❗ስለ መሬት መንቀጥቅጡ ዝርዝር መረጃ❗
ብዙዎች የዛሬው ይለያል ያሉት በሬክተር ስኬል 5.3 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ እሁድ ለሊት ተከሰተ
በኢትዮጵያ በሬክተር ስኬል 5.3 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ እሁድ ለሊት 8 ሰዓት ከ44 ደቂቃ ላይ መከሰቱን የአውሮፓ ሜዲትራንያን ሴይስሞሎጂ ማዕከል (EMSC) አስታወቀ። ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየው የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው ንዝረት መዲናዋ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል።
የለሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው፤ ከጭሮ ከተማ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ እንደሆነ የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት ገልጿል። የመሬት መንቀጥቀጡ እንደ ጭሮ ከተማ ሁሉ በአዋሽም “ቀላል” የሆነ ንዝረት ማስከተሉን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦችን የሚመዘግበው “ቮልካኖ ዲስከቨሪ” አመልክቷል።
ንዝረቱ “ደካማ” በሆነ መጠን ድሬዳዋ፣ ሂርና፣ በዴሳ፣ ገለምሶ፣ ደደር፣ አቦምሳ፣ ገዋኔ፣ መተሐራ፣ አዳማ፣ ወንጂ፣ ሞጆ እና ቢሾፍቱ ከተሞችን ማዳረሱን ይኸው ተቋም ጠቁሟል። ተመሳሳይ መጠን ያለው ንዝረት በደብረሲና፣ ደብረ ብርሃን፣ ከሚሴ፣ ባቲ፣ ኮምቦልቻ እና ደሴ ድረስ መሰማቱንም የ“ቮልካኖ ዲስከቨሪ” መረጃ ያሳያል።
ዛሬ እሁድ የካቲት 16 ለሊት የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ካለፈው ዘጠኝ ቀን ወዲህ የተመዘገበ ከፍ ያለ መጠን ያለው ርዕደ መሬት ነው። ከመተሐራ ከተማ ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ፤ የካቲት 7 እኩለ ለሊት ገደማ የተከሰተው እና በሬክተር ስኬል 6.0 የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ ባለፉት ወራት ሁሉ ከደረሱት ሁሉ በመጠን ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።