#ከዓይን ሲርቅ የሚደርቀው እንቁላል…
“ሐልዎተ እግዚአብሔር” የእግዚአብሔርን መኖር ከምናውቅባቸው ነገሮች አንዱ ፍጥረታትን መመልከት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶቻችን ያስተምሩናል፡፡
ይህ ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌለው ፍጥረት አስገኚ፣ ፈጣሪ ባይኖረው ከዓለም ጅማሬ እስካለንበት ዘመንና እስከ ዓለም ፍጻሜ ስርዓቱን ጠብቆ ባልኖረም ነበር ይሉናል፡፡
ያውም ከድንቅ ተፈጥሯዊ ባሕርዩ ጋር፡፡ በዚህ ድንቅ ተፈጥሯዊ ባህርይ ከሚታወቁት ፍጥረታት አንዷ ግዡፏ የአእዋፋት ዝርያ ሰጎን ናት፡፡
ሰጎን እንቁላል ከጣለች በኋላ እስኪፈለፈል ድረስ አይኗን ከእርሱ ላይ አታነሳም፡፡ ምግብ ፍለጋ ስትሔድም ወንዱን አስጠብቃ ነው፡፡ አይኗን አንስታ ረጅም ጊዜ ከቆየች ይደርቅና አይፈለፈልላትም፡፡
የመፈልፈያ ጊዜያቸው ሲደርስም ከውጪ ሆና ቅርፊቱን ታንኳኳለች፣ እነርሱም ከውስጥ ሆነው ያንኳኳሉ፡፡ ድምጽ ታሰማቸዋለች፣ እነርሱም መልሰው ድምጽ ያሰማሉ፡፡ ይህን ጊዜ እንቁላሉን ሰብራ ታወጣቸዋለች፡፡
ስታንኳኳ ካላንኳኩ፣ ድምጽ ስታሰማቸው ድምጽ ካላሰሙ ጊዜያቸው ገና ነው አሊያም ሞተዋል፣ ወይም እንቁላሉ ባዶ ነው ብላ ስለምታስብ ትታቸው ትሔድና በዚያው ይደርቃል፡፡
እኛም እንደ ጫጩቶቹ ነን፡፡ አባታችን እግዚአብሔርም የከከበበን የኃጢአት ቅርፊት ሰብሮ የሚያወጣን ዘወትር አይኖቹን ከኛ የማያነሳ ጠባቂያችን ነው፡፡
ይህ እንዲሆን ግን ቅርፊቱን ሲያንኳኳ እኛም በኃጢአት ውስጥ እንኳን ብንሆን አድነኝ ብለን መልሰን እናንኳኳ፤ ድምጽ ሲያሰማ፣ ሲጠራን፣ ተመለሱ ሲለን የእሺታ፣ የመዳን ፍላጎት ድምጽ እናሰማው፡፡
አዎ ቅርፊቱን አንሳልኝ መውጣት፣ መራመድ፣ በጽድቅ ስራ መብረር እፈልጋለሁ እንበለው፡፡ በዘመነ ስጋዌው በዚህ ምድር ሲመላለስ ፈውስ ፈልገው ወደርሱ የሚመጡትን “ልትድን ትወዳለህን? ብሎ ይጠይቅ የነበረው በፈቃዳችን ስለሚሰራ ነው፡፡
መዳን፣ እንደ ሰጎኗ ጫጩቶች ከቅርፊቱ መውጣት፣ በበጎ ምግባር፣ በትሩፋት መጓዝ የምንችልበት እድል ተሰጥቶናል፡፡
ይህን ድንቅ ምስጢር የሚገልጹልን የመዳንን መንገድ እንድንከተል በጸሎታቸው የሚያስቡንን፣ የኃጢአት ቅርፊቷን የምትጭንብንን ይህቺን ዓለም ንቀው የመነኑትን ገዳማውያንና ቅዱሳት መካናትንም እናስብ፡፡ ጥሪውን እንድንሰማ፣ ለማንኳኳቱም መልስ እንድንሰጥ ይርዳን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444