelalemu
የፍቅር ሰው ዘበ ፍጥረት
የኑር ብራ የጊዜ አለት
በወፍ ዜማ ተቃኝቼ
በተራራ ሜዳ ሰርጓጅ
ቀለም አልባ ውሃ ፍሳሽ
ከድጋይ ጋር ዜማ ምዋጅ
እንቡጥ ለጋ ኪዳነ ቃል
በምድር ልብ አጎንብሼ
እንደሰሌን የምነጠፍ
መጪ ሂያጁ የሚረግጠኝ
ወጭ ወራጁ የሚያጎብጠኝ
በእድሜ ቀላይ የምቀጠፍ
ሁሉ ገርፎ የሚያስጮኸኝ
ሁሉ ስቆ የሚያስቀኝ
ሁሉ ወድቆ ሚያስነክሰኝ
ከአፀዱ ስር አደግድጌ
ከሙሀባው ተጠምቄ
እንደአምላኬ ሆድ የባሰኝ
ከሰው ስጋ ተፈጥሬ
ከአፈር ብናኝ ተከልቄ
ሰው ፍለጋ ምንከራተት
ከተፈጥሮ ተዋድቄ
የመኖር ሀቅ የከውኑን ሲር
በአጭር ቋንቋ ላመሳጥር
ድቅድቅ መሀል የምታትር
ለቀን ፀሀይ ወፍ ዘምሮ ሳያበስረኝ
ዶሮ ቀድሞኝ ሳይኮሎኩል
ሻማ ኩራዝ አንጠፍጥፌ
ለሰው ንጋት የምቸኩል
ከትል ከዛፍ እውቀት ስሻ
ለአንድ እውነት ሰባት ግዜ የምባክን
ተቅበዝብዤ የማልጠፋ
ተናግሬ የማልሰክን
ከዲዳ ጋር የማወራ
ብጫቂ ጨርቅ ያልደለለኝ
ቀለም መርጦ ማይገድበኝ
ከእብድ ጋር የምዋልል
በአየሁት ላይ የምማልል
ፍቅር ልኩን የመገበኝ
ፆታዬን በነብሴ
ግብሬን በወድ ልክ አኗኗሬን በሴት
ያበቃው ያነቃው
ገጣሚ ነኝ የሰው ደሴት
[ አዲብ መሃመድ ]
@Samuelalemu