የሰላሌ የነዋሪው ሰቆቃ
በኦሮሚያ ክልል ግጭት ከከፋባቸው አከባቢዎች አንዱ የሆነው ሰላሌ በግጭቱ ምክንያት የነዋሪዎች ሕይወት ለአደጋ መጋለጡን እየተናገሩ ነዉ።
ነዋሪዎቹ እንደሚሉት እገታ፣ ማስፈራሪያና ቅሚያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባበሰ ነዉ። አንድ የሰሜን ሸዋ ዞን የደብረጽጌ ከተማ ነዋሪ እንደሚሉት የመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎችና አማፂያን ሠላም እንደሚያወርዱ የአካባቢዉ ህዝብ በተደጋጋሚ በአደባባይ ሠልፍ ጭምር ጠይቋል።
ተደጋጋሚዉ ጥያቄና ተማጽዕኖ መና ቀርቶ ታጣቂዎች የሚያደርሱት አስገድዶ ስወራ፣ እገታና ዘረፋዉ ቀጥሏል። የአከባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ገበያ ለመሔድና እና ለቅሶ ለመድረስ እንኳን እየሠጉ ነዉ።
ከአንድ ሳምንት በፊት ከደብረሊባኖስ አከባቢ ለገበያ በመኪና ሲጓዙ የነበሩ 50 ያክል ነጋዴዎች ሳዲኒ ብዮ በሚባል የያያ ጉሉለ ወረዳ ታፍነው እንደተወሰዱ ሌላዉ ነዋሪ አስታዉቀዋል።
የያያ ጉሌሌ ፊታል ከተማ አስተያየት ሰጪ አክለዉ እንዳሉት የፀጥታ ችግሩ ፋታ አይሰጥም። መኪና ሙሉ ሰዎች መወሰዳቸዉ የችግሩን ክፋት እንደሚያሳይ ነዋሪዉ ገልፀዋል። ይህ ቦታ ከአንድ ወር ግድም በፊት አምስት የዞን ባለስልጣናትን ጨምሮ የመንግስት ሰራተኞች የተገደሉበት አካባቢ ነው፡፡ ነዋሪዉ እንደሚሉት ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የተወሰዱት ወደ 50 የሚሆኑ ገበያተኞች እስካሁን አልተመለሱም፤ «የመኪናዉ ሾፈርም አብሮ እንደተወሰደ ነው” ብለዋል፡፡
በቅርቡ ከዞን የመጣው የመንግስት ሠራዊትም ዘመቻ መክፈቱን ባስታወቀ በጥቂት ጊዜ ዉስጥ ከአካባቢዉ በመልቀቁ ምንም ለውጥ አልታየም፡፡ «ከዚህ ከተማ ውጪ ታጣቂዎች የማይገኙበት ሥፍራ የለም» ይላሉ ነዋሪዎቹ።
“ተቸግረናል፡፡ ከተማ ውስጥ እንኳ ቢሆን ተኝቶ የሚያድር ሰው አታገኝም፡፡ ሰው እየተደበቀ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ ነው ቀን የሚገፋው፡» ይላሉ። ነዋሪዉ እንደሚሉት ሁለቱ ተፋላሚዎች ብዙ ጊዜ ፊትለፊት ሲዋጉ አታይም፡፡ «የመንግስት ጦር ሲመጣ ጫካ ያለው በደፈጣ ነው የሚጠብቀው፡፡ ሁለቱ ተፋላሚዎች ተነጋግረው መግባባት ስላልቻሉ በመሃል የመጨረሻ ስቃይ እያየን ነዉ» አከሉ ነዋሪዉ።
የመንግስት የጸጥታ ሃይልም፣ አማጺዎችም የነዋሪዉን ሥልክ ሥለሚወስዱ መረጃ መለዋወጥ እንኳን አዳጋች ሆኖ ህዝቡ ከዚህ በፊት ሲኖር ከነበረው ሃምሳ ኣመት ወደ ኋላ ተመልሶ እየኖረ ነው ብለዋል፡፡
(DW )
@sheger_press