የፋኖ አመራሮችን ኢላማ ያደረገ የድሮን ጥቃት መፈፀሙ ታወቀ
"በመግለጫ፤ በመልዕክት እና በፎቶ ጋጋታ ህዝብን መሸወድ አይቻልም" የሚሉ ፅሁፎች ባለፉት ጥቂት ቀናት ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት የተሰራጩ ሲሆን በይዘታቸውም የፋኖ አመራር የሆነው ዘመነ ካሴ በድሮን ጥቃት እንደተገደለ ይገልፃሉ።
"የሞተ ሰው መቼም አይነሳም፣ ዘመነ በህይወት ቢኖር መቼም በሚዲያ ወጥቶ ባልዋለበት አውደ ውጊያ እንደዋለ አድርጎ የሚያወራ ሰው አሁን በድምጽ ፊት ለፊት መግለጫ መስጠት አይቻልም" የሚሉት እነዚህ ፅሁፎች ለዘመነ መሞት አስረስ ማረ ዳምጤ በተደጋጋሚ የዘመነ መልዕክት በሚል የሚያወጣቸውን ፎቶዎች በማስረጃነት ሲያቀርቡ ተመልክተናል።
በዚህ ዙርያ መሠረት ሚድያ ማጣራት ያደረገ ሲሆን አየር ሀይል የፋኖ አመራሮችን ኢላማ ያደረገ ተደጋጋሚ ጥቃት ባሳለፍነው ሳምንት ማድረጉን አረጋግጧል።
"እኔም የጥቃቱ ኢላማ ነበርኩ" ብሎ ቃሉን ለመሠረት ሚድያ የሰጠው የፋኖ ሀይሎች የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አስረስ ማረ ዳምጤ የድሮን ጥቃቱ አሁን አሁን የየእለት ድርጊት ሆኗል ብሏል።
አስረስ ማረ ስለ ዘመነ ካሴ ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚዘዋወረውን መረጃ በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ "ሁላችንም ሰላም ነን" በማለት መረጃው ትክክል እንዳልሆነ ጠቁሟል።
አክሎም "የድሮን ጥቃቱ እስካሁን ለዘመነ ስጋት አልነበረም፣ ይሁንና በቅርቡ እርሱ የነበረባቸው 3 ቦታዎች በድሮን ተመተዋል። ጥቃቱ እሱን ሳይሆን ንፁሀን ዜጎችን ሰለባ አድርጓል" በማለት ተናግሯል።
መሰረት ሚድያ
@Sheger_press