ተሽከርካሪን በመጠቀም በተለምዶ ሿሿ ተብሎ የሚጠራውን ወንጀል በተለያዩ ቦታዎች ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ‼️
ግለሰቦቹ ወንጀሉን ሲፈፅሙ በቁጥጥር ስር የዋሉት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አየር ጤና አካባቢ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጥሩነሽ ቤጂንግ አካባቢ ነው።
በከተማችን አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች በተለምዶ አጠራሩ ሿሿ ተብሎ የሚጠራውን የወንጀል አይነት አስቀድሞ ለመከላከል እያከናወነ ያለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠሉን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አየር ጤና አካባቢ በኮድ 3 20947 ኦሮ በሆነ ተሽከርካሪ ሁለት ተጠርጣሪዎች ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር ወንጀሉን ሲፈፅሙ በፖሊስና በአካባቢው ህብረተሰብ ተባባሪነት ከሰረቋቸው 9 ሞባይል ስልኮች ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ብሏል።
በተመሳሳይ ዜና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማም ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሠዓት ገደማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ጥሩነሽ ቤጂንግ አካባቢ የታክሲ ሾፌር፣ ረዳትና ተጓዥ በመምሰል በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 በሆነ 26019ደሕ ሚኒ ባስ ተሽከርካሪ አንድ መንገደኛ ሴት ካሳፈሩ በኋላ የያዘችውን ሳምሰንግ የእጅ ስልክና 20 ሺ ብር በመቀማት በኃይል ገፍትረው በመጣል ለማምለጥ ሲሞክሩ በስራ ላይ በነበሩ የታክሲ ተራ አስከባሪዎችና የፖሊሰ አባላት ከነ ኤግዚቢቱ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውንም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
በተለምዶ ሿሿ እየተባለ የሚጠራው የማታለል ወንጀል የሚፈፀመው በትራንስፖርት ተሽከርካሪ መሆኑን ያሳሰበው ፖሊስ ህብረተሰቡ ትራንስፖርት ሲጠቀም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ገልፆል።