ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በቱርክ አሸማጋይነት ከሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ ጋር በኹለቱ አገራት የባሕር በር ውዝግብ ዙሪያ ለመነጋገር ወደ አንካራ ያቀኑት በዋሽንግተን ጉትጎታ እንደኾነ ጉዳዩን ከሚያውቁ ምንጮች መስማቱን ሚድል ኢስት አይ ጋዜጣ ዘግቧል።
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ ዐቢይ በአንካራው ሽምግልና ላይ እንዲገኙ ስልክ ደውለው እንዳሳመኗቸው ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
አንድ የቱርክ ባለሥልጣንም፣ ዐቢይ ወደ አንካራ የተጓዙት በምዕራባዊያን ምክር መኾኑን ጠቅለል ባለ መልኩ ጠቁመዋል ተብሏል።
ሚድል ኢስት አይ፣ ከዐቢይ ቃል አቀባዮች በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ለማግኘት ጠይቆ፣ ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱን ጠቅሷል።
@Sheger_press