❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #የካቲት ፳፰ (28) ቀን።
❤ እንኳን #ለአርእስተ_አበው_ለቅዱሳን #ለአብርሃም_ለይስሐቅና_ለያዕቆብ ለበዓላቸው መታሰቢያና #ለሮማዊ_ቅዱስ_ቴዎድሮስ በነገሥታት መክሲሞስና መክስምያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ቴዎድሮስ_ማኅበር ከሆኑ #ስድስት_ሺህ_ሦስት_መቶ_አራት ሰዎች በሰማዕትነት ከዐረፉ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሮማዊው_ሰማዕቱ_ቅዱስ_ቴዎድሮስ፦ እርሱም ከእስያ አውራጃ አስጢር ከሚባል አገር ነው። ይህንንም ቅዱስ በነገሥታት ዘንድ አማልክትን በማምለክ እርሱ እንደማይስማማ ወነጀሉት በዚያንም ጊዜ አስጠርተው "ለአማልክት ለምን አትሰግድም" አሉት፡እርሱም "እኔ ክርስቲያን ነኝ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አላመልክም" ብሎ መለሰላቸው። የበርብዮስጦስ፡ ልጅን ጉሥም "ለአማልክቶቼ ብትገዛ በጭፍራዎቼና በመኳንቶቼ ሁሉ ላይ አለቃ አድርጌ እሾምሃለሁ ብዙ ወርቅና ብር የከበሩ ልብሶችንም እሰጥሃለሁ" አለው ቅዱስ ቴዎድሮስም "ወርቅህና ብርህ ለጥፋት ይሁንህ እኔስ በንጉሤ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለጸጋና አለቃ ነኝ" አለው።
❤ ንጉሥም "ለአምላክህ ልጅ አለውን?" አለው የከበረ ቴዎድሮስም "አዎን ከመለኮቱ ባሕርይ የተገኘ ከእርሱ ጋር ዓለምን የፈጠረ በእውነት ልጅ አለው" ብሎ መለሰለት ንጉሡም "አምላክህን ብናውቀው ልናገኘው እንችላለን" አለው ቅዱስ ቴዎድሮስም "ወደርሱ ከተመለስክ እንደ እኔ ጭፍራ ትሆናለህ የተወደደ መሥዋትም ያደርግሃ" አለው። ንጉሡም "ነገር አታብዛ ብዙ ገንዘብ እሰጥ ዘንድ ለአማልክቶቼ መሥዋዕትን አቅርብ እንጂ" አለው የከበረ ቴዎድሮስም ንጉሡን ረገመው ጣዖታቱንም ሰደበ በዚያንም ጊዜ ንጉሡ ተቆጣ። ልብሱንም እንዲገፉት በትምህርቱም ከአመኑ አሕዛብ ጋር በጨለማ ቤት ያሥሩት ዘንድ አዘዘ። የከበረ ቴዎድሮስም ጸለየ በሌሊትም ወጣ ዕንጨቶችንም ሰብስቦ ጣዖቶችን ሁሉ አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጠላቸው እንዳይሰሙ በአገልጋዮቻቸው ላይ እግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ አሳድሮባቸዋልና።
❤ ለንጉሡም በነገሩት ጊዜ አጽንቶ አሠረውና ልዩ ልዩ በሆነ በጽኑ ሥቃይ አብዝቶ ያሠቃየው ዘንድ ለመኰንኑ ሰጠው መኰንኑም እንዲህ አለው "ለንጉሥ ለምን አትሠዋም" የከበረ ቴዎድሮስም "እኔስ ለረከሱ አማልክት አልሠዋም ለከሀዲ ንጉሥም አልታዘዝም" ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከወንበሩ ላይ ተነሥቶ እንደ ነብር ተወርውሮ አንገቱን አነቀውና የከበረ ቴዎድሮስን በምድር ላይ ጥሎ ፊቱን ጸፋው በእግሮቹም ረገጠው እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አይቶ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ላከለት መኰንኑንም ገድሎ ከምድር ዐዘቅት አሠጠመው ለከበረ ቴዎድሮስም በእስያ አገር ውስጥ እየተዘዋወረ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ሃይማኖት እንዲአስተምር መንፈሳዊ ፀዓዳ ፈረስ ሰጠው። ንጉሡም ይህ በሰማ ጊዜ የከበረ ቴዎድሮስን ከነፈረሱ እንዲይዙት በትምህርቱም የአመኑትን ሁሉ እንዲገድሉ መቶ ፈረሰኞች ወታደሮቹን ላከ። ከሴቶችና ከልጆች በቀር ስድስት ሺህ አርባ ስምንት ሰውን ገደሉ። ሊይዙትም ወደ ቅዱስ ቴዎድሮስ በደረሱ ጊዜ ፈረሱ በላያቸው ተወረወረ ከአፉም እሳትን አውጥቶ አመድ እስኪሆኑ አቃጠላቸው ነገር ግን ሌሎች አግኝተው ያዙትና ወደ ንጉሥ ወሰዱት እርሱም ወደ እሥር ቤት እንዲአስገቡት እንዳይበላና እንዳይጠጣም ደጃፎችን እንዲዘጉበት አዘዘ።
❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጸለትና ቃል ኪዳን ሰጠው በዚያንም ጊዜ ከእሥር ቤት አውጥተው ዘቅዝቀው ሰቀሉት ደሙ እንደ ውኃ እስቲፈስ ከላም ቆዳ በተሰራ ጅራፍ ገረፉት ደሙ የነካቸውም ብዙ በሽቶኞች ዳኑ ተዓምራቱንም ያዩና የሰሙ በጌታችን አመኑ በዚያችም ቀን መቶ አርባ ስምንት ሰዎች ተገደሉ። እሊህን የተገደሉትንም ሰማዕታት ወደ እሳት ማደጃ ውስጥ ከእርሱ ጋር ጨመራቸው በዚያንም ጊዜ ነፋስ ነፈሰ መብረቅና ነጐድጎድም ሆነ እሳቱንም አቀዝቅዞት የከበረ ቴዎድሮስ ምን ሳይነካው ከእሳት ውስጥ ወጣ።
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የሚያደርግበትን በአጣ ጊዜ ኃምሳ አራት ልጥር የሚመዝን ልጓም አምጥተው አፉን እንዲለጒሙት እግሮቹንና እጆቹንም በችንካር ቸንክረው ለአንበሳ እንዲጥሉት አዘዘ። አንበሳውም እንባውን እያንጠባጠበ እንደ ሰው አለቀሰለት እንጂ ምን አልነካውም ጌታችንም ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራ፣ መታሰቢያውን ለሚያደርግ፣ ገድሉንም ለሚጽፍ እድል ፈንታውም ከእርሱ ጋር በመንግሥተ ሰማያት ያደርግ ዘንድ ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኋላ የሁለት መቶ ሰው ሸክም እንጨት፣ መቶ ልጥር ባሩድ፣ መቶ ልጥር የዶሮ ማር፣ መቶ ልጥር ነሐስ አመጡ ከማንደጃውም ጨምረው እጅግ እስከሚግል አነደዱት ጸሎቱንም ከፈጸመ በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስን ወደ ነደደው እሳት ወረወሩት ምስክርነቱንም የካቲት28 ፈጸመ።
❤ የመላእክት አለቆች ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ነፍሱን ተቀበሉት በሦስት አክሊላትም አቀዳጁት ሥጋውንም አውሳብያ የተባለች የመኰንኑ ሚስት ወሰደች ዋጋው ብዙ በሆነ ሽቱም ገነዘችውና ወደ ገላትያ ወሰደችው በዕብነ በረድ ሣጥንም አድርጋ በዚያ ቀበለችው ቤተ ክርስቲያንም ሠራችለት ከሥጋውም ታላላቆች ድንቆች ተዓምራቶች ተገለጹ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቴዎድሮስ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላላሙ አሜን። ምንጭ፦ የካቲት 28 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለክሙ_አምዓት_ስሳ። ወበበዐሠርቱ ሠላሳ #ማኅበራነ_ቴዎድሮስ_ማር_መኵሴ_ቴዎድሮስ ዕጓለ አንበሳ። እምኂሩትክሙ ብየ ኃሠሣ። ታናሕስዩ ሊተ ክቡደ አበሳ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_28።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ዘሠርዓ ለአብርሃም። ወመሐለ ለይስሐቅ። ወአቀመ ስምዐ ለያዕቆብ"። መዝ 104፥9። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥8-22፣ ያዕ 3፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥1-17። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 20፥37-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ወራት። ለሁላችንም ይሁንልን።
@sigewe
https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL