በኢትዮጵያ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙ 2 መቶ 70 ናይጄሪያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲላኩ ትዕዛዝ ተሰጠ
ሕዳር 11፣2017 (አራዳ ኤፍ ኤም)
በአቡጃ የሚገኘው የናይጄሪያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ኢንያንግ ኤኮ ለናይጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የናይጄሪያውያን ዲያስፖራ ኮሚሽን ባስተላለፉት መልዕክት፣በኢትዮጵያ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙትን ከ2 መቶ 70 ያላነሱ ናይጄሪያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አዘዋል
ዳኛው ይህን ውሳኔ ያስተላለፉት የኢትዮጵያ መንግስት ለእነዚህ እስረኞች የምግብ፣መድኃኒት እና ሌሎች ግብዓቶች የሚሆን በጀት እንደሌለው ማሳወቁን ተከትሎ ነው ተብሏል
የኢትዮጵያ መንግስት ለናይጄሪያ መንግስት በላከው ይፋዊ መልዕክቱ እስረኞቹን እንዲረከብ መጠየቁን በመግለጽ፣በእስር ላይ የሚገኙትን ናይጄሪያውያን ተቀብሎ እንዲመልስ የሚያስገድድ ትዕዛዝ ዳኛው ሰጥተዋል ተብሏል።
የናይጄሪያ ፌደራል መንግስት ለዚህ ዋናው ምክንያት ነው ያለውን የብሄራዊ የስደት ፖሊሲን በመገምገም፣የዜጎችን ሞት፣በደል፣ መድልዎ እና ናይጄሪያውያን ወደ ውጭ በሚጓዙበት ጊዜ የሚያጋጥሟቸውን ሌሎች ጉዳዮችን እንደሚገታ አስታውቋል ሲል የዘገበው ዘ ስትሪት ጆርናል ነው
!