#ገዳሙን ከነረበት ችግር አላቃ ወደ ገነትነት ለውጣዋለች
ገና በትንሽ እድሜዋ ለምንኩስና ልዩ ፍቅር ያደረባት፣ የበጎ ነገር ጠላት የሆነው ጠላታችን ያደረሰባትን ፈተና ተቋቁማ ያሸነፈችው፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዩ በረከት ያደሏት፣ የግብጽ ኦርቶዶክሳውያን 6ኛ ፓትርያርክ ቅዱስ ቄርሎስ ታላቅ እመምኔት እንደምትሆን ገና በመጀመሪያ የምንኩስና ዘመኗ የተበዩላት ድንቅ ገዳማዊት ናት፡፡ በርካቶች ስለ ቅዱሳን ጻድቃን እናቶች የሚነገረውን ገድልና ተአምራት ለመንቀፍ ከሚሞክሩበት ምክንያት አንዱ ከምዕተ ዓመታት በፊት የነበሩ፣ ታሪኮች ናቸው የሚል ነው፡፡ ይሁንና በአውሮፓውያኑ 1999 ጥቅምት 21 ቀን ያረፈችው እማሆይ ጣማፍ ኡምና ኤሬን (ሔራኒ) በዘመናችንም ቅድስና እንዳለ ያሳየች ድንቅ ገዳማዊት ናት፡፡
ግብጽ ጊጋር በተባለ ስፍራ የተወለደችው ቅድስት የልደት ስሟ ፋውዚያ ነበር፡፡ በስጋዊው ዘመናዊ ትምህርት ቤት የተማረች፣ በመኪናና በአውሮፕላን የተጓዘች፣ አብረዋት የተማሩና የሚያውቋት ሰዎች አሁን ድረስ በሕይወት ያሉና የሚመሰክሩላት፤ በመንፈሳዊው ደግሞ ገና በትንሽነቷ ምንኩስናን የመረጠች፣ በግብጻውያን “አቡ ሰይፈን” የሚባለው የሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎች የሴቶች ገዳም እመ ምኔት የነበረች፣ የሰራቻቸው አስደናቂ ተአምራቶች በአል-አህራም ጋዜጣ ሳይቀር ታትሞ የወጣላት፣ እግዚአብሔር በሰጣት ጸጋ እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት በቅጽበት ከአንዱ ስፍራ ወደ ሌላው የምትጓዝ ነበረች፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስ ገዳምን እስከ ዕለተ ሞቷ በእመ ምኔትነት በመራችበት ወቅት በችግር ውስጥ የነበረውን ገዳም በርካታ ልማት ወደ ሚሰራበት ስፍራም ቀይራዋለች፡፡
በረከቷን ሽተው የሚመጡ ክርስቲኖች በሚያደርጉት ድጋፍ ገዳሙን ከነበረበት ችግር አላቃ የበረሃው ገነት፣ ትልቅ የቅድስና ስፍራ አድርጋው ነው ያረፈችው፡፡ የግብጹ አልአህራም ጋዜጣ ይዟቸው ከወጣ ተአምራቶቿ አንዱ “አጊባ” ወደ ተባለ አካባቢ በአውሮፕላን ስትጓዝ፣ የተፈጠረውን ብልሽት ተከትሎ ሙሉ መንገደኞች ሊያልቁ የነበረበትና በአፍንጫው ከተከሰከሰው አውሮፕላን አንድም ሰው ሳይጎዳ በጸሎቷ ያዳነችበት፣ በዘመናችንም የቅዱሳን ጸሎት በስራዋ ኃይል እደምታደርግ ያሳየ ነው፡፡ ገዳማውያንን ማሰብ እጅግ ማትረፊያና የበረከታቸው ተሳታፊ መሆኑን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምትነግረንም ይህንን መሰረት አድርጋ ነው፡፡
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ያሉበት ልዩ ስፍራ ነው፡፡ ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያንን የሚፈውስ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ባደረግነው ጥሪ መሠረትም የዘረጋችሁት እጃችሁ ድንቅ ነገር ሰርቷል፡፡ የሴቶች ገዳማውያን መኖሪያ ባማረና በዘመነ ሁኔታ ተሰርቶ፣ የሶላር ኃይል ተገጥሞለት ጭምር ተጠናቋል፡፡ ለዚህም ባወጣችሁት አብዝቶ ይተካ፣ በዘረጋችሁት እጅ ማለቂያ የሌለው በረከት ያሳፍሳችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡ አሁንም ይህ ልግስናችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል፡፡ አንድ ትልቅ ምዕራፍ ብንጓዝም ለመስራት ከታሰበው ግማሽ ያህል እንኳ አልተጠናቀቀምና ገዳማውያኑ ልገሳችሁን ይሻሉ፡፡ አካባቢውን የበረሃ ገነት የማድረግ እድል አለንና እንጠቀምበት፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444