ታይሰን በአንድ ወቅት ዶናልድ ትራምፕን ቀጥሯቸው ነበር ‼️
ከአመታት በፊት ፡ ላስቬጋስ ውስጥ በሚገኝ ሆቴል ፡ አንድ ክፍል ውስጥ ውድ የሆነ ሉዊስ ቪተን ቦርሳ ተገኘ ።
የሆቴሉ ሃላፊዎች በክፍሉ ውስጥ የተገኘውን ቦርሳ ሲከፍቱት በውስጡ አንድ ሚሊየን ዶላር ነበረበት ።
ወዲያው በክፍሉ ውስጥ አድሮ ፡ አንድ ሚሊየን የሚያህል ብር እንደቀልድ ረስቶ ወደሄደው ሰው ተደወለ ።
" ሃሎ ማይክ ፡ ያደርክበት ሆቴል ውስጥ እቃ ሳትረሳ አልቀረህም "
ታይሰን ልክ ይህን ሲሰማ እንዲህ አለ ....
ኦው ፡ ልክ ናችሁ ገንዘብ ረስቻለሁ ።
ታይሰን ማለት እንዲህ ነው ። ሚሊየን ዶላር ረስቶ እስኪያስታውሱት የሚጠብቅ ።
በ1990 ዎቹ በስፖርቱ ዘርፍ የምድራችን ከፍተኛ ተከፋይ የሆነውና በአንድ ወቅት ሚስቱ ለነበረችው ሴት ፡ 2.2 ሚሊየን ዶላር አውጥቶ ከወርቅ የተሰራ የመታጠቢያ ገንድ በመግዛት ስጦታ የሰጠው. ....
እጅግ ዘናጭ እና መርጦ ለባሽ በመሆኑ ፡ በዛን ወቅት በየወሩ ከመቶሺህ ዶላር በላይ ፡ ለልብስና ለጌጣጌጥ ያወጣ የነበረው ታይሰን ...... በቤቱ ውስጥ እንደውሻና ድመት እየደባበሰ የሚያሳድጋቸው ሶስት ነብሮች የነበሩት ሲሆን ለነዚህ እንስሳትም ወጭ ከፍተኛ በጀት መድቦ ነበር ።
እንግዲህ በዚህ ....... ገንዘብ ታይሰንን እያሳደደ በሚይዝበት ወቅት ነበር ፡ ሀይለኛ የቢዝነስ ማይንድ የነበራቸውን ሚሊየነሩን ነጋዴ ዶናልድ ትራንፕን የፋይናንስ አማካሪ አድርጎ የቀጠረው ።
እናም በዛሬው እለት. .. በ31 አመት ከእሱ በእድሜ ከሚያንሰው ቦክሰኛ ጃክ ፓውል ጋር ስሙን ለማስጠበቅ የሚወዳደረው የ58 አመቱ ማይክ ታይሰን ፡ ከሰአታት በኋላ በላስቬጋስ የሚያደርጉትን ፍልሚያ አለም በጉጉት እየጠበቀው ነው ።