የሳዑዲ ዓረቢያ ጸጥታ ኃይሎች፣ ከፈረንጆች 2019 እስከ 2024 ከየመን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ በገቡ ኢትዮጵያዊያን በሚበዙባቸው ፍልሰተኞች ላይ የግድያና አስገድዶ መድፈር ወንጀሎችን እንደፈጸሙ ከፍልሰተኞች መስማቱን ጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል።
የሳዑዲ ዓረቢያ ጸጥታ ኃይሎች አኹንም በፍልሰተኞች ላይ ኃይል መጠቀም እንዳላቆሙ ዘገባው ጠቅሷል። ሂውማን ራይትስ ዎች ከዓመት ከመንፈቅ በፊት ባወጣው የምርመራ ሪፖርት፣ ከየመን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ በሕገወጥ መንገድ በሚገቡ ፍልሰተኞች ላይ ግድያን ጨምሮ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሊባሉ የሚችሉ ድርጊቶች ተፈጽሞባቸዋል በማለት መክሰሱ አይዘነጋም።
ከአውሮፓዊያኑ 2022 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ከየመን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ የገቡ ወይም ለመግባት የሞከሩ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በ32 በመቶ ጨምሮ ቁጥሩ ከ96 ሺሕ 600 በላይ ደርሶ እንደነበር የተመድ ሪፖርት ያመለክታል።
ሂውማን ራይትስ ዎች፣ ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር ግንኙነት ያላቸው አገራት ይሄን ድርጊት ካላወገዙ በስተቀር፣ ድርጊቱ ወደፊትም ይቀጥላል በማለት ማስጠንቀቁን ጋርዲያን ጠቅሷል።
@sheger_press