❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤
❤ #ጥር ፳፪ (22) ቀን።
❤ እንኳን #በግብጽ_አገር_ከቅማን ከተማ ለከበረና ለገነነ #ለመነኰሳት_ሁሉ_አባት በገዳም ለሚኖሩ እንደ ኮከብ ለሚያበራላቸው #ለአባ_እንጦንስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከማፍን_ኤጲስቆጶስ_ከአባ_ሚናስ እግዚአብሔር አምላክ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #ርእሰ_መነኰሳት_አባ_እንጦንስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ንጹሐን ክርስቲያን ናቸው እርሱም ከታናሽነቱ ጀምሮ ተንኰል ሽንገላ በልቡ ውስጥ የለውም ከወላጆቹም ጋር ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ በቆረበ ጊዜ ከሕፃናት ጋር በመጫወት ከቶ አይስቅም ነበር። ጥቂት በአደገም ጊዜ ራሱን ዝቅ አድርጎ ለወላጆቹ ይታዘዝ ነበር ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ተማረ ያን ጊዜም የእስክንድር አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ቲዎናስ የተሾመበት ዘመን ነበር የእንጦንዮስንም ወሬውን ሰምቶ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ባረከውና ስርሱ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "ይህ ሕፃን በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናል ዜናውም በዓለሙ ሁሉ ይወጣል" እጁንም በላዩ ጭኖ ዲቁና ሾመው።
❤ ከዚህም በኋላ ወላጆቹ በሞቱ ጊዜ ታናሽ ብላቴ እኅት ትተውለት ነበር። ከሰባት ወርም በኋላ እንደ ልማዱ ወደ ቤተ ክርስቲያን በሔደ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ፍቅር በልቡ አደረበትና በኀሳቡ በዓለም የሚሠራውን ሁሉ አባቶቻችን ሐዋርያት ሁሉን ዓለምን ሥራ ትተው ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ተከትሉት በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍም እንደተጻፈ ጥሪታቸውን እየሼጡ የሽያጩንም ዋጋ በሐዋርያት እግር ሥር ያኖሩትን አሰበ "እግዚአብሔር በሰማያት ያዘጋጀላቸው ዋጋቸው ምን ያህል ይሆን" አለ ይህም ኀሳብ በልቡ ውስጥ የሚወጣ የሚወርድ ሆነ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደ የክብር ባለቤት ጌታችን በከበረ ወንጌል ለባለጸጋው የተናገረውን ሰማ እንዲህ ሲል "ፍጹም ትሆን ዘንድ ከወደድክ ሒድ ጥሪትህን ሁሉ ሽጠህ ለድኆች ስጥ በሰማይም ላንተ ድልብ አድርገው መጥተህም ተከተለኝ"። ከእግዚአብሔር ዘንደሰ ይህን ልዩ ኀሳብ አግኝቶ ይህ ቃል ስለርሱ እንደተነገረ አሰበ በዚያንም ጊዜ ከቤተ ክርስቲያን ወጣ ለአባቲም ያማረ ሰፊ ምድር ነበረው ለአገሩም ሰዎች ሰጣቸው ለርሱ የተዉለትንም ጥሪታቸውን ሁሉ ሽጦ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጣቸው እኅቱንም ወስዶ ከደናግል ገዳም አስገባት።
❤ በዚያንም ወራት የምንኵስና ሥርዓት አልተገለጸም ነበር እግዚአብሔርንም ለማገልገል የሚሻ ከመንደር ጥቂት ወጣ ብሎ ብቻውን በመቀመጥ በጾም በጸሎት ተወስኖ ይጋደላል የከበረ እንጦንዮስም እንዲሁ አደረገ ሰይጣናትም በስንፍናና በዝሙት ጦር የሚዋጉት ሆነ በሕልሙም የሴት ገጽ በማሳየት አብራውም እንደምትተኛ ያደርጓታል።
❤ ከዚህም በኋላ ባበባህር ዳርቻ ወዳለች የመቃብር ቤት ሒዶ በዚያ የሚኖር ሆነ በላዩ በአደረ በእግዚአብሔርም ረድኤት በተጋድሎ በረታ ምግቡንም ከዘመዶቹ ወገን ያመጡለት ነበር ሰይጣናትም ሲጋደል አይተው ቀኑበት ታላቅ ድብደባንም ደብድበው ጥለውት ሔዱ ዘመዶቹም ሲመጡ እንደ ሞተ ሁኖ ወድቆ አገኙት ተሸክመውም ወደ ቤተ ክርስቲያን ወሰዱት ጌታችንም አዳነው በነቃም ጊዜ ወደ ቦታው ተመልሶ ይጋደል ዘንድ ተጋድሎውን ጀመረ።
❤ በዚያንም ጊዜ ሰይጣናትን ወደርሱ ሲመጡ አያቸው በአራዊት አምሳል በአንበሶችና በተኵላዎች የተመሰሉ አሉ በእባቦችና በጊንጦችም የተመሰሉ አሉ ያስፈሩትም ዘንድ አንዱም አንዱ በላዩ ተነሣሡ እንጦንዮስም "በእኔ ላይ ለእናንተ ሥልጣን ካላችሁ ከእናንተ አንዲ ያቸንፈኝ ነበር" ብሎ ዘበተባቸው ወዲያውኑ እንደ ጢስ ተበተኑ በሰይጣናት ላይ ድልን እግዚአብሔር ሰጥቶታልና ሰይጣናትም ከሚያመጡበት መከራና ሥቃይ ዐረፈ። ምግቢንም በየዓመቱ ሁለት ጊዜ ያበስላል በፀሐይም ያደርቀዋል ወደበዓቱም ማንም እንዲገባ አያሰናብትም የሚሻውም ሁሉ በውጭ ይቆምና ድምፁን ይሰማል እንጂ ሃያ ዓመትም እንዲህ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ በገድል ተጠምዶ ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ ፍጹም የሆነ እግዚአብሔርን መፍራትንና አምልኮቱን ለሰዎች ወጥቶ ያስተምር ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘው ስለዚህም ወደ ፍጹም አገር ወጥቶ ብዙዎች ደቀ መዛሙርትን ሰብስቦ አስተማራቸው በእግዚአብሔርም ሕግ አጸናቸው ደቀ መዛሙርቶቹ በውስጣቸው የሚኖሩባቸው በዙዎች ገዳማት ተሠሩለት።
❤ ስለ ሃይማኖት ስደት በሆነበት ወራት በሰማዕትነት መሞትን ወዶ እስክንድርያ አገር ሔዶ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ ከቶ አልያዙትም በክርስቶስም ስም የታሠሩ እሥረኞችን በመጐብኘት ቢአረጋጋቸውና ቢአጽናናቸውም አልያዙትም መኰንኑም እንደማይፈራ በአየው ጊዜ ከፍርድ አደባባይ ውስጥ እንዳይታይ አዘዘው እርሱ ግነሰ ሁል ጊዜ መታየትን አልተወም እንደመአሠየውና በሰማዕትነትም እንዲሞት የሚያስቆጣውን ነገር ይናገረው ነበረሰ መኰንኑም በእርሱ ላይ ምንም ክፉ ነገር አላደረገም አምላካዊት ኃይል ከልክላዋለችና።
❤ ሊቀ ጳጳሳት ጴጥሮስ ለሰማዕታት ፍጻሜ ሁኖ የመከራው ወራት ከአለፈ በኋላ እንጦኒ ወደ ገዳሙ ተመለሰ ይህም በአምላክ ፈቃድ ሆነ የሚለብሰውም ማቅ ነበር በዘመኑ ሁሉ ገላውን በውኃ አልታጠበም ብዙዎች በሽተኞችም ወደርሱ ይመጣሉ በላያቸው ሲጸልይ ይድናሉ። ብዙዎች ሕዝቦችም ትምህርቱን ሊሰሙ ወደርሱ ሲመጡ በአያቸው ጊዜ ብቻውንም ይኖር ዘንድ እንዳልተውት አይቶ ከእርሱ ስለሚደረገው ነገር ልቡ እንዳይታበይ ፈራ እነርሱ ወደማያውቁት ቦታ ወደላይኛው ግብጽ ይሔደሰ ዘንድ ወዶ ወደ ባሕሩም ወደብ ደርሶ መርከብ እየጠበቀ ተቀመጠ ከሰማይም ወደርሱ ቃል መጣ እንዲህም አለው "እንጦንዮስ ሆይ ወዴት ትሒዳለህ ከዚህስ ምን ትሻለህ" አለው እርሱም "ብዙዎች ወደእኔ ስለሚመጡ እንደምፈልገው ለብቻ መኖር አልተቻለኝም ስለዚህም ወደ ላይኛው ግብጽ እሔድ ዘንድ ወደድኩ" አለ ያም ቃል መልሶ እንዲህ አለው ወደ "ላይኛው ግብጽ ብትሔድ ድካምህ ደግሞ እጥፍ ይሆናል ብቻህን መኖር ከወደድክ ግን የሦስት ቀን ጐዳና ያህል ወደ ውስጠኛው በረሀ ተጓዝ"።
❤ በዚያንም ጊዜ በዚያች ጐዳና ሊጓዙ የሚሹ የዓረብ ሰዎችን አብርአቸው ወደ እርሳቸውም ሒዶ አብሮአቸው ይሔድ ዘንድ ለመናቸው እነርሱም በደስታ ተቀበሉት ወደ አንድ እጅግ ረጅም ወደሆነ ተራራ እስከሚያደርስ የሦስት ቀን ጐዳና ተጓዘ በዚያም የጠራና የቀዘቀዘ ውኃ አለ ደግሞም የሰሌን የተምር ዕንጨቶች መቃዎችም በብዛት አሉበት እንጦንዮስም ያንን ቦታ ወደደው ዓረቦችም ምግቡን የሚያመጡለት ሆነ ብዙዎች የከፉ አራዊትም ነበሩ በጸሎቱም እግዚአብሔር አስወገዳቸው ወደዚያም ቦታ ከቶ አልተመለሱም። አንዳንድ ጊዜም ወደ ባሕሩ ዳርቻ በመውጣት ደቀ መዛሙርቶቹን ጐብኝቶና አረጋግቶ በበረሀ ውስጥ ወደአለው ቦታው ይመለሳል።