የኬንያ መንግስት በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ 'ልዩ የፀጥታ ዘመቻ' መጀመሩን አስታወቀ
ዘመቻው የተጀመረው ባለፈው ወር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከዊሊያም ሩቶ ጋር በናይሮቢ ከተነጋገሩ በኋላ ነው።
የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት በማርሳቢት እና ኢሲዮሎ ግዛቶች በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ 'ልዩ የፀጥታ ዘመቻ' መጀመሩን አስታወቀ።
አገልግሎቱ ትናንት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚጠቀምባቸውን መሸሸጊያዎች ለቆ እንዲወጣ ለማድረግ “ኦንዶአ ጃንጊሊ ኦፖሬሽን” የተባለ ዘመቻ ከትናንት ጥር 26 ቀን ጀምሮ እንደሚያካሄድ ገልጿል።
በከፍተኛ ደረጃ የሚካሄደው ዘመቻ ለኬንያ ብሔራዊ ደህንነት ከፍተኛ ስጋት የሚጥሉ እንደ የጦር መሳሪያ፣ የአደንዛዥ ዕፅ እና የሰዎች ዝውውር፣ ህገወጥ የማዕድን ማውጣት ያሉ ህገወጥ ስራዎችን የሚያከናውኑ ወንጀለኞችን ዒላማ ያደረገ ነው ተብሏል።
@sheger_press