❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤
❤ #ጥር ፳፭ (25) ቀን።
❤ እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት_ለሮም_ንጉሥ_ልጅ ለከበረ #ለሰማዕቱ_ለቅዱስ_ስብስትያኖስ ምስክርነቱ ለፈጸመበት ለዕረፍቱ በዓልና አስቀድሞ ቀራጭ ለነበረ ራሱን ለሸጠው በገድል ለተጸመደ ለኖረ ለከበረ #ቅዱስ_ጴጥሮስ_ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕት #ቅዱስ_አስኪላ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ስብስትያኖስ፦ ይህም የቅዱስ የሮሜ ንጉሥ ልጅ ነው። እርሱንም ወላጆቹ በተግሣጽና እግዚአብሔርን በመፍራት የአሳደጉት ነው። አባቱም ከሞቱ በኋላ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ ይህንንም ቅዱስ አገረ ገዥነት ሾሙት እንደ አባቱም እጅግ አከበሩት። እርሱሜ በጥበብና በማስተዋል ይጓዝ ነበር በሽተኞችን ሁሉ የዕውራንንም ዐይኖች በጸሎቱ ከፈተ።
❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ዲዮቅልጥያኖስ በካደው ጊዜ ለጣዖት ይሰግድ ዘንድ ስብስትያኖስን ግድ አለው ባልሰማውም ጊዜ ከደረቀ ግንድ ጋር አሠረው ቊጥር በሌላቸው ፍላጻዎች ይነድፉት ዘንድ አዘዘ እንደሞተም ጠርጥረው ትተውት ሔዱ ምእመናንም በሌሊት ሲመጡ በሕይወት አገኙት ፈትተውም ወደ ደሴት መካከል ወስደው በዚያ አኖሩት።
❤ ዲዮቅልጥያኖስም ሰምቶ ወደርሱ አስቀረበውና በብረት ዘንጎች ይደበድቡት ዘንድ አዘዘ እየደበደቡትም ብዙ ቀኖች ኖሩ ከዚህም በኋላ ነፍሱን አሳለፈ። ለቅድስት ውሉድስና በሕልም ተገልጦ ሥጋው ያለበትን ነገራት እርሷም ሒዳ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስና ጳውሎስ መቃብር ወስዳ ቀበረችው። ጌታችንም መታሰቢያውን ለሚያደርግና ስሙን ለሚጠራ የቸነፈር ሕመም እንዳይቀርበው ቃል ኪዳንን ሰጠው።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ጴጥሮስ፦ ይህም ቅዱስ አስቀድሞ ቀራጭ ነበረ እርሱም ልቡ የደነደነ ርኅራኄ የሌለው ነው በዚህም ክፉ ስም ጨካኝ ርኅራኄ የሌለው ብለው ይጠሩታል። ከዚህም በኋላ የኃጢአተኞች ሞት የማይሻ ጌታችን ከእርሱ ምጽዋት የሚለምነውን ድኃ ላከለትና ለመነው በዚያንም ጊዜ አገልጋዩ እንጀራ ተሸክሞ ደረሰ አገልጋዩ ከተሸከመው ከራሱ ላይ አንድ እንጀራ ለዚያ ድኃ ጣለለት ይህንንም ያደረገ ስለ ርኅራኄ አይደለም ከአጠገቡ እንዲሔድለትና ከቶ ወደርሱ እንዳይመለስ ነው ምስኪኑም ተቀብሎ ወደ ማደሪያው ሔደ።
❤ በዚያችም ሌሊት ተኝቶ ሳለ በሕልሙ እንዲህ አየ ብዙዎች ሊተሳሰቡት ይሻሉ በእጆቻቸውም ሚዛኖች ተይዘዋል ብዙዎችም መልካቸው እጅግ የከፉ ጥቋቊሮች ኃጢአቱ ሁሉ ከእርሳቸው ጋር አለ በግራ በኩል ባለው ሚዛን ውስጥ አኖሩት ደግሞ ልብሳቸቻው ነጫጭ የሆኑ ከብርሃናውያን መላእክት መልካቸው ያማረ ብዙዎች ነበሩ እነርሱም ቁመው በማዘን "ምንም ያገኘነው ነገር የለም በቀኝ ባለው ሚዛን ውስጥ ምን አናኖራለሁ" ይሉ ነበር በዚያንም ጊዜ ከእርሳቸው አንዱ መልአክ ጴጥሮስ ለድኃው የጣላትን ያችን እንጀራ አምጥቶ "ከዚች እንጀራ በቀር ሌላ ከበጎ ሥራ ምንም አላገኘሁለትም" አለ ባልንጀሮቹ መላእክትም "በእነዚህ ሁሉ ኃጢአቶቹ አንጻር ይቺ ምን ትጠቅማለች" ብለው መለሱ በዚያንም ጊዜ እየፈራና እየደነገጠ ከእቅልፋ ነቅቶ ከተኛበት ተነሣ።
❤ ከዚያችም ዕለት ወዲህ ስለቀደመች ክፉ ሥራው ተጸጸተ እጅግም የሚራራ ሆነ ቤቱንና ጥሪቱን ሁሉ ሽጦ ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ ራሱንም ሸጠ። ብዙዎችም ከበጎ ሥራዎች ይህን ስለ ሠራ እንደሚአመሰግኑትና እንደሚያደንቁት በአወቀ ጊዜ ከዚያ በመሸሽ ወደ አስቄጥስ ገዳም ገብቶ ከአባ መቃርስ ገዳም በዚያ መነኰሰ ፍጹም በሆነ ተጋድሎም ተጠምዶ እግዚአብሔርን አገልግሎ የዕረፍቱን ጊዜ አውቆ የከበሩ አረጋውያንን ጠርቶ ተሳለማቸውና በዚያን ጊዜ ጥር24 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በቅዱስ ሰብስትያኖስና በአባ ጴጥሮስ በጸሎታቸ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር25 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከ_ስብስትያኖስ_ሰማዕተ ዋሕድ ወልድ። ዘንዱፍ በአሕፃ ወእሡር በጒንድ። ተውላጠ ዝንቱ ፃማከ ወሕማምከ ፍድፉድ። መጽሐፈ ገድልከ በኀበ ሀሎ ዐፀድ። እግዚአብሔር አሕረመ ኢይባዕ ብድብድ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጥር_25።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ተፈሣሕ በእግዚአብሔር ወይሁበከ ስእለተ ልብከ። ክሥት ለእግዚአብሔር ፍኖተከ። ተወከል ቦቱ ወውእቱ ይገብር ለከ"። መዝ 36፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ማር 9፥16-30።
❤ መልካም የአቡነ ሕፃን ሞዐ የልደት በዓልና የቅዱስ መርቆሬዎስ የተአምራት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
@sigewe
https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL